• BetBegara.com
  • Buy
  • Rent
  • Sale
  • Services
  • Contact Us
Betegna - ቤተኛ | Ethiopian Housing and Real Estate News & Insights
Advertisement
  • Home
  • Guides
    • Buying Guide
    • Renting Guide
    • Selling Guide
    • Knowledge Base
  • Mortgage
  • Technology
  • Legal
    • Proclamations (አዋጅ)
    • Regulations (ደንብ)
    • Directives (መመሪያዎች)
    • Community Complaints
    • Corruption (ሙስና)
  • Tender
    • Auction (ሐራጅ)
    • Land Lease (የመሬት ሊዝ)
    • Request for EOI
  • Project Highlight
  • More
    • Community & CSR
    • Construction & Projects
    • Construction Material Supply
    • Design & Innovation
    • Public Housing
    • Insights & Profiles
    • Sales & Marketing
    • Property Handover
    • Global
    • Contact Us
No Result
View All Result
Sell, Buy, Rent
  • Home
  • Guides
    • Buying Guide
    • Renting Guide
    • Selling Guide
    • Knowledge Base
  • Mortgage
  • Technology
  • Legal
    • Proclamations (አዋጅ)
    • Regulations (ደንብ)
    • Directives (መመሪያዎች)
    • Community Complaints
    • Corruption (ሙስና)
  • Tender
    • Auction (ሐራጅ)
    • Land Lease (የመሬት ሊዝ)
    • Request for EOI
  • Project Highlight
  • More
    • Community & CSR
    • Construction & Projects
    • Construction Material Supply
    • Design & Innovation
    • Public Housing
    • Insights & Profiles
    • Sales & Marketing
    • Property Handover
    • Global
    • Contact Us
No Result
View All Result
Betegna - ቤተኛ | Ethiopian Housing and Real Estate News & Insights
No Result
View All Result
“አዲስ አበባ ውስጥ መሬት የለንም የሚባለውን ነገር አልስማማበትም” – ደሳለኝ ከበደ (ኢንጂነር)

“አዲስ አበባ ውስጥ መሬት የለንም የሚባለውን ነገር አልስማማበትም” – ደሳለኝ ከበደ (ኢንጂነር)

Betegna Team by Betegna Team
January 31, 2024
in Insights & Profiles
A A
0
0
SHARES
Share on FacebookShare on LinkedIn

በወንደሰን መኮንን

ደሳለኝ ከበደ(ኢንጂነር) ተወልደው ያደረጉት አዲስ አበባ ጣሊያን ሠፈር ነው፡፡ የመጀመሪያ ትምህርታቸውን ቀይ ኮኮብ ወይንም አጋፋሪ የሚባል ትምህርት ቤት፣ መካከለኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአርበኞች ትምህርት ቤት ተከታትለዋል፡፡ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን መድሀኒአለም ት/ቤት ጨርሰዋል፡፡ በመቀጠል አምስት ኪሎ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቴክኒዮሎጂ ፋካሊቲ በሲቪል ኢንጂነሪንግ በ1990 ዓ/ም በማእረግ ተመርቀዋል፡፡ ከአራት አመት በኃላ የማስተርስ ዲግሪያቸውን በስትራክቸራል ኢንጂሪነግ ጨርሰዋል፡፡ በአለም አቀፍ ቢዝነስ ኤምቢኤ ከግሪን ዊች ዩንቨርሲቲ የማስተርስ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል፡፡ በሪል እስቴት አማካሪነት በርካታ አመታት ሰርተዋል፡፡ በቅርቡም ስለ ሪል እስቴት በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነውን መጽሀፍ ጽፈው አስመርቀዋል፡፡ በሪል እስቴት ዘርፍ አጫጭር ስልጠና የሚሰጥ ትምህርት ቤትም ከፍተዋል፡፡ ሪል እስቴት ምንድነው በሀገራችን መቼ ተጀመረ ? የሕብረተሰቡን የቤት ችግርስ እንዴት መፍታት ይችላል ? በሚሉት ነጥቦች ዙሪያ ከአዲስ ዘመን ጋር ቆይታ አድርገዋል፡፡ ይከታተሉት፡፡

አዲስ ዘመን፦ ከዩኒቨርሲቲ ከጨረሱ በኋላ መጀመሪያ ስራ የት ጀመሩ ?

