ኩባንያችን ከተመሠረተ የአራት ዓመት ዕድሜ ብቻ ቢኖረውም ከወዲሁ የ30 ዓመት ሥራ ሠርቷል ሲሉ የአፍሪካ ሆልዲንግ ግሩፕ መሥራችና ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ደረጀ ማሙዬ ተናገሩ።
አፍሪካ ሆልዲንግ ግሩፕ በአፍሪካ ግዙፉ ኩባንያ ነው ሲሉ የተናገሩት ዋና ሥራ አስኪያጁ ኩባንያቸው ‘’ቤቶን በካምፓኒዮ ይገንቡ’’ በሚል መሪ ቃል ሲሠራ መቆየቱን ተናግረዋል።
አፍሪካን ሆልዲንግ ግሩፕ በሚቀጥሉት 10 ዓመታት ውስጥም 500ሺ ቤቶችን ገንብቶ ለማስረከብ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን የገለፁት አቶ ደረጀ ከጥቁር አንበሳ ከፍ ብሎ ተክለሃይማኖት አካባቢ አሥር ሺ ካሬ ሜትር ላይ 15 ቢሊዮን በሚገመት ብር ከምድር በታች 4 ወለል፣ ከምድር በላይ ደግሞ 35 ወለል የያዘ እና 5 ህንጻዎችን በአንድ ላይ ያጣመረ ጎዶ ሃውስ ኤንድ ስማርት ሪል እስቴት እየተገነባ መሆኑን ተናግረዋል።
በዚህም እስከ ሰኔ 30 ቀን 25 በመቶ ለሚከፍሉ ደንበኞች ኩባንያቸው ታላቅ ቅናሽ ማዘጋጀቱን ይፋ አድርገዋል። ዋጋው ለአፓርትመንት በካሬ 75ሺ ብር ሲሆን ለንግድ ሱቆች ደግሞ በካሬ ከ320ሺ ብር ጀምሮ መሆኑ ተገልጿል።
አፍሪካን ሆልዲንግ ግሩፕ ማህበራዊ ካፒታልን በማቀናጀትና በፈጠራ ሥራዎች ከአፍሪካ ልዩ በሆነና በከፍተኛ ደረጃ በተደራጀ ሁኔታ በአሥር ዓመታት ጊዜ 20 ሚሊየን ባለአክሲዮኖችን በማሰባሰብ ከ150 በላይ ኩባንያዎችን ለማቋቋም እንዲሁም ለ155,000 ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር አቅዶ በመንቀሳቀስ ላይ እንደሚገኝ የኩባንያው መሥራችና ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ደረጀ ማሙዬ አክለው ተናግረዋል።
ምንጭ፡ ሀገሬ ቴቪ


















