ሀገራችን የከተማና የመሰረተ ልማት ዘርፍ የ2025 -2050 የኮንስትራክሽን ኢኒሼቲቭ ትራንስፎርሜሽን በሚል መርህ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪውን ወደ ተሻለና ዘመናዊ አሰራር ከፍ ለማድረግ እየተከተለች ያለውን ስራ በማገዝ ረገድ ብቁና ውጤታማ ዜጎችን ለማፍራት መሠራት ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል።
የተቋሙን አጠቃላይ እንቅስቃሴ እንዲሁም የስልጠና ሂደቱን በተመለከተ በዛሬው ዕለት ጥቅምት 8 ቀን 2018 ዓ.ም በካሶፒያ ሆቴል ለመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የተቋሙ ዋና ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ፍሬዘር ተሾመ ገልፀዋል።
ሪቪዚት ኢንስቲቱሽን ኦፍ ዲዛይን አ.ማ በአሁን ስዓት በልዩነት እጅግ ወቅታዊ የሆኑ ሶፍትዌሮችን ለማሰልጠን ዝግጅቱን ያማጠናቀቁን ገልጸዋል።
ስልጠናው በዋናነት በቢም (ቢውልዲንግ ኢንፎርሜሽን ሞዴሊንግ)፣ በኢንቴርይር ዲዛይን፣ በአርክቴክቸራል ዲዛይን ሶፍትዌር፣ በሲቭል ኢንጅነሪንግ ዲዛይን ሶፍትዌር እንዲሁም በኤ አይ እና በግራፊክ ዲዛይን መስኮች በሙያው በሰለጠኑና ከፍተኛ ልምድ ባላቸው አሰልጣኞች እና ባለሙያዎች ለማሰልጠን ዝግጅቱን አጠናቆ ወደ ስራ መግባቱ በመግለጫው ላይ ተነግሯል።
ምንጭ፡ FastMereja

