ኢንጂነር ደሳለኝ፦ ልክ እንደተመረቅን ከአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ በውጤታችን ተመርጠን ወደ ኢትዮጵያ ቴሌኮሚኒኬሽን ተመደብን። ቴሌኮሚኒኬሽን የሲቪል ኮንስትራክሽን የሚባል ዲፓርትመንት ነበረው። እዛ ውስጥ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን በመሐንዲስነት ሰርቻለሁ። ቀጥዬ ወደ ትምህርት ነው የገባሁት ። እየተማርኩ በተለያዩ ዩንቨርስቲዎች አስተምሪያለሁ ። ክሳማ ዩኒቨርስቲ ፤ አዲስ ኮሌጅ ፤ ዩኒቲ ዩኒቨርስቲ፤ ለስራ በሄድኩበት ግዜ ድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ጨምሮ እስከ 2004ዓ/ም ድረስ አስተምሬአለሁ። መደበኛ ስራዬ ስትራክቸራል ዲዛይን (የመዋቅር ጥናት) መስራት ነው ። በትርፍ ጊዜዬ በኢስት አፍሪካ ሪል እስቴት በዲዛይንና ግንባታ ስራ አማካሪነት እና በሪል እስቴት ሥራ አስኪያጅነትም ሰርቻለሁ ።

አዲስ ዘመን፦ ከቴሌ ውጭ መንግሥት መስሪያ ቤት አልሰሩም ?

ኢንጂነር ደሳለኝ፦ መንግሥት መሥሪያ ቤት ከቴሌ በኋላ ሰርቼ አላውቅም።

አዲስ ዘመን፦ በቅርቡ ለሀገራችን በዘርፉ የመጀመሪያ የሆነውን መጽሀፍ አሳትመዋል። መጽሀፉን ለመጻፍ ምን አነሳሳዎት? በሀገራችንስ ሪል እስቴት እንዴት ተጀመረ ?

ኢንጂነር ደሳለኝ፦ ይሄን መጽሀፍ ለመጻፍ ዋነኛው ምክንያት የሆነኝ ችግር ነው ። እንደ ሲቪል መሐንዲስም ሆነ እንደ ስትራክቸራል መሐንዲስ በሪል እስቴት ሥራ ላይ ከ15 አመት የበለጠ ሰርቻለሁ። በሪል እስቴት ስራ ውስጥ ሥራ አስኪያጅ ሆኜ እንድሰራ የተጠየኩት መሐንዲስ ስለሆንኩ ነበር። ባለሀብቶች ሪል እስቴትን የሚያገናኙት ከግንባታ ጋር ነው። ሪል እስቴት ግን ከግንባታ ጋራ ብቻ የሚገናኝ አይደለም። ከብዙ ሙያዎች ከብዙ ስራዎች ጋር ይገናኛል። የቢዝነስ፤ የማኔጅመንት፤ የማርኬቲንግ፤ ፋይናንስ ፣ የንብረት አስተዳደር የፕሮጀክት ማኔጅመንት ፣ የሕግ ፣ የዲዛይን ሌሎችም ክፍል አሉት ። መስኩ እነዚህን ሁሉ ያቀፈ እንደሆነ ተረድቻለሁ። የምሰራውን ስራ በተግባር የሚጠበቅብኝን አገልግሎት ለመስጠት የሚያስፈልገኝን እውቀቱን ማሟላት ነበረብኝ። ይሄን እውቀት ለማሟላት ማንበብ መጠየቅ መማር ነበረብኝ።

