በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በአራዳ ክ/ከተማ በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም አካባቢ በኮሪደር ልማት ምክንያት የፀዱ ቦታዎችን ጨምሮ፣ በንፋስ ስልክ ላፍቶ፣ ኮልፌ ቀራንዮ፣ በአቃቂ ቃሊቲ፣ በየካ፣ በቦሌ፣ በአዲስ ከተማ፣ በቂርቆስ፣ በጉለሌ፣ እና በልደታ ክ/ከተሞች የሚገኙ ለተለያዩ አገልግሎቶች የተዘጋጁ ቦታዎችን በጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ለማስተላለፍ እንደሚፈልግ አስታውቋል፡፡
አስተዳደሩ በ10ሩም ክፍለ ከተሞች ባሉ ቦታዎች ያቀረበው የሊዝ መነሻ ዋጋ ዝቅተኛው በካሬ 927 ብር ከ84 ሳንቲም ሲሆን ከፍተኛው ደግሞ በካሬ 2 ሺህ 213 ብር ከ25 ሳንቲም ነው። የአሁኑ የሊዝ ጨረታ፣ የከተማ አስተዳደሩ ባለፈው ዓመት መጨረሻ ካወጣው የሊዝ ጨረታ በኋላ ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ ነው። የቦታ ስፋታቸው ከ2 ሺህ 179 ካሬ ሜትር ስፋት ካለው ቦታ ጀምሮ እስከ ዝቅተኛው 101 ካሬ ሜትር ድረስ የሚገኙ 243 ቦታዎች የሊዝ ጨረታ ወጥቶባቸዋል።

ሙሉ የጨረታውን ዝርዝር ከታች ይመልከቱ።
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ
የመሬት ሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በአራዳ ክ/ከተማ አድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም አካባቢ በኮሪደር ልማት ምክንያት የጸዱ ቦታዎችን ጨምሮ፣ በንፋስ ስልክ ላፍቶ፣ በኮልፌ ቀራንዮ፣ በአቃቂ ቃሊቲ፣ በየካ፣ በቦሌ፣ በአዲስ ከተማ፣ በቂርቆስ፣ በጉለሌ፣ እና በልደታ ክ/ከተሞች የሚገኙ ለተለያዩ አገልግሎቶች የተዘጋጁ የልማት ቦታዎችን በጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ለማስተላለፍ ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች
- ለአንድ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 2.300.00 (ሁለት ሺህ ሶስት መቶ ብር) በቴሌ ብር በመክፈል የጨረታውን ሰነድ ከሚያዝያ 10/2016 ዓ.ም እስከ ሚያዝያ 24/2016 ዓ.ም ከቀኑ 9 ሰዓት ድረስ
በ2merkato.com ወይም afrotender.com መግዛት ይችላሉ። - ማንኛውም በዚህ የመሬት ሊዝ ጨረታ ለመሳተፍ የፈለገ ተጫራች በተራ ቁጥር 1 ላይ በተገለጸዉ ዌብ ሳይት የጨረታ ሰነድ ለመግዛት በመጀመሪያ በስሙ የቴሌ ብር አካውንት በመክፈት ከአካውንቱ ተቀናሽ በማድረግ ሰነዱን መግዛት ይጠበቅበታል።
- ተጫራቾች ቦታዎቹ የሚገኙበት ቦታ በመሄድ አጠቃላይ የቦታዎችን ሁኔታ በማየት ዋጋ ማቅረብ አለባችሁ።
- አንድ ተጫራች በአንድ የጨረታ ዙር ከአንድ ቦታ በላይ መጫረት አይችልም። በመሆኑም ከአንድ በላይ ቦታ ተጫርቶ ከተገኝ ተጫራቹ ከጨረታ ውጪ ይሆናል።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ ሰነድ ላይ በቀረበው መስፈርት መሠረት መሆን ይኖርበታል።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበት ቦታ ስፋት በመነሻ ዋጋ ተባዝቶ ከሚገኘውን ጠቅላላ ዋጋ 50% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የክፍያ ማዘዣ /ሲፒኦ/ ለየቦታ ኮዱ በጋዜጣው ላይ የተቀመጠውን መጠን ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ይህ ሳይሆን ቢቀር ወይንም ከ 50% ቢያንስ ተጫራቹ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከውድድር ይሰረዛል። እንዲሁም አንድ ተጫራች ሌላው በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም። ከአዲስ አበባ ውጪ ከሚገኙ ባንኮች ሲፒኦ ስታሠሩ አዲስ አበባ ከሚገኙ ባንኮች በኔትወርክ የተያያዘ መሆን አለበት፤ ይህ ሳይሆን ቀርቶ ችግር ቢፈጠር ጽ/ቤቱ አይጠየቅም።
- ተጫራቾች የጨረታ መልስ ማቅረቢያ ሰነድ ስትመልሱ፣
