የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ቀደም ሲል በ20/80 እና 40/60 ተመዝግበው የነበሩ የቤት ቆጣቢዎችን በ70/30 ማህበር ቤት ተደራጅተው ቤት መገንባት እንዲችሉ ጥሪ አድርጎ ኦንላይን ተመዝግባችሁ የነበረ እና መረጃ እንድታሟሉ ጥሪ በተደረገበት ወቅት ባለመስማት ያለፋችሁ ተመዝጋቢዎች፣
በተደጋጋሚ ለቢሮ ጥያቄ ባቀረባችሁት መሰረት እንድትመዘገቡ የተፈደ በመሆኑ ለመጨረሻ ጊዜ ሚያዝያ 28/08/2017 ጀምሮ ለተከታታይ ሰባት የስራ ቀናት ብቻ በአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ የጋራ መኖሪያ እና ቤት ማህበራት ክትትል ዳይሬክቶሬት 6ኛ ፎቅ በአካል የቤት ቁጠባ ደብተራችሁን ይዛችሁ በመቅረብ እንድትመዘገቡ እናሳውቃለን፡፡
ምንጭ፡ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ


















