• BetBegara.com
  • Buy
  • Rent
  • Sale
  • Services
  • Contact Us
Betegna - ቤተኛ | Ethiopian Housing and Real Estate News & Insights
Advertisement
  • Home
  • Guides
    • Buying Guide
    • Renting Guide
    • Selling Guide
    • Knowledge Base
  • Mortgage
  • Technology
  • Legal
    • Proclamations (አዋጅ)
    • Regulations (ደንብ)
    • Directives (መመሪያዎች)
    • Community Complaints
    • Corruption (ሙስና)
  • Tender
    • Auction (ሐራጅ)
    • Land Lease (የመሬት ሊዝ)
    • Request for EOI
  • Project Highlight
  • More
    • Community & CSR
    • Construction & Projects
    • Construction Material Supply
    • Design & Innovation
    • Public Housing
    • Insights & Profiles
    • Sales & Marketing
    • Property Handover
    • Global
    • Contact Us
No Result
View All Result
Sell, Buy, Rent
  • Home
  • Guides
    • Buying Guide
    • Renting Guide
    • Selling Guide
    • Knowledge Base
  • Mortgage
  • Technology
  • Legal
    • Proclamations (አዋጅ)
    • Regulations (ደንብ)
    • Directives (መመሪያዎች)
    • Community Complaints
    • Corruption (ሙስና)
  • Tender
    • Auction (ሐራጅ)
    • Land Lease (የመሬት ሊዝ)
    • Request for EOI
  • Project Highlight
  • More
    • Community & CSR
    • Construction & Projects
    • Construction Material Supply
    • Design & Innovation
    • Public Housing
    • Insights & Profiles
    • Sales & Marketing
    • Property Handover
    • Global
    • Contact Us
No Result
View All Result
Betegna - ቤተኛ | Ethiopian Housing and Real Estate News & Insights
No Result
View All Result
ዩስራ ሆም ሁለተኛውን የአሽሊ ፈርኒቸር ቅርንጫፍ ከፈተ

ዩስራ ሆም ሁለተኛውን የአሽሊ ፈርኒቸር ቅርንጫፍ ከፈተ

Betegna Team by Betegna Team
June 28, 2026
in Construction Material Supply
A A
0
0
SHARES
Share on FacebookShare on LinkedIn

በአሜሪካ ለ80 ዓመታት ዓለም አቀፍ ብራንድ ሆኖ የዘለቀው አሽሊ ፈርኒቸር ለዩስራ ሆም በሰጠው የብቸኛ ወኪልነትና አቅራቢነት ፍቃድ ኢትዮጵያ ውስጥ ሁለተኛ ቅርንጫፉን ከፍቷል።

ባለፈው ጥር ወር የመጀመሪያውን ቅርንጫፍ ዩስራ ሆም ብስራተ ገብርኤል አካባቢ መክፈቱ የሚታወቅ ሲሆን ዛሬ ደግሞ ሁለተኛ ቅርንጫፉን በጉርድ ሾላ ማሳያው አስመርቋል።

ከ155 በላይ ሀገራት ታዋቂ የሆነው አሽሊ ፈርኒቸር የኢትዮጵያን ገፅታ በመልካም ጎን በማሳየትና ዓለም አቀፍ ግንኙነቷን በማጠናከር ረገድ የራሱን ሚና እንደሚያበረክት ይታመናል።

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ፣ የዩስራ ሆም መሥራችና ዋና ስራ አስፈፃሚ ዩስራ ኑር ሁሴን ረጃ እንዲሁም የአሽሊ ፈርኒቸር የሥራ መሪዎች በተገኙበት ቅርንጫፉ በይፋ የተመረቀ ሲሆን ታላላቅ የንግድ ሰዎች ፣ ዲፕሎማቶች እና የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ተገኝተዋል።

እንደሚታወቀው ኢትዮጵያ እያስመዘገበችው ያለው የቱሪዝም ዘርፍ ዕድገት እና በመላ ሀገሪቱ እየተስፋፋ የመጣው የዘመናዊ ሆቴሎች ግንባታ የዓለም አቀፍ ግዙፍ ኩባንያዎችን ትኩረት እየሳበ ይገኛል።

በዓለም የፈርኒቸር ኢንዱስትሪ ቀዳሚ የሆነው የአሜሪካው አሽሊ ፈርኒቸር ወደ ኢትዮጵያ ገበያ በይፋ መግባቱ የሀገሪቱን የግንባታና የእንግዳ ተቀባይነት (Hospitality) ዘርፍ ይበልጥ እንደሚያጠ ናክር ተገልጿል።

