የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ለ2005 ዓ.ም በ20/80 እና በ40/60 የቤት ልማት ፕሮግራም የቤት ተመዝጋቢዎችን ቀደም ሲል በወጣዉ ማስታወቂያ መሰረት አቅምና ፍላጎት ያላቸዉ ተመዝጋቢዎች በማህበር በማደራጀት የቤት ተጠቃሚ እንዲሆኑ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች አጠናቆ የሳይት ዕጣ ለማውጣት በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡
በመሆኑም በ54 ማህበር ለተደራጁ የማህበሩ አባላት በመመሪያው ላይ በተቀመጠው መሠረት ሰባ ከመቶውን (70%) በነባሩ የ20/80 እና የ40/60 የቁጠባ ሂሳብ ከቀን 08/09/2015 – 12/09/2015 ዓም ድረስ እንድታስገቡ እያሳሰብን በቀጣይ በማህበሩ ስም አዲስ የዝግ ሂሳብ ሲከፈት የነባሩ የ20/80 እና የ40/60 ቁጠባ ሂሳብ ወደ አዲሱ የማህበሩ ሂሳብ ተዘዋውሮ ስለሚከፈት ቁጠባ ሂሳቡ የዘጋ እንዲሁም በወቅቱ ያላስገባ ቢሮው በምትኩ እንደሚተካ ከወዲሁ እናሳዉቃለን።
ምንጭ፡ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ


















