ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ስብሰባ የቤት ግንባታን በሚመለከት ያነሱት ሃሳብ።
እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የቤት ባለቤት እንዲሆን ማሰብ፣ መሻት፣ መስራት ብዙ የሚቻል ጉዳይ አይመስለኝም፤ አሜሪካም እንደዛ አይቻልም፣የለም።
የሚቻለው ጉዳይ እያንዳኑ ሰው ቢያንስ በአቅሙ ለመከራየት ቢፈልግ የቤት አማራጭ እንዲያገኝ ማድረግ እንጂ ሁሉም ሰው 500 ካሬ ሜትር እየተከፋፈለ ቤት እንዲሰራ ማድረግ አይደለም።
ዋናው አላማ ቢያንስ የፓርላማ አባላት ወይም ሌላ ሰው ከቦታ ቦታ ሲንቀሳቀስ በኪራይ ቤት ሲፈልግ ማጣት እንዳይችል ማስቻል ነው።
ይሄ ችግር ነው አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ በኪራይም ቤት አይገኝም ከተገኘም ያው እንዳላችሁት ውድ ነው።
ይሄንን ችግር መፍታት በዘላቂነት የኑሮ ውድነት እና cost of living እያመጣ ያለውን ጫና ለመቀነስ ያግዛል። እኛ ዘንድሮ 1.5 ሚልዮን unit በሚቀጥለው 6 ዓመታት እንገነባለን ብለን ስናቅድ ስራው አሁን አልተጀመረም።
ቅድም እንዳነሳችሁት ብረት በሀገር ውስጥ ለማምረት ከኦሩ(Ore) በስተቀር ሰፊ ስራ ሲሰራ ቆይቷል። አሁን scrap ካገኘን ወይም ore ካገኘን የኢትዮጵያን ፍላጎት ለማሟላት የሚያስችሉ ፋክትሪዎች(factories) ኢትዮጵያ ውስጥ አሉ።
ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ፋብሪካዎች የኢትዮጵያን ብረት አቅልጠው ለኢትዮጵያ ፍላጎት ለማዋል ብቃት አላቸው። ችግሩ ዋናው ኦሩን መስራት ነው። እሱም የጀመርናቸው ጉዳዮች አሉ።
ሲሚንቶ በከፍተኛ ደረጃ ለማሻሻል የተሰራው ስራ ይታወቃል፤ ለሚ ላይ። አሁንም እያስፋፋን እንገኛለን።
መስታወት እናንተም እንዳያችሁት ነው። በዚህ አመት ይመረቃል። የኢትዮጵያን ፍላጎት ከሞላ ጎደል የሚሸፍን የመስታወት ፋብሪካ ከኦር ጀምሮ፣ ከአፈሩ ጀምሮ የሚሰራ በግል ባለሀብት እየተሰራ ይገኛል። እሱም ለዚህ ለቤት ግንባታ ትልቅ ግብዓት ይሆናል።
ግራናይት፣ ማርብል ላይ፣ የእንጨት ስራ ላይ፣ ሶፋ ስራዎች ላይ፣ በር ላይ ሰፋፊ ስራዎች እና ዝግጅት ሲደረግ ቆይቷል።
ከዚህ በተጨማሪ ቴክኖሎጂ ላይ፣ ፍብሪካዎች አሉ ቤት የሚሰሩ። አሁን በቅርቡ አራት አምስት ቤቶች ሳምፕል(Sample) አዲስ አበባ ላይ ይሰራሉ። የተከበረው ምክር ቤት ስራው ሲያልቅ እንዲያይ ይደረጋል። G+3 በፋብሪካ የሚመረተው ቤት በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ፣ ከአንድ ወር ባነሰ ጊዜ ውስጥ ያልቃል። ፋብሪካ ይመራታል፤ ይገጣጠማል ማለት ነው። እና ፋብሪካዎች እያስገባን እንገኛለን።
እንደዚህ አይነት ሰፋፊ ዝግጅት ስናደርግ ቆይተናል። አዋጅ ወይም wish አይደለም ያስቀመጥነው። ስንዘጋጅ ቆይተን፣ ያለው ዝግጅት ስራ ለመጀመር የሚያስችል ነው ብለን ስናስብ ነው ለህዝባችን ያበሰርነው።
ይሄ 1.5 ሚልዮን unit እያንዳንዱ unit በጣም በረከሰ መንገድ 2 ሚሊዮን ብር ፈጀ ብለን ብናስብ በድምሩ ከ 3 ትሪሊዮን ብር በላይ ሀብት ይፈስበታል። 3 ትሪሊዮን ማለት አሁን ኢትዮጵያ ባላት GDP፣ 20% ማለት ነው። በጣም ትልቅ ስራ ነው።


