ኢትዮጵያ ያላትን የተፈጥሮ ፣ የታሪክ እና የባህል ፀጋዎች በመጠቀም አዳጊ የቱሪዝም ተስፋ ካላቸው የአፍሪካ ሀገራት መካከል ቀዳሚ እየሆነች ትገኛለች ያሉት የዩስራ ሆም መሥራች ወ\ሮ ዩስራ ኑር ሁሴን ሲሆኑ ድርጅታቸው የመጀመሪያውን የአሽሊ ፈርኒቸር ቅርንጫፍ በከፈተ በስድስት ወሩ ሁለተኛውን በይፋ በማስመረቁ ታላቅ ኩራት ይሰማዋል ብለዋል።

በአሽሊ ፈርኒቸር የአፍሪካ እና የእንግሊዝ ምክትል ፕሬዚዳንት ማርክ ማራስ በምረቃ መርሀ ግብሩ ላይ በሰጡት መግለጫ ዩስራ ሆም ከአሽሊ ፈርኒቸር የሚጠበቀውን መስፈርት አሟልቶ በመገኘቱ የወኪልነት እና የአቅራቢነት ማረጋገጫ መስጠቱን ተናግረዋል። አሽሊ ፈርኒቸር በፍሬንቻይዝ ለዩስራ ሆም ምርቶቹን በማቅረቡ ኩራት ይሰማዋል ሲሉም ሚስተሩ ማርክ ተናግረዋል።

የአፍሪካ መዲና የሆነችው አዲስ አበባ ዕድገቷ የሚታይ እና እኛ ልንፈጥር ላሰብነው ገበያ የምትመች ናት ሲሉም ለከተማዋ ያላቸውን አድናቆት ገልፀዋል።

ወ\ሮ ዩስራ ኑር ሁሴን የዩስራ ሆም መስራች አሽሊ ፈርኒቸርን ወደ አገር ቤት ለማስገባት ሁለት ዓመት እንደወሰደባቸው ገልጸው ወደፊት ደግሞ ተጨማሪ ቅርንጫፍ ይከፈታል ብለዋል።

አጥኚዎች እንደሚናገሩት የቱሪዝም ፍሰት እና የዓለም አቀፍ ጉባኤዎችን መስተንግዶ ተከትሎ በአዲስ አበባ እና በተለያዩ የቱሪስት መዳረሻዎች የኮከብ ደረጃቸውን የጠበቁ ዘመናዊ ሆቴሎች እና የመዝናኛ ስፍራዎች ግንባታ በከፍተኛ ፍጥነት እየተበራከቱ መጥተዋል።

ይህ እያደገ የመጣው የሆቴሎች እና የሕንፃዎች ግንባታ ደግሞ ከፍተኛ ጥራት እና ዘመናዊ ዲዛይን ያላቸው የቤትና የቢሮ ዕቃዎች ፍላጎትን በከፍተኛ ደረጃ ጨምሮታል በሚለው ሁሉም አጥኚዎች የሚስማሙበት ሐቅ ነው።

የአሽሊ ፈርኒቸር ወደ ኢትዮጵያ መግባት ከሀገሪቱ የቱሪዝም እና የግንባታ ዘርፍ ጋር ያለውን ግንኙነት ያጠናክረዋል ሲሉ የዩስራ ሆም የሥራ መሪዎች ይናገራሉ።

ለአብነትም አዳዲስ ለሚገነቡ እና ነባር ለሆኑ ሆቴሎች፣ ሬስቶራንቶች እና ሎጆች ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ፣ ዘመናዊና ምቹ የፈርኒቸር ምርቶችን በሀገር ውስጥ በቀላሉ ለማቅረብ ያስችላል።

በተጨማሪም ቀደም ሲል ሆቴሎች እና አልሚዎች ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን ዕቃዎች ለማግኘት ወደ ውጭ ሀገር በመጓዝ ያወጡት የነበረውን ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እና የትራንስፖርት ወጪ በከፍተኛ ደረጃ ይቀንሳል።

የ80 ዓመታት ልምድ ያለው የአሽሊ ፈርኒቸር የንድፍ እና የጥራት ደረጃዎች ወደ ሀገር ውስጥ መግባታቸው ለሀገር ውስጥ የፈርኒቸር ባለሙያዎች የዕውቀት ሽግግር እንደሚፈጥርም በምረቃ መርሀ ግብሩ ላይ ተናግሯል።

ደንበኞች እና የሆቴል ባለሀብቶች እነዚህን ለአጠቃቀም ምቹ እና ዘመናዊ የሆኑ የአሽሊ ፈርኒቸር ምርቶችን በአዲስ አበባ ከተማ በቦሌ አትላስ በሚገኘው ሴንቸሪ ኤግዚኪውቲቭ ታወር እንዲሁም በብሥራተ ገብርኤል ኦልማርት ሱፐርማርኬት ህንፃ ላይ በሚገኙት የዩስራ ሆም ማሳያ ማዕከላ፣ አሁን ደግሞ ጉርድ ሾላ ከሚገኘው ማሳያ ማግኘት እንደሚችሉ ተጠቁሟል።

