ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ለኑሮ አመቺ ያልነበሩ ቤቶችን አፍርሰን በአጭር ጊዜ መልሰን የገነባናቸውን እና ያደስናቸውን 907 ቤቶች እንኳን ለትንሳኤ በዓል አደረሳችሁ ብለን ዛሬ ለነዋሪዎች አስተላልፈናል ብለዋል።
አዳዲስ ግንባታዎችንም አስጀምረናል ሲሉም ከንቲባ አዳነች አስታውቀዋል።
አርጅተው በመፍረስ ላይ የነበሩ ጎስቋላ ቤቶችን አፍርሰን ለዘመናዊ አኗኗር አመቺ በሆነ መልክ በነበሩበት ቦታ ላይ መልሰን የገነባነው በርካታ ልበ ቀና ባለሃብቶችን በማስተባበር ነው ሲሉም አክለዋል በመልዕክታቸው።

ጥሪያችንን በመቀበል ለወገኖቻችሁ በመድረስ ማህበራዊ ኃላፊነታችሁን የተወጣችሁ የከተማችን ባለሃብቶችን በተጠቃሚ ነዋሪዎቹ እና በራሴ ስም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ ብለዋል።
ነዋሪዎቻችንም የዚህ እድል ተጠቃሚ ስለሆናችሁ እንኳን ደስ አላችሁ! ማህበራዊ ፍትህ የነገሰባት አዲስ አበባን የመገንባት ስራችን ተጠናክሮ ቀጥሏል ሲሉም ገልጸዋል።

















