የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽንና ኦቪድ ግሩኘ የፒያሳ መልሶ ማልማት አካል የሆኑ ዘመናዊ የንግድ ሞሎችንና የመኖሪያ ቤቶችን ለመገንባት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ።
የግንባታ መግባቢያ ስምምነቱን የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ረሻድ ከማል እና የኦቪድ ግሩኘ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዮናስ ታደሰ ተፈራርመዋል።
የመግባቢያ ስምምነቱ የፒያሳ መልሶ ማልማት አካል በሆነው 9 ነጥብ 5 ሄክታር መሬት ላይ አራት ግዙፍ የንግድ ሞሎችንና የመኖሪያ ቤት ግንባታን ከአንድ ዓመት ባነሰ ጊዜ (በ6 ወራት) በማጠናቀቅ ለማስረከብ የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል።
በስምምነቱ የወርቅ ቤቶች የንግድ ሱቅ ሞል ( FHC Gold Plaza ) ፣ መዝቦልድ ሞል እና ጣይቱ የመኖሪያ አፓርትመንት በአልሙኒየም ፎርም ወርክ ቴክኖሎጂ ከአንድ አመት ባነሰ ጊዜ ገንብቶ ወደ አገልግሎት ለማስገባት የሚያስችል ነው።

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ረሻድ ከማል፥ ኦቪድ ኩባንያ በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በሥራ ላይ እያዋለ የሚገኝ ተቋም በመሆኑ ስምምነቱን ታሪካዊ ያደርገዋል ብለዋል።
ስምምነቱም የመንግሥትና የግል አጋርነት ትብብርን በማሳደግ አዲስ የሥራ ባህል እንዲፈጠር የሚያደርግ መሠረታዊ ጉዳይ መሆኑን ገልፀዋል።
ኮርፖሬሽኑ ፕሮጀክቶችን በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ የሚያስችለውን ዘመናዊ የፕሮጀክት አስተዳደር የዘረጋ በመሆኑ የሳይቶቹን ግንባታ በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ እንደሚያስችለውም ተናግረዋል።
በኮርፖሬሽኑ ታሪክም በብዛት እና በዘመናዊነቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚገነባ የመጀመሪያው የንግድ ሞሎችና ፕላዛ ግንብታ ፕሮጀክት እንደሆነም ክቡር ዋና ሥራ አስፈፃሚው ጠቁመዋል።

የአቪድ ግሩኘ ዋና ሥራ አስፈፃሚ በበኩላቸው ከዚህ በፊት ከኮፖሬሽኑ ጋር በመሆን በ18 ወራት ጊዜ ውስጥ ግዙፍ የመኖሪያ መንደር ገንብተው ማጠናቀቃቸውን አሰታወሰው ፣ ውለታ የገቡትን የንግድ ሞሎችን እና የመኖሪያ ቤቶችን በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ አቪድ አጠናቆ እንደሚያስረክብ ቃል ገብተዋል።
ሳይቶችን በ6 ወራት ለማጠናቀቅ የሚያስችለው የአልሙኒየም ፎርምወርክ ቴክኖሎጂም ለግንባታ ዝግጁ ማድረጋቸውንም አቶ ዮናስ ታደሰ አስተውቀዋል፡፡
ፕሮጀክቶችን በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዘመናዊ የፕሮጀክት አስተዳደር ሥርዓት ምቹ እንደሆነም ገልፀዋል።
ሞሎቹ እና የመኖሪያ ቤቶቹ የሚገነቡት በፒያሳ መልሶ ማልማት ለልማት ዝግጁ በሆኑት የኮርፖሬሽኑ ይዞታዎች ላይ ነው።
ምንጭ፦ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን


















