የ7ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ ማስተካከያ እና የተሰረዙ ቦታዎችን ስለማሳወቅ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የከተማ ቦታን በሊዝ ጨረታ ስለመፍቀድ በወጣው የሊዝ አዋጅ 721/2004 መሰረት ለ7ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ በ8 ክ/ከተሞች የተዘጋጁ ቦታዎችን በጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ለማስተላለፍ ጥቅምት 01 ቀን 2018 ዓ.ም አዲስ ልሳን ጋዜጣ ማስታወቂያ ማውጣቱ ይታወቃል፡፡
ይሁን እንጂ በወጣው ጋዜጣ ላይ በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ከቀረቡ ቦታዎች በተራ ቁጥር 43 የቦታ ኮድ LDR-KOL-MIX-00015003 የሚለው በቦታ ኮድ LDR-KOL-MIXoool5o04 እና ተራ ቁጥር 44 የቦታ ኮድ LDR-KOL-MIX-000l5004 የተባለው በቦታ ኮድ LDR-KOL-MIXoool5o03 በሚል የተስተካከለ መሆኑን እየገለጽን
በተጨማሪም ለጨረታ ከወጡት ቦታዎች መካከል የቦታ ኮዳቸው ከዚህ በታች የተገለጹ በቦሌ ክ/ከተማ 30 እና በን/ስ/ላፍቶ ክ/ከተማ 34 ቦታዎች በድምሩ 64 ቦታዎች ከጨረታ የተሰረዙ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ምንጭ፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ


