የሚገርመው ነገር በአማርኛ ሆነ በእንግሊዝኛ የተጻፈ የሪል እስቴት መጽሀፍ ገበያ ላይ የለም። የተጻፉ ጥናቶችን ብዙ ሰው አያነባቸውም ። የነበረኝ አማራጭ አሮጌ የመጽሐፍት ተራ ሄዶ መጽሀፍቶችን ማፈላለግ ነበር። እኔም ሆንኩ ሌላ ሰው ወደ ውጪ ሲሄድ ሪል እስቴትን በተመለከተ የተጻፉ መጽሀፍቶችን አስመጣ ነበር።

በሀገራችን የሪል እስቴት ችግሮችን ክፍተት ሊሞሉ የሚችሉ መጽሀፍትን አሰባስብ ነበር ። በተግባር ስራው ላይ እየቆየሁ ስሄድ ብዙ ችግሮችን እያስተዋልኩ እያየሁ መጣሁ። ችግሮቹ ሁላችንም የምናያቸው የምንሰማቸው ናቸው። በዚህም ምክንያት መጽሐፉን ጽፌ ሌሎች በዘርፉ ብዙ ልምድና እውቀቱ ያላቸው እንዲጽፉ ለማበረታታት ለዘርፉ የመጀመሪያ የሆነውን መጽሐፍ ለመጻፍ ችያለሁ።

አዲስ ዘመን፦ በሪል እስቴት ዘርፍ በሕብረተሰቡ ውስጥ የሚነሱ በርካታ ችግሮች አሉ። እርስዎ ምን ምን ችግሮች አስተዋሉ?

ኢንጂነር ደሳለኝ፦ ሪል እስቴትን በተመለከተ ችግሩ ይሄ ነው ብሎ ለመናገርም ሆነ በመጀመሪያ ደረጃ ትክክል ነው ወይስ አይደለም ለማለት መስፈርቶች ያስፈልጋሉ ። እነዛ መስፈርቶች በእኛ ሀገር የሉም። ኢንቨስተር የሆነ ሰው ችግር ደርሶበት ወይ ከስሮ እናገኛለን። ወይ ደግሞ የተቋቋመ ሪል እስቴት ተግባራዊ ማድረግ አቅቶት ሲቆም አሊያም ገዢዎች ሲንገላቱ እናያለን። እነዚህ በአይናችን የምናያቸውና ሁሌ የምንሰማቸው ችግሮች ናቸው። መጽሀፉን ለመጻፍ ዋና ምክንያት የሆነኝ ራሴ ስራው ላይ ሆኜ ስሰራ የነበሩብኝ ክፍተቶች እንጂ በዚህ ጉዳይ ዙሪያ እከሌ ትክክል ነው እከሌ ትክክል አይደለም ለማለት አልችልም።

አዲስ ዘመን፦ በስራው ላይ ያዩት ያጋጠመዎት ችግር ምንድነው ?

ኢንጂነር ደሳለኝ፦ ዘርፉን ለመመዘን አንደኛ የእውቀት ክፍተት አለ ። ይሄን መጽሀፍ ለመጻፍ ባደረኩት ጥረት ባገኘኋቸው ጽሁፎች እንደተረዳሁት የእኛ ሀገር ሪል እስቴት ኢንቨስትመንት አሰራራችን በትክክል እየተመራ ነው ብዬ አላምንም። ምክንያቱም የተለያዩ ባለሙያዎችን አሳትፎ አይደለም እየተሰራ ያለው።

አዲስ ዘመን ፦በሀገራችን የሪል እስቴት ቢዝነስ እንዴት ተጀመረ?

ኢንጂነር ደሳለኝ፦ ኢትዮጵያ ውስጥ ሪል እስቴት እንዴት ተጀመረ የሚለውን ለማየት መጀመሪያ ሪል እስቴት ከሚለው ትርጉሙ መነሳት ያስፈልጋል ። ሪል እስቴት መሬትና ከመሬት ጋር የተያያዙ ጉዳዮች ጋር የተያያዘ በመሆኑ የሰው ልጅ በአንድ ቦታ ተወስኖ ሰፍሮ መኖር ከጀመረበትና የመሬት ባለቤትነት በነገሥታት መያዝ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ እንደተጀመረ ነው ማሰብ ይቻላል ። ሀገራችን ኢትዮጵያ ቀደምት ከሚባሉት ሀገራት ውስጥ የምትቆጠር በመሆኗ ሪል እስቴት ከብዙዎቹ ቀድማ የጀመረች ናት። እንደ ንግድ ዘርፍ ተቆጥሮ መስራት የተጀመረበትን ጊዜ ከሆነ ግን ከሁለት አስርት አመታት ብዙም የማይርቅ ሆኖ እናገኘዋለን።

በፊውዳል ስርዓት መሬት የመሬት ከበርቴዎችና የንጉሡ ነው። ንጉሡ ለሚቀርቡት ባለሟሎቹ እየሰጠ እያስተዳደረ ከመሬት ከሚገኘው ገቢ ግብር ይሰበስባል። ገቢ ከሌላቸው ላይ ደግሞ ጉልበት ይሰበስባል። ጭሰኝነት ማለት ነው። ያገለግላሉ። ያ እንደ ክፍያ ነው የሚወሰደው።

አዲስ ዘመን ፦ሪል እስቴት በፊውዳሊዝም ስርዓተ ማሕበር ተመስርቶ በካፒታሊዝም ስርዓት ውስጥ ካፒታሊስቱ መሬትን እንደ ትልቅ ሀብት አድርጎ ስለሚሸጠውና ስለሚለውጠው በዘመናዊነት አደገ ማለት ይቻላል ? መሬት ራሱን የቻለ የማይነቃነቅ ካፒታል ስለሆነ ማለቴ ነው።

ኢንጂነር ደሳለኝ፦ የሪል እስቴት ቃሉ ራሱ የመጣው ሮያል ከሚለው ቃል ነው ፤ይህም ባለቤቶቹ ነገሥታት መሆናቸውን የሚያመለክት ነው። እውነተኛ (ሪል) ቋሚ ንብረት ማለት ነው የሚሉም አሉ። እንደ ንግድ ዘርፍ እየሆነ የመጣው ከፊውዳሊዝም በኋላ ከተሞች መመስረት ሲጀምሩ በፊውዳሉ ስርአት የተሻለ ነገር ማግኘት ይችሉ የነበሩ ሰዎች አሁንም የተሻለ ነገር እያገኙ ሄዱ። ፍላጎታቸው እየጨመረ ቤት እየሰሩ የሚሸጡበት የገበያ ቦታዎች ለምሳሌ፡- አርብ ገበያ፤ ሐሙስ ገበያ፤ ሰኞ ገበያ ፤ቅዳሜ ገበያ እያሉ እየከፈቱ እያስፋፉ ሄዱ። እዛ አካባቢ ያሉት ንግድ ቤቶችና ቤቶች ናቸው ለትናንሽ ከተሞች መቆርቆር በሂደትም መስፋት ምክንያት የሆኑት።

የከተሞች መቆርቆርና የሕዝብ በአንድ ቦታ ተሰባስቦ መኖር መጀመር ቤት መገንባት ማከራየት መሸጥ እንዲኖር አድርጎአል፤ አስችሎአል። ሪል እስቴት በዚህ ግዜ ተጀመረ ብሎ ለመደምደም ከባድ ነው።

የጭቃም ቤት ሰርቶ የሚኖር ሰው ለራሱ የሪል እስቴት አልሚ ነው። ሪል እስቴት በትርጉሙ ካየነው ይዞታ እንደማለት ነው። ቋሚ ንብረት ነው። የራስ ባለቤትነት ነው። አሁን ለምሳሌ አንድ የሆነ ቦታ ያለው ሰው ግቢው ውስጥ ዛፍ አለ እንበል። የሪል ስቴቱ ንብረት ነው። የራሱ ነው። ከቋሚ ንብረቶች አንዱ ሪል እስቴት ነው።

