ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የአነስተኛ ወጪ ቤቶችን ገንብተው አስረከቡ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማይት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በአዋሬ አካባቢ በ1523.3 ሜትር ካሬ ላይ የተገነባውን ተጨማሪ የአነስተኛ ወጪ ቤቶች ግንባታ መርቀዋል።

የተመረቁት ሁለቱ ባለ 11 ወለል ህንፃዎች በሶስት ወራት ጊዜ ተገንብተው የተጠናቀቁ ሲሆኑ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር የ’መደመር ትውልድ መጽሃፍ ሽያጭ ገቢ እና ከኦቪድ ኮንስትራክሽን ግሩፕ ድጋፍ የተገነቡ ናቸው። ህንፃዎቹ ባለአንድ፣ ባለሁለት እና ባለሦስት የመኝታ ክፍሎች ያላቸው 110 ቤቶች እንዲሁም እታችኛው ወለል ላይ 51 የምድር ቤት ክፍሎችን የያዙ ናቸው።

በተጨማሪም የጋራ የእንጀራ እና ዳቦ መጋገሪያ፣ ማብሰያ እና የማጠቢያ አካባቢዎች የተካተቱባቸው ናቸው። ሁለቱ አፓርትመንቶች በጠባብ ቦታ ላይ ለየአገልግሎቱ በልዩ ሁኔታ የመጠቀም ጥበብ ያረፈባቸው ሲሆኑ፣ ሁሉም ቤቶች ሙሉ እቃ ተገጥሞላቸዋል።

ክብር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በንግግራቸው ባለሃብቶች በበጎ አድራጎት እና ፈጠራ የኦቪድ ኮንስትራክሽን ግሩፕን አርዓያነት እንዲከተሉ ጥሪ አቅርበዋል።

Source: PMOEthiopia

Share to your Network:

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *