• BetBegara.com
  • Buy
  • Rent
  • Sale
  • Services
  • Contact Us
Betegna - ቤተኛ | Ethiopian Housing and Real Estate News & Insights
Advertisement
  • Home
  • Guides
    • Buying Guide
    • Renting Guide
    • Selling Guide
    • Knowledge Base
  • Mortgage
  • Technology
  • Legal
    • Proclamations (አዋጅ)
    • Regulations (ደንብ)
    • Directives (መመሪያዎች)
    • Community Complaints
    • Corruption (ሙስና)
  • Tender
    • Auction (ሐራጅ)
    • Land Lease (የመሬት ሊዝ)
    • Request for EOI
  • Project Highlight
  • More
    • Community & CSR
    • Construction & Projects
    • Construction Material Supply
    • Design & Innovation
    • Public Housing
    • Insights & Profiles
    • Sales & Marketing
    • Property Handover
    • Global
    • Contact Us
No Result
View All Result
Sell, Buy, Rent
  • Home
  • Guides
    • Buying Guide
    • Renting Guide
    • Selling Guide
    • Knowledge Base
  • Mortgage
  • Technology
  • Legal
    • Proclamations (አዋጅ)
    • Regulations (ደንብ)
    • Directives (መመሪያዎች)
    • Community Complaints
    • Corruption (ሙስና)
  • Tender
    • Auction (ሐራጅ)
    • Land Lease (የመሬት ሊዝ)
    • Request for EOI
  • Project Highlight
  • More
    • Community & CSR
    • Construction & Projects
    • Construction Material Supply
    • Design & Innovation
    • Public Housing
    • Insights & Profiles
    • Sales & Marketing
    • Property Handover
    • Global
    • Contact Us
No Result
View All Result
Betegna - ቤተኛ | Ethiopian Housing and Real Estate News & Insights
No Result
View All Result
አይ መሬት ያለው ሰው!!!!

አይ መሬት ያለው ሰው!!!!

Desalegn Kebede by Desalegn Kebede
February 2, 2025
in Insights & Profiles
A A
0
0
SHARES
Share on FacebookShare on LinkedIn

በቅርቡ በስራ ላይ እየገጠመን ያለው ነገር ” አይመሬት ያለው ሰው ” እያስባለን ነው። ከምንሰራው ስራ አንዱ መሬት ወይም ነባር ቤት ያላቸው ባለይዞታዎችንና ገንዘብ ያላቸውን በማስማማት ወደ አብሮማልማት እንዲገቡ ፣ የተገነባ ቤት ያላቸው በመሬቱ ግምት የተገነባ ቤት ሰጥተው በአይነት እንዲገበያዩ፣ የተወሰነ ብር ተሰጥቶ ከሚገነባ እንዲወስዱ …አልሚዎችም የሚያዋጣቸውን ብዙ አማራጮችን አቅርቦ በቁጥር እስልቶ አስማምቶ ማፈራረምና ፕሮጀክቱን ማስተግበር ላይ እስከተስማማነው ድረስ አብሮ መስራት ነው።

ይህ በሌሎች ሀገራትም የተለመደ አሰራር ነው። ለምሳሌ በካናዳ ከ ሃያ ዓመታት በላይ እድሜ ያስቆጠረ ከሶስት ሺህ በላይ አልሚዎች አባል የሆኑበት የሪል እስቴት ኢንቨስትመንት ኔትወርክ (Real Estate Investors Network ) የሚባል ማህበር አላቸው።

ማህበሩ በየወቅቱ ያሉ የኢንቨስትመንት አሰራርና የተለያዩ አዋጭ አማራጮችን እያጠና ያለመድሎ ለሁሉም አባል ተቋማት ያቀርባል። አልሚዎቹ የሚያመቻቸውን የኢንቨስትመንት አማራጭ መርጠው በራሳቸው ተጨማሪ ጥናት አድርገው ወደ ትግበራ ይገባሉ።

የዚህ አይነት ተቋም በሀገራችን ቢኖረን ኖሮ በዚህ ወቅት ሊያቀርብ ከሚችለው አገልግሎት ውስጥ አንዱና ዋናው በሀገር ውስጥ ያለውን አቅም በማሰባሰብ በጋራ የማልማት ( Joint venture ) ይመስለኛል። ምክንያቱም የመሬት ውድነት አለ፣ የገንዘብ አቅርቦት እጥረት አለ፣ ፕሮጀክቶች የሚፈልጉት ወጪ ከፍ እያለ በወቅቱ ማጠናቀቅ እየከበደ ነው፣ ከሚጀመረው አዲስ ፕሮጀክት ይልቅ ተጀምሮ የሚቆመው በርክቷል፣ የጀመሩም ማስጨረሻው መላው ጠፍቷቸዋል፣ መሬት ያላቸው ለገበያ ቢያወጡም ጠያቂው ጥቂት ነው፣ መሬት ኖሯቸው ገዢ ወይም አብሮ የሚያለማ ፈላጊዎች እየተበራከቱ ነው።

ግን ምን ያደርጋል ብዙው ባለ መሬቶቹም ሆኑ ኢንቨስትመንት ውስጥ የሚገቡትን ለማስማማት በሚደረግ ጥረት ውስጥ መሬት/ይዞታ ያላቸው ወገኖቻችን አሁንም በቀደመው የመሬት ዋጋ እንዲሰላላቸው ወይም ስሌት የሌለበት ቦሌም ሸጎሌም ላይ በ70/30 ካልሆነ ብለው ግትር እያሉ ንብረታቸውን ዋጋ እያሳጡት መሆኑን ሳይ እየበሰጨኝ ነው።

መሬት በቢሊየን ሲጠየቁ እምብኝ ያሉ በመቶ ሚሊየኖች ሲለመኑ የነበሩ መሬታቸው ህንጻ ሳይሆን ሳር በቅሎበት መናፈሻ ሆኖ እኛም በብስክሊሊት ሽር ብትን እያልንበት እነሱም አራብሳ ላይ በተሰጣቸው ምትክ እየተንጎማለሉ እንዳሉ አብረን እያየን … አሁንም መሬት ያላቸው ሰዎች ዋጋ ለመቀነስ አልፈቀዱም።

መሬት በጣም ውድ እየሆነ መጥቶ ከናበረባቸው ምክንያቶች አንዱ በመንግስት በኩል የነበረው የመሬት አቅርቦት እጅግ ውሱን ወይም ምንም ሆኖ በነበረበት ወቅት ነው። አሁን ግን መንግስት በኮሪደር ልማትና ከተማ ማደስ ፕሮግራም የተነሳ በርካታ ለግንባታ የሚሆን መሬት በጨረታና በድርድር ለአንዳንዶችም በምደባ በሰፊው እያቀረበ ይገኛል።

ብዙዎች ዋጋ ቀንሰው ወቅቱን ታሳቢ ያደረገ ግብይት ከመፈጸም ወይም ወደቋሚ የተመጣጠነ ንብረት ከመቀየር ይልቅ የድሮ የመሬት ውድነት ዞሮ ተመልሶ ይመጣል ብሎ ማሰብ …ጥፋት ነው። ኦገኔ ጊዜው ሌላ መላውም ሌላ ነው።

አይደለም መሬትና ከቤትነት ይልቅ በመሬትነት የሚጠራ ቤት ያለበት ቤት ቀርቶ በጅምር ያለ ያልተጠናቀቀ ግንባታ ከጥቂት ጊዜያት በኋላ ጣጣ ይዞ የሚመጣ ነውና ጥቅምን ቀንሶ ፣ ትርፍን አጋርቶ ፣ አቅምን አሰባስቦ አብሮ ማጠናቀቁ ያድናል….

“አብሮ ማልማት ያድናል” የሚል መፈክር አጽፈን ድምጽ ማጉያም እየጮህን በጎዳና ላይ እንጩህ እንዴ?

በአንዱ የሀገራችን ክፍል የሆነ ነው አሉ። አንድ ዘመድ ያረፈባቸው ወገኖቹ አስክሬኑን ወደ ትውልድ ስፍራው ለመውሰድ ሲጠይቁ ውድ ዋጋ በመጠየቃቸው ቢጨንቃቸው ተስማምተው ያስጭኑታል …የሚፈልጉበት ቦታ ደርሰው ክፈሉ ሲባሉ ያላቸውን ሰጥተው አስክሬኑን እንዲሰጣቸው ቢጠይቁት እምቢ ብሎ የሰጣቸውን ብር ይመልስላቸዋል…. እነሱም አስክሬኑን ትተው መጓዝ ይጀምራሉ …ሹፌሩ ኑ ከፍላችሁ ውሰዱት ሲላቸው…የመለሱለት መልስ “ቀቅለህ ብላው” የሚል ነበር….

አሁንም መሬት ያላቸው ሰዎች ገበያው የሰጣቸውን ተቀብለው ቢሸጡ፣ በቤቶች ቢለውጡ ወይም አቅም ካላቸው ግለሰቦችና ድርጅቶች ጋር በጋራ ቢያለሙ ይመከራሉ ….እምቢ ካሉ…”ቀቅለህ ብላው ” የሚል ባይኖርም “ጎመን ተክለህ ቀንጥሰህ ቀቅለህ ጨው ጨምረህ ብላበት” የሚለው ወይም መልክ የሚይስይዘው ከበራቸው ላይ እይጠፉም።

አሁን ጽፌ ልወጣ ስል አንድ አባገዳ ያሉኝ ትዝ አለኝ “በጊዜ ነው መጠቅለል አለ እባብ ጭንቅላቱ እንዳይቀጠቀጥ”። ልብ ያለው ልብ ይበል። እኛም አይ መሬት ያለው ሰው ማለታችንን እናቁም።
ለማንኛውም ቁልቁል እየወረደ ላለው የሪል እስቴት ኢንቨስትመንት አንዱ ማቃኛው አቅምንና ችሎታን አሰባስቦ በጋራ ማልማት ነው።

Tags: Joint Ventureland ownershipland price inflationproperty valuereal estate Ethiopia
Previous Post

የቤቶችን የገንዘብ ችግር ለመቅረፍ የቤቶች ፋይናንስ ሥርዓት እንደ ሀገር ተግባራዊ ሊደረግ መሆኑ ተሰማ

Next Post

ጎዶ ሃውሲንግ ኤንደ ስማርት ሪል እስቴት ለመኖርያ ቤትና ለሱቆች ለአንድ ሳምንት የሚቆይ ኤክስፖ ማዘጋጀቱን ገለፀ

Desalegn Kebede

Desalegn Kebede

ኢንጂነር ደሳለኝ ከበደ የሲቪል ምህንድስና ባለሙያ፣ የሪል እስቴት አማካሪ፣ አሰልጣኝ እና ጸሐፊ ሲሆኑ፤ በግንባታ፣ በሪል እስቴት ስልጠና እና በገበያ ጥናት ዘርፎች የሚታወቀውን አቡቀለምሲስ ግሩፕ (Abukelemsis Group) መሥራችና ዋና ሥራ አስኪያጅ ናቸው።