የኢንዱስትሪ አብዮትን ተከትሎ የሰው ልጅ በተለያዩ መሳሪያዎች በመታገዝ ከጉልበት ስራ በመላቀቅ ዕውቀት መገብየትና የተሻለ ኑሮን መፈለግ ፣ መብቶችንም መጠየቅ እየጀመረ መሄዱ፣ የተለያዩ የፖለቲካ አመለካከቶች እየተስፋፉ መምጣታቸው ከፊውዳል ስርዓት ወደ ካፒታሊዝም መሸጋገር ምክንያት ከሆኑት ውስጥ አንዱ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል። ነገር ግን መሬት ከምድራችን ከ30% በታች የሆነውን የሚሸፍንና አብዛኛው ክፍሉም ለመኖር የሚመች በመሆኑ እንደ አዲስ የሚመረት ቁስም ስላልሆነ በየትኛውም ስርዓት ቢሆን እየተወደደ መሄዱ የሚጠበቅ ነው ።

አዲስ ዘመን፦ አሁን ከምናየው ሰፋፊ የሪል እስቴት ስራዎች አንጻር በደርግ ግዜ ሪል እስቴት ነበር ?

ኢንጂነር ደሳለኝ፦ ነበረ እንጂ ። የማሕበር ቤቶች ነበሩ። ሪል ስቴቶች ናቸው። የአገነባብ ስርዓቱ ነው እንጂ ከየዘመኑ ጋር እየተለያየ የሚሄደው በፊውዳሊዝም ግዜም ቤት ይሰራ ነበር። ሪል እስቴት ነው። ፋብሪካዎች ይገነባሉ። የሻይ ቅጠል እርሻዎች አሉ። ለምሳሌ ውሽውሽ የሻይ ቅጠል እርሻ ሪል እስቴት ነው። ኢንደስትሪ ፓርክ ቻይኖች የሰሩት ሪል እስቴት ነው። መንግሥት በየቦታው የሰራቸው ያለማቸው ኢንደስትሪ ፓርኮች ሪል ስቴቶች ናቸው። ኮንዶሚኒየም ቤት ግንባታዎች ሪል ስቴቶች ናቸው። መሬትና መሬት ላይ የሚሰራ ቋሚ ንብረት ያለበት ሪል እስቴት ነው።

አዲስ ዘመን፦ ለመኖሪያ ተብለው በብዛት ፎቆች ሰርተው የሚሸጡትን ሪል ስቴቶች በተመለከተ ችግር እንዳለ ሕዝቡ ይናገራል። ክስ ላይ ያሉም አሉ።እርስዎ ስራው ላይ ብዙ ስለቆዩ ያዩዋቸውን ችግሮች ቢገልጹልን ?

ኢንጂነር ደሳለኝ፡- በመሰረታዊነት የተፈጠረውን ችግር እኔ የማያይዝው ተገቢ የሆነ የቤቶች የግብይት ስርዓት ካለመኖሩ ጋር ነው። የሪል እስቴት አልሚ ባለሀብቶች አስበውበት ይህንን ችግር ፈጥረዋል ብዬ አላምንም። ምክንያቱም እነሱ ነጋዴዎች ናቸው። የቤት እጥረት እንዳለ ያውቃሉ። እጥረት ደግሞ የኢንቨስትመንት አንዱ አጓጊ ጉዳይ ነው። ችግሩ የሚፈጠረው ለምንድነው ብትለኝ ወደስራው የገቡት ባለሀብቶች አስቀድሞ በሕግና በደንብ ያልታገዘ የግብይት መመሪያ ያልወጣበት ዘርፍ ውስጥ ቀድመው መግባታቸው ነው ።

አዲስ ዘመን ፦ ባለሀብቶቹ ያለእውቀት ያለልምድ ያለበቂ ዝግጅትና ፋይናንስ ምን አይተው ገቡ ?

ኢንጂነር ደሳለኝ፦ ሀሳብና ገንዘብ ይዘው የገቡት የቤት እጥረት ስላለ ነው። እውቀት አላቸው። እውቀታቸው የንግድ እውቀት ነው። የንግድ እውቀታቸውን ይዘው ገቡ። መንግሥት ያለውን መሬት በሊዝ ለሽያጭ አቀረበ። ገዙ፣ አለሙ፣ ሸጡ። መንግስት የቤት ችግር እንዲቀረፍ በተለያዩ አግባቦች ለዘርፉ ተዋንያን መሬት ቢያቀርብም ከዚያ በኋላ ግን ግብይቱ የሚመራበትን መመሪያ ሳያወጣ ቆይቷል።

አዲስ ዘመን፦ ይሄን የሪል እስቴት ዘርፍ የሚመራው መንግስታዊ ተቋም ማነው ?

