የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የከተማ ቦታን በሊዝ ጨረታ ስለመፍቀድ በወጣው የሊዝ አዋጅ 721/2004 መሰረት ለ7ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ በ8 ክ/ከተሞች የተዘጋጁ ቦታዎችን በጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ለማስተላለፍ ጥቅምት 01 ቀን 2018 ዓ.ም አዲስ ልሳን ጋዜጣ ማስታወቂያ ማዉጣቱ ይታወቃል፡፡
ይሁን አንጂ ለጨረታ ከወጡት ቦታዎች መካከል ቅዳሜ ጥቅምት 22 ቀን 2018 ዓ.ም በወጣው አዲስ ልሳን ጋዜጣ ላይ የተገለፁ በቦሌ 30 ቦታዎች፣ በንፋስ ስልክ ላፍቶ 34 ቦታዎች በድምሩ 64 ቦታዎች ከጨረታ የተሰረዙ መሆኑን መግለፃችን ይታወሳል፡፡
በተጨማሪም የቦታ ኮዳቸው ከዚህ በታች የተገለጹ በለሚ ኩራ 12፣ በኮልፌ ቀራንዮ 17 እና በን/ስ/ላፍቶ 17 ቦታዎች በድምሩ 46 ቦታዎችም ከጨረታ የተሰረዙ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ
ከጨረታ የተሰረዙ ቦታዎች ከታች ይገኛሉ።


