ተዛማጅ ጽሑፎች

የሪል እስቴት አልሚዎች ማህበር የ7% የብድር ወለድ ጥያቄ በባለሙያዎች መካከል ያስነሳው ክርክር
Insights & Profiles

የሪል እስቴት አልሚዎች ማህበር የ7% የብድር ወለድ ጥያቄ በባለሙያዎች መካከል ያስነሳው ክርክር

November 18, 2026
በከፊል የተጠናቀቁ አፓርትመንቶች መኖሪያ ቤቶች አይደሉም
Insights & Profiles

በከፊል የተጠናቀቁ አፓርትመንቶች መኖሪያ ቤቶች አይደሉም

September 25, 2026
ተሾመ ግርማ በቴምር ፕሮፐርቲስ የሽያጭና ማርኬቲንግ ሥራ አስኪያጅ፤ ቀደም ሲል የሀሞና መስራችና በአያት ሪል እስቴት የሽያጭ ሰራተኛ
Insights & Profiles

በስምንት ዓመታት የሪል እስቴት ጉዞዬ ከ1,000 በላይ ቤቶችን ለመሸጥ የቻልኩበት ሚስጥር

September 25, 2026
Next Post
ጎዶ ሃውሲንግ ኤንደ ስማርት ሪል እስቴት ለመኖርያ ቤትና ለሱቆች ለአንድ ሳምንት የሚቆይ ኤክስፖ ማዘጋጀቱን ገለፀ

ጎዶ ሃውሲንግ ኤንደ ስማርት ሪል እስቴት ለመኖርያ ቤትና ለሱቆች ለአንድ ሳምንት የሚቆይ ኤክስፖ ማዘጋጀቱን ገለፀ

  • Trending
  • Comments
  • Latest
የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የወጣ አዋጅ 721/2004

የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የወጣ አዋጅ 721/2004

April 23, 2024
ስለ ግብር የሚከፈልበት የቤት ኪራይ ገቢ

ስለ ግብር የሚከፈልበት የቤት ኪራይ ገቢ

April 6, 2024
በአዲስ አበባ የቤት ሽያጭ ዋጋ ተመን ላይ በድጋሚ ማሻሻያ ተደረገ

በአዲስ አበባ የቤት ሽያጭ ዋጋ ተመን ላይ በድጋሚ ማሻሻያ ተደረገ

April 3, 2024
የመሬት ልማትና አስተዳር ደንብ ቁጥር 163/2016

የመሬት ልማትና አስተዳር ደንብ ቁጥር 163/2016

April 22, 2024
ስለ ሪል እስቴት ምን ያውቃሉ?

ስለ ሪል እስቴት ምን ያውቃሉ?

August 18, 2023
Home pic

ቤት ለሚገዙ እና ለሚሸጡ አካላት ማሳሰቢያ ተሰጠ

0
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤት አቅርቦትን ለማሳደግ የሚያስችል ውይይት ከሪል እስቴት አልሚዎች ጋር ውይይት አደረገ!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤት አቅርቦትን ለማሳደግ የሚያስችል ውይይት ከሪል እስቴት አልሚዎች ጋር ውይይት አደረገ!

0
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ያስተዋወቀበትን የገርጂ መኖሪያ መንደር ፕሮጀክት ሊያስመርቅ ነው

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ያስተዋወቀበትን የገርጂ መኖሪያ መንደር ፕሮጀክት ሊያስመርቅ ነው

0
ባለ 9 ወለል ህንፃ በተጀመረ በ69ኛ ቀኑ ተጠናቀቀ!!

ባለ 9 ወለል ህንፃ በተጀመረ በ69ኛ ቀኑ ተጠናቀቀ!!

0
ስለ ሪል እስቴት ምን ያውቃሉ?

ስለ ሪል እስቴት ምን ያውቃሉ?