ኢንጂነር ደሳለኝ፡- እስከማውቀው ድረስ ልክ እንደ ሌሎች ኢንቨስትመንቶች እንጂ የሚታየው ለብቻው የሪል እስቴት ዘርፍን መንግሥት የሚመራበት ጸድቆ የወጣ መመሪያ ወይም የተለየ አካል የለም። እየተመራ ያለው ለተለያዩ ዘርፎች በተዘጋጁ የተለያዩ ሕጎች ነው። አሁን ለምሳሌ ግንባታ ሲገነባ በግንባታ ሕጎች ይመራል። ሲሸጥ ንብረት መሸጥ በሚለው ይገበያያል። በነጋዴውና በገዢው መካከል የሚያገናኝ፤ ግብይቱን የሚመራ ከሚዋዋሉት ውል ውጪ ይሄ ነው የሚባል ምንም ነገር የለም።

አዲስ ዘመን፦ እንዴት ነው የማይገናኘው ?

ኢንጂነር ደሳለኝ፡- በምሳሌ እንየው። ሰው እየተገነባ ያለ ቤት ሲገዛ ያለዋስትና ነው ገንዘብ የሚከፍለው። ዋስትናው ደረሰኙና ውሉ ነው። እያንዳንዱ የሚገዛ ሰው ቤት ለመግዛት ሲፈልግ የሕግ አማካሪ አማክሮ አይደለም ገንዘቡን የሚከፍለው።አልሚ ድርጅቶች የሰጡትን ውል ነው የሚፈርመውም ሆነ የሚጠቀመው።

በዚህ ሰዓት ማን ተጠቃሚ ይሆናል፤ ማን ተጎጂ ይሆናል የሚለውን የሚወስነው በግብይቱ መሀል የሚኖረው አካሄድ ነው። በቀላሉ አንድ የመሬት ይዞታ ያለው ሪል እስቴት አልሚ ቤቶች ገነባ እንበል። ቤቱን በግንባታ ሂደት ሸጠ። አብሮ ካርታ እስካልሰጠ ድረስ ባለሀብቱ ሊበደርበት ይችላል። ምንም የሚያግደው ነገር የለም። እዳው ካልተከፈለ ይሄ ንብረት የአበዳሪው አካል ነው ማለት ነው ።

አዲስ ዘመን፦ የሪል እስቴት ቤት የሚገዙ ሰዎች የባለቤትነት ካርታ አይሰጣቸውም ?

ኢንጂነር ደሳለኝ፦ ትክክለኛው ግብይት ተጠናቀቀ የሚባለው ካርታቸውን ወስደው ሪል እስቴት አልሚው አልምቶ ሲወጣ ነው። ይሄን አድርገው ካርታ አውጥተው የሚያስረክቡ ብዙዎች አሉ። ለደንበኞቻቸው ካርታ ለማውጣት ጊዜ ወስዶባቸው ግብይታቸውን በአግባቡ ያላጠናቀቁም በርካቶች ናቸው። እንደ ሪል እስቴት ልማት በርካታ ቤቶችን ገንብተው በሚያስረክቡበት ወቅት ገዥዎች ተደራጅተው የጋራ መጠቀሚያቸውን ስለማያስከብሩ አንዳንድ አልሚዎች ገንብተው ከጨረሱ በኋላ ለነዋሪዎቹ በተወሰነው የጋራ መጠቀሚያ ቦታ ላይ ሲገነቡበት ይታያል። ይሰማል። ግሪን ኤርያው ወይ ማስታወቂያ ላይ የነበረ ነው። ይሄን የሚያግድ የሚከለክል ሕግ የለም። በምን ያግደዋል ። እኔ አሁን አንድ ሁለት መኝታ ቤት የራሴን እገዛለሁ ልበል። የጋራ መጠቀሚያ ግን የሁሉም ነዋሪ ነው። ከዚህ እስከዚህ ብሎ ሰፍሮ ለክቶ የሚያስረክበው የለም።