በአጠቃላይ የአሽሊ ፈርኒቸር እና የኢትዮጵያ ግንኙነት መጀመር፣ የሀገሪቱን የንግድ ኢንቨስትመንት ከማሳደጉም በላይ የቱሪዝም ዘርፉ የሚፈልገውን ዘመናዊና ማራኪ ገፅታ ለመገንባት ትልቅ አቅም ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል።

የመርሀ ግብሩ የሚድያ ይዘት ዝግጅት በተወዳጅ ሚድያና ኮምዩኒኬሽን የተሰናዳ ሲሆን ተወዳጅም ከዩስራ ሆም ጋር ህጋዊ የሥራ ውል በመፈራረም የአሽሊ ፈርኒቸርን ወደ አገር ውስጥ መግባት አስመልክቶ የመገናኛ ብዙሀንን የማስተባበር ሥራውን እንዳከናወነ ለማወቅ ተችሏል።

ምንጭ: Michael Alemayehu

Tags: Ashley FurnitureYusira Home
Previous Post

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በጁባ የቤቶች ግንባታ ለመጀመር ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታወቀ

Next Post

በውልና ማስረጃ ንብረት ገዝተው ስም ያላዞሩ ባለንብረቶች ሂደቱን እንዲያጠናቅቁ ጥሪ ቀረበ

Betegna Team

Betegna Team

Betegna - ቤተኛ, is a media platform that focuses on Ethiopian housing and real estate news, developments, technology, policies, and lifestyle.

ተዛማጅ ጽሑፎች

ሮሜል ኤሌክትሪካል አዳዲስና ዘመናዊ ምርቶቹን አስተዋወቀ
Construction Material Supply

ሮሜል ኤሌክትሪካል አዳዲስና ዘመናዊ ምርቶቹን አስተዋወቀ፤ ምርቶቹን ወደ ውጭ ገበያ ለማቅረብ እየሰራ መሆኑን ገለጸ

September 22, 2026
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሞጆ የተገነባውን ግዙፍ የሴራሚክ ፋብሪካ መረቁ
Construction Material Supply

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሞጆ የተገነባውን ግዙፍ የሴራሚክ ፋብሪካ መረቁ

May 23, 2026
የአርጆ ድንጋይ ከሰል ፋብሪካ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተመረቀ
Construction Material Supply

የአርጆ ድንጋይ ከሰል ፋብሪካ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተመረቀ

February 18, 2026
Next Post
በውልና ማስረጃ ንብረት ገዝተው ስም ያላዞሩ ባለንብረቶች ሂደቱን እንዲያጠናቅቁ ጥሪ ቀረበ

በውልና ማስረጃ ንብረት ገዝተው ስም ያላዞሩ ባለንብረቶች ሂደቱን እንዲያጠናቅቁ ጥሪ ቀረበ

  • Trending
  • Comments
  • Latest
የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የወጣ አዋጅ 721/2004

የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የወጣ አዋጅ 721/2004

April 23, 2024
ስለ ግብር የሚከፈልበት የቤት ኪራይ ገቢ

ስለ ግብር የሚከፈልበት የቤት ኪራይ ገቢ

April 6, 2024
በአዲስ አበባ የቤት ሽያጭ ዋጋ ተመን ላይ በድጋሚ ማሻሻያ ተደረገ

በአዲስ አበባ የቤት ሽያጭ ዋጋ ተመን ላይ በድጋሚ ማሻሻያ ተደረገ

April 3, 2024
የመሬት ልማትና አስተዳር ደንብ ቁጥር 163/2016

የመሬት ልማትና አስተዳር ደንብ ቁጥር 163/2016

April 22, 2024
ስለ ሪል እስቴት ምን ያውቃሉ?

ስለ ሪል እስቴት ምን ያውቃሉ?

August 18, 2023
Home pic

ቤት ለሚገዙ እና ለሚሸጡ አካላት ማሳሰቢያ ተሰጠ

0
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤት አቅርቦትን ለማሳደግ የሚያስችል ውይይት ከሪል እስቴት አልሚዎች ጋር ውይይት አደረገ!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤት አቅርቦትን ለማሳደግ የሚያስችል ውይይት ከሪል እስቴት አልሚዎች ጋር ውይይት አደረገ!

0
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ያስተዋወቀበትን የገርጂ መኖሪያ መንደር ፕሮጀክት ሊያስመርቅ ነው

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ያስተዋወቀበትን የገርጂ መኖሪያ መንደር ፕሮጀክት ሊያስመርቅ ነው

0
ባለ 9 ወለል ህንፃ በተጀመረ በ69ኛ ቀኑ ተጠናቀቀ!!

