የሪል እስቴት ግብይት መስከረም ወር ላይ ባንኮች ብድር ይለቃሉ ተብሎ በተወሰደ ግምት አልሚዎች ለሽያጭ ያወጧቸው ምርቶቻቸው ላይ ዋጋ በመጨመራቸውና አንዳንዶችም የተሻለ ዋጋ ጥበቃ ለሽያጭ ባለማውጣታቸው ወይም መሸጥ በማቆማቸው ገዢውም የተሻለ ጊዜ ይመጣል በማለት በገበያው ውስጥ ገዢና ሻጭ እዛና እዚህ ካብ-ለ-ካብ ተፋጠው ይገኛሉ።
መንግስትም የ1.5 ሚሊዮን ቤት አቅርቦት እቅድ ይዞ ቀርቧል። ይህ የመንግስት እቅድ በሪል እስቴት አልሚዎች እየተገነቡ ያሉትን፣ ጀምረው ያቆሙትን፣ ግንባታ ፈቃድ አውጥተው ያልጀመሩትን፣ ቦታ ወስደው መገንባት ያልጀመሩትን፣ ከመንግስት ጋር በ 70/30 እና መሰል ማዕቀፎች የሚደረጉ ልማቶችን (PPP)፣ የማህበር ቤት ገንቢዎችን፣ በጅምር ያሉ ያልተጠናቀቁ ኮንዶሚኒየም ቤቶችን ….. እንዲሁም በአዳዲስ ቴክኖሎጂና በተለየ አቅም ለሚገነቡ የሚመቻቹ ግዙፍ መንደሮች ግንባታና በአቅም ላይ የተመሰረተ ሰፋፊ የመሬት አቅርቦትና ሌሎች ሁኔታዎች የቤት ግንባታን ያፋፍመዋል ቁጥጥሩንም ያጠብቃል ለስኬታማዎቹ አልሚዎችም ድጋፉን ይጨምራል የቢሮክራሲ መስመሩን ያሳጥራል ተብሎም ይጠበቃል።
ይህ ሁሉ አካሄድ አቅም ላለው ቤት ገዢ ጥሩ አማራጭን ይዞ ሲመጣ በዚህ ሁሉ መሃል ቀድመው ገንብተው ያልሸጡ አልሚዎች ግን ምን እንደሚገጥማቸው እንዳላቸው? ያሳዝኑኛል።
በቅርቡ በኦሮሚያ ክልል በሸገር ሲቲ በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች ለሚገኙ የክልሉ ተወላጆች (ዲያፖራ) ያቀረበው የቤት ባለቤት የሚያደርግ አማራጭ በሸገር ሲቲ ባሉ አልሚዎችና የቤት ዋጋ ላይ ያመጣውን ተጽዕኖ በእጁ እሳት ያልናካ ሰው አይረዳውም።
ወቅቱ ከሚጠበቀው ብቻ ሳይሆን ከሚገባው በላይ በሚለዋወጥ ሂደት ተሯሩጦ የሚያሯሩጥ አብሮ ወይም ቀድሞ መሮት ለማይችል አዙሮ የሚጥል ከገደል የሚጨምር ከገደል አውጥቶ ለጅብ የሚሰጥ አይነት ነውና አልሚዎችዬ ዓይናችሁን ከፍታችሁ እያያችሁ ……..በአጭሩ መብረቅ በእጅ እንደመያዝ ያለ ነው የሚሆነው… እየፈጠናችሁ።


