ካርታ ሲሰጥ የቤቷ ካርታ ብቻ ነች የምትሰጣቸው። ሙሉ ግቢው የይዞታ ካርታ አለው። የመኖሪያ ቤት ደግሞ የራሱ የምትኖርበት የቤቱ ካርታ አለው። ከዛ ውጭ ያለው ቦታ የአንተ አይደለም። ሪል ስቴቶች አልምተው ሲወጡ ምንድነው ለገዢዎቹ ማድረግ ያለባቸው ? ለሚለው በማሕበር እንዲደራጁ ይደረግና ማሕበሩ ነው ጉዳዩን መያዝ ያለበት። ለሁሉም የጋራ መጠቀሚያ ስለሆነ። ይሄ ግን እየሆነ አይደለም። ያንን የጋራ መጠቀሚያ ቦታ ይገነቡበታል። ሲፈልጉ ይሸጡታል። ገዥዎች ተጠያቂ ሲሆኑ አይታይም።

አዲስ ዘመን ፦ መሰረታዊ ችግሩ ምንድነው ?

ኢንጂነር ደሳለኝ፦ መሬት አንድ ካሬ መሬት በ50 .000 ብርና በ100. 000ብር ከዛም በላይ እየተገዛ በዚህ ዋጋ ለምን አላቀረብክም ተብሎ ሪል እስቴት አልሚን መውቀስ አይቻልም። የመሬት አቅርቦት በጣም ቀላል በሆነበት ቦታ ላይ ቤት በጣም በቅናሽ ዋጋ ማግኘት ይቻላል።

አዲስ ዘመን ፦ የነዋሪዎችን የቤት ችግር መፍታት የሚቻለው እንዴት ነው ?

ኢንጂነር ደሳለኝ፦ የነዋሪዎች የመኖርያ ቤት ችግር የሚፈታው ስርነቀል የፖሊሲ ለውጥ ሲኖር ብቻ ነው የሚል እምነት አለኝ። ሕንድን የሚያህል የሕዝብ ብዛት የለንም። ሕንዶች የሪል እስቴት አብዮት አድርገው ብዙ ቤቶችን ገንብተው ለሕዝቡ አስረክበዋል።

አዲስ ዘመን፦ የሕንድ ሪል እስቴት በማን ነው የሚመራው ?

ኢንጂነር ደሳለኝ፡- ኢንቨስተሮች ናቸው። ፖሊሲ አለው። አንድ ራሱን የቻለ መመሪያ መተዳደሪያ ደንብ ያለው መጽሀፍ አላቸው። ሕጎቻቸውን ማሳየት እችላለሁ።ተጠያቂነቱ ሁሉ አብሮ አለ። ኪራይ እንደፈለጉ ማውጣት አይቻልም።ስለመሬትና ሌሎች ጉዳዮች በዝርዝር የተሰራ ነው። እነሱ በዘርፉ በአመት 25 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ኢንቨስትመንት ለመሳብ እየሰሩ ነው።

አዲስ ዘመን፦ ሌሎች ሀገሮችስ ከሪል እስቴት አንጻር እንዴት ነው የሚሰሩት ?

ኢንጂነር ደሳለኝ፦ የሪል እስቴት ሕጎች ሁሉም ሀገራት አላቸው። ጎረቤት ኬንያ ከእኛ የተሻለ የተደራጀ የሪል እስቴት ሕግ ደንብና ትምህርት አላቸው። እኛ ሀገር ትምህርት የለም። የሪል እስቴት ትምህርት እኛ ሀገር አለ ወይ ብትል መልሱ የለም ነው።

አዲስ ዘመን፦ እርስዎ በሪል እስቴት ዘርፍ ላይ በሀገራችን የመጀመሪያ የሆነውን ትምህርት ቤት እያቋቋሙ ነው። ምንድነው አላማና ግቡ ?