0
የሪል እስቴት አልሚዎች ማህበር የ7% የብድር ወለድ ጥያቄ በባለሙያዎች መካከል ያስነሳው ክርክር

የሪል እስቴት አልሚዎች ማህበር የ7% የብድር ወለድ ጥያቄ በባለሙያዎች መካከል ያስነሳው ክርክር

November 18, 2026
በጋዜቦ አደባባይ አካባቢ በግንባታ ሂደት ላይ ከነበረ ሕንጻ ላይ የወደቁ ሦስት ሠራተኞች ሕይወታቸውን አጡ

በጋዜቦ አደባባይ አካባቢ በግንባታ ሂደት ላይ ከነበረ ሕንጻ ላይ የወደቁ ሦስት ሠራተኞች ሕይወታቸውን አጡ

November 14, 2026
በ5 ዓመታት ቤቶችን ገንብተን ለማስረከብ የገባነውን ቃል በተግባር ለማረጋገጥ እየተጋን ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

በ5 ዓመታት ቤቶችን ገንብተን ለማስረከብ የገባነውን ቃል በተግባር ለማረጋገጥ እየተጋን ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

November 13, 2026
የ1.5 ሚሊዮን መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት ወደ ተግባር ምዕራፍ ተሸጋግሯል

የ1.5 ሚሊዮን መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት ወደ ተግባር ምዕራፍ ተሸጋግሯል

November 12, 2026
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከዩኤን ሃቢታት ዋና ዳይሬክተር አናክላውዲያ ሮስባክ ጋር መወያየታቸውን ገለፁ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከዩኤን ሃቢታት ዋና ዳይሬክተር አናክላውዲያ ሮስባክ ጋር መወያየታቸውን ገለፁ

November 11, 2026

ብዙ የተነበቡ

  • የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የወጣ አዋጅ 721/2004

    የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የወጣ አዋጅ 721/2004

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ስለ ግብር የሚከፈልበት የቤት ኪራይ ገቢ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአዲስ አበባ የቤት ሽያጭ ዋጋ ተመን ላይ በድጋሚ ማሻሻያ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የመሬት ልማትና አስተዳር ደንብ ቁጥር 163/2016

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ስለ ሪል እስቴት ምን ያውቃሉ?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Categories

  • Community & CSR (28)
  • Construction & Projects (29)
  • Construction Material Supply (9)
  • Design & Innovation (18)
    • Architecture (2)
    • Technology (14)
  • Global (4)
  • Insights & Profiles (20)
  • Legal Updates (89)
    • Community Complaints (8)
    • Corruption (ሙስና) (2)
    • Directives (መመሪያዎች) (1)
    • Proclamations (አዋጅ) (7)
    • Regulations (ደንብ) (2)
  • Mortgages & Finance (14)
  • Property Handover (16)
  • Public Housing (71)
  • Real Estate Guides (13)
    • Buying Guide (3)
    • Knowledge Base (1)
    • Renting Guide (2)
    • Selling Guide (7)
  • Sales & Marketing (67)
  • Tenders & Bids (60)
    • Land Lease (29)
    • Request for EOI (1)
  • Home
  • Guides
  • Mortgage
  • Highlights
  • Legal Updates
  • Tenders & Bids
Betegna Logo Footer

Betegna – ቤተኛ, powered by Betbegara.com, is a media platform that focuses on Ethiopian housing and real estate news, developments, technology, policies, and lifestyle.

© 2026 Betegna – ቤተኛ | Ethiopian Housing and Real Estate News & Insights

  • Home
  • Guides
    • Buying Guide
    • Renting Guide
    • Selling Guide
    • Knowledge Base
  • Mortgage
  • Technology
  • Legal
    • Proclamations (አዋጅ)
    • Regulations (ደንብ)
    • Directives (መመሪያዎች)
    • Community Complaints
    • Corruption (ሙስና)
  • Tender
    • Auction (ሐራጅ)
    • Land Lease (የመሬት ሊዝ)
    • Request for EOI
  • Project Highlight
  • More
    • Community & CSR
    • Construction & Projects
    • Construction Material Supply
    • Design & Innovation
    • Public Housing
    • Insights & Profiles
    • Sales & Marketing
    • Property Handover
    • Global
    • Contact Us
No Result
View All Result
Sell, Buy, Rent