ባለ 9 ወለል ህንፃ በተጀመረ በ69ኛ ቀኑ ተጠናቀቀ!!

0
ስለ ሪል እስቴት ምን ያውቃሉ?

ስለ ሪል እስቴት ምን ያውቃሉ?

0
የሪል እስቴት አልሚዎች ማህበር የ7% የብድር ወለድ ጥያቄ በባለሙያዎች መካከል ያስነሳው ክርክር

የሪል እስቴት አልሚዎች ማህበር የ7% የብድር ወለድ ጥያቄ በባለሙያዎች መካከል ያስነሳው ክርክር

November 18, 2026
በጋዜቦ አደባባይ አካባቢ በግንባታ ሂደት ላይ ከነበረ ሕንጻ ላይ የወደቁ ሦስት ሠራተኞች ሕይወታቸውን አጡ

በጋዜቦ አደባባይ አካባቢ በግንባታ ሂደት ላይ ከነበረ ሕንጻ ላይ የወደቁ ሦስት ሠራተኞች ሕይወታቸውን አጡ

November 14, 2026
በ5 ዓመታት ቤቶችን ገንብተን ለማስረከብ የገባነውን ቃል በተግባር ለማረጋገጥ እየተጋን ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

በ5 ዓመታት ቤቶችን ገንብተን ለማስረከብ የገባነውን ቃል በተግባር ለማረጋገጥ እየተጋን ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

November 13, 2026
የ1.5 ሚሊዮን መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት ወደ ተግባር ምዕራፍ ተሸጋግሯል

የ1.5 ሚሊዮን መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት ወደ ተግባር ምዕራፍ ተሸጋግሯል

November 12, 2026
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከዩኤን ሃቢታት ዋና ዳይሬክተር አናክላውዲያ ሮስባክ ጋር መወያየታቸውን ገለፁ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከዩኤን ሃቢታት ዋና ዳይሬክተር አናክላውዲያ ሮስባክ ጋር መወያየታቸውን ገለፁ

November 11, 2026

ብዙ የተነበቡ

  • የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የወጣ አዋጅ 721/2004

    የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የወጣ አዋጅ 721/2004

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ስለ ግብር የሚከፈልበት የቤት ኪራይ ገቢ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአዲስ አበባ የቤት ሽያጭ ዋጋ ተመን ላይ በድጋሚ ማሻሻያ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የመሬት ልማትና አስተዳር ደንብ ቁጥር 163/2016

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ስለ ሪል እስቴት ምን ያውቃሉ?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Categories

  • Community & CSR (28)
  • Construction & Projects (29)
  • Construction Material Supply (9)
  • Design & Innovation (18)
    • Architecture (2)
    • Technology (14)
  • Global (4)
  • Insights & Profiles (20)
  • Legal Updates (89)
    • Community Complaints (8)
    • Corruption (ሙስና) (2)
    • Directives (መመሪያዎች) (1)
    • Proclamations (አዋጅ) (7)
    • Regulations (ደንብ) (2)
  • Mortgages & Finance (14)
  • Property Handover (16)
  • Public Housing (71)
  • Real Estate Guides (13)
    • Buying Guide (3)
    • Knowledge Base (1)
    • Renting Guide (2)
    • Selling Guide (7)
  • Sales & Marketing (67)
  • Tenders & Bids (60)
    • Land Lease (29)
    • Request for EOI (1)
  • Home
  • Guides
  • Mortgage
  • Highlights
  • Legal Updates
  • Tenders & Bids
Betegna Logo Footer

Betegna – ቤተኛ, powered by Betbegara.com, is a media platform that focuses on Ethiopian housing and real estate news, developments, technology, policies, and lifestyle.

© 2026 Betegna – ቤተኛ | Ethiopian Housing and Real Estate News & Insights

  • Home
  • Guides
    • Buying Guide
    • Renting Guide
    • Selling Guide
    • Knowledge Base
  • Mortgage
  • Technology
  • Legal
    • Proclamations (አዋጅ)
    • Regulations (ደንብ)
    • Directives (መመሪያዎች)
    • Community Complaints
    • Corruption (ሙስና)
  • Tender
    • Auction (ሐራጅ)
    • Land Lease (የመሬት ሊዝ)
    • Request for EOI
  • Project Highlight
  • More
    • Community & CSR
    • Construction & Projects
    • Construction Material Supply
    • Design & Innovation
    • Public Housing
    • Insights & Profiles
    • Sales & Marketing
    • Property Handover
    • Global
    • Contact Us
No Result
View All Result
Sell, Buy, Rent