ኢንጂነር ደሳለኝ፦የሪል እስቴት ትምህርት በሀገራችን የመጀመሪያ ስለሆነ አጫጭር ስልጠና ለመስጠት ሕጋዊ ፈቃድ አግኝተናል። አሜሪካን ሀገር ከ1906 እኤአ ጀምሮ ትምህርት ይሰጡበታል። በአለም ላይ ይህ ትምህርት የተጀመረው በዛው ዘመን ነው። እኛ እንግዲህ ከአሜሪካን በፊት ጥንታዊ ስልጣኔ የነበረን ነን። ነገር ግን የቤት ችግር እኛ ሀገር እስከአሁን አልተፈታም። እነሱ ጋ የቤት ችግር ያን ያህል የሚነሳ አይደለም። ባንኮች ያበድራሉ። አሁን እኛ ሀገር አንዱ ችግር የአቅም ውስንነት አለ። ሪል እስቴት እንደ ቢዝነስ ተቋማዊ ሆኖ እነሱ መስራት የጀመሩት ቆይቷል ለማለት ነው። ከመቶ አመታት በላይ ነው።

እነሱ በዘርፉ ስልጠናዎች ይሠጣሉ። በማስትሬት ዲግሪ ደረጃ አላቸው። ራሱን የቻለ ኢንቨስትመንት ነው። አሁን እኛ ሀገር የቴክስታይል ኢንደስትሪ የሚባል ትምህርት አለ። ልጆች ይመረቃሉ። ይወጣሉ። በእኛ ሀገር የሪል እስቴት ሽያጭ ስራን ማነው የሚሰራው ? ባዮሎጂ ፣ግብርና ፣ ኢኮኖሚስት የተማረ ሁሉም ነው። ስራው በትምህርት

እኛ ትኩረታችን ስራ ላይ ያሉ ልጆች አሉ። አሁን ጫማ እያስጠረግህ እያለህ ቤት ግዛ ብሎ የሚመጣ አለ። ቲማቲምና ሌላ ገዝተህ ከሱፐር ማርኬት ስትወጣ ቤት ግዛ ይሉሀል። ይሄን ስራ የሚሰሩ እየተለማመዱ ያሉ ልጆች አሉ ማለት ነው። ብዙዎቹን ዞረን የዳሰሳ ጥናት አድርገናል። ትምህርት የላቸውም። አልወሰዱም። ለዛ ነው ትምህርት ቤቱን ማቋቋም የፈለኩት። ዋናው ስራዬ ማማከር ነው።

አዲስ ዘመን፦ የተሻለ የሪል እስቴት ሕግና ደንብ ካላቸው ሀገራት ውስጥ ተጠቃሽ የሆኑትን ቢነግሩን ?

ኢንጂነር ደሳለኝ፦ እኛን የመሰሉ ጥቂት ሀገራት ካልሆኑ በስተቀር ብዙዎች በዘርፉ ስኬታማ ሆነው እየሰሩ ነው። ዱባይን የመሰለ ከተማ በጥቂት አመታት መገንባት የተቻለው አስተማማኝና ምቹ የሆነ የሪል እስቴት ኢንቨስትመንት አካሄድ ስላላቸውና በእውቀት ላይ ተመስርተው ስለሰሩ ነው።

ብዙ ሀገራት ወደ አንድ ዘርፍ ኢንቨስትመንት በሚገቡበት ግዜ መጀመሪያ ሕግና ደንባቸውን አዘጋጅተው ነው የሚጀምሩት። ይሄ አሰራር እኛ ሀገር ባለመኖሩ ስኬታማ አይደለንም።

አዲስ ዘመን፦ በእኛ ሀገር ሪል እስቴት በፖሊሲ ደረጃ ሕጎችና ደንቦች እንዲቀረጹለት መንግስትን አላነጋገራችሁም ?

ኢንጂነር ደሳለኝ፦ ሪል እስቴት ግብይት የሚመራበት መመሪያ ለማውጣት መንግስት እየሄደበት እንደሆነ መረጃዎች ሰምተናል። እኛን በተመለከተ ግን ለትምህርት