በቤቶቹ ማስተላለፍ በስነ-ስርዓት ላይ የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ የመከላከያ ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር)፣ የመከላከያ ከፍተኛ አመራሮችና አባላት ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስትር ዶክተር አብረሃም በላይ ባስተላልፉት መልእክት ከዚህ በፊት ተመዝግበውና ቆጥበው መመዘኛውን አሟልተው ለተገኙ የሠራዊት አባላትና ስቪል ሠራተኞች በሶስት ዙር 1,236 ቤቶች በእጣ እንደተላለፉ፣ እንዲሁም በዛሬው ቀን (ግንቦት 03 ቀን 2016 ዓ.ም) በአራተኛው ዙር ደግሞ 1,336 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን በእጣ መተላፋቸውን ገልፀዋል።

ሚኒስቴሩ አክለውም “ይህ ስራ ጀመርነው እንጂ አሰራራችን በማዘመን፣ አፈፃፀማችን በማሻሻል፣ አማራጮች በማስፋት የመላ የሰራዊታችን የቤት ፍላጎት ለማሟላት ገና ብዙ መንገድ እንደሚቀረንም እንገነዘባለን። ይህንን እንድናሳካ ሁሉም ባለድርሻ ኣካላት ከጎናችን እንደሚሆኑና አስፈላጊ ድጋፍ እንደሚያደርጉልንም አንጠራጠርም።” በማለት የእድሉ ተጠቃሚዎችንም የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት አስተላፈዋል።
ቤቶቹ በመከላከያ ኢንጂነሪንግ እና ኦቪድ ኮንስትራክሽን አማካኝነት በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ተገንብተው የተጠናቀቁ መሆናቸው ተገልጿል።
በኮዬ ፈጬ ክ/ከ በ16 ሄክታር ላይ በመከላከያ ኢንጂነሪንግ እና ኦቪድ ኮንስትራክሽን አማካኝነት የተሠራው አንደኛው ፕሮጄክት 7 ህንፃዎች ያሉት ሲሆን አራት ሕንፃዎች ባለ G+7 ወለል፣ ሦስት ሕንፃዎች ደግሞ ባለ G+9 ወለል ሲሆኑ በውስጡ 248 ቤቶችን ይዟል።
የቤት ባለዕድለኞች ስም ዝርዝር በPDF ተያይዟል።

