7.1 ኦርጅናል ሲፒኦ (CPO)7.2 ኦሪጅናል የመስሪያ ቤቱ ማህተም ያረፈበት የጨረታ መልስ ማቅረቢያ ሰነድ7.3 የተጫራቹ መታወቂያ ኮፒ7.4 ሰነድ ለመግዛት በቴሌ ብር የተከፈለበት ስሊፕ (ደረሰኝ)7.5 ተጫራቹ የሚጫረተው በተወካይ ከሆነ የተወካይ መታወቂያ እና የውክልና ማስረጃ ኮፒ7.6 የውጭ አገር ዜግነት ያለው በትውልድ ኢትዮጵያዊ የሆነ ማንኛውም ተጫራች ከሚኖርበት አገር በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ /ቆንስላ ጽ/ቤት የተሰጠውንና በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተረጋግጦ በውልና ማስረጃ የፀደቀ መታወቂያ የዋናውን ኮፒ ከመልስ ማቅረቢያው ጋር ማያያዝ አለበት።7.7 የንግድ ማኅበራት ለሆኑት በሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ ፅ/ቤት የፀደቀ የማኅበሩን መመሥረቻ ጽሁፍ እና መተዳደሪያ ደንብ ፎቶ ኮፒ ሌሎች ሕጋዊ ሰውነት ያላቸው ድርጅቶች ከሆኑ ሕጋዊነታቸውን የሚያረጋግጥ ሰነድ እና የታደሰ ምስክር ወረቀት ፎቶ ኮፒ7.8 ጨረታው የሚሳተፉት ባልና ሚስት በአንድ ሰነድ ከሆነ ሕጋዊ የጋብቻ ማስረጃ ኮፒ እና በአንድ ወገን ስም የተሠራ የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ማቅረብ አለባቸው።7.9 በአንድ የጨረታ ሰነድ ከአንድ ሰው በላይ ሆነው ለመወዳደር ከፈለጉ ከሰነዶች ማረጋገጫ እናምዝገባ ፅ/ቤት የተረጋገጠ የተደራጁበትን ሕጋዊ ማስረጃ ኮፒ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።7.10 በአጠቃላይ ከላይ የተገለጹትን ማስረጃዎች በፖስታ በማሸግ የጨረታ ቁጥር እና የቦታ መለያ ኮድ በፖስታው ላይ በመጻፍ ሚያዝያ 24/2016 ዓ.ም ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ድረስ ለም ሆቴል አካባቢ ኤም ኤ (M A) ሕንጻ ላይ በሚገኘው በከተማው መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ለዚህ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሚያዚያ 28/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡ዐዐ ሰዓት ጀምሮ በ9 ተከታታይ የሥራ ቀናት በቦሌ ክ/ከተማ አስተደዳር አዳራሽ የሚከፈት ሆኖ ዝርዝሩ በውስጥ ማስታወቂያ ይገለፃል። ተጫራቾች ቦታውን በአካል ለመመልክት ከፈለጉ በ14/8/16ዓ.ም፣16/08/16 ዓ.ም እና በ18/08/16 ዓ.ም ጠዋቱ በ3፡00 እና ከሰዓት በ8፡00 ሰዓት ለጨረታ የተዘጋጁ ቦታዎች የሚገኙበት ክ/ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤት ድረስ በመቅረብ ለዚህ ሥራ በሚመደቡ አስጎብኝዎች አማካኝነት ቦታዎቹን መመልከት ይቻላል።
- ጨረታውን ያላሸነፉ (ተሸናፊ) ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙትን ሲፒኦ የጨረታው አሸናፊዎች በአዲስ ልሳን ጋዜጣ ከተገለጸበት ከ15 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ አጫራቹ መ/ቤት ለባንክ በመላክ | ወዳሠሩበት የባንክ ሂሳብ ተመላሽ ይደረጋል። በካሽ ያሠሩ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናውን ለመረከብ በቅድሚያ የሲፒኦውን ጉርድ ኮፒ ማቅረብና ማንነቱን የሚገልጽ መታወቂያ በመያዝ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ቀርበው መውሰድ አለባቸው። ከላይ በተገለጸው የጊዜ ገደብ ውስጥ ቀርበው ካልወሰዱ ለሚፈጠረው ችግር አጫራቹ መ/ቤት ተጠያቂ አይሆንም።
- መሥሪያ ቤቱ (ቢሮው) የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ የመሬት ልማት አስተዳደር ቢሮ፡-
· በስልክ ቁጥር +251111566440 +251911197478 / +251911714690 መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡
· https://addismayor.gov.et/
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር
የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ
በአዲስ ልሳን ታትሞ የወጣው የቦታዎች መረጃ ከታች ያገኙታል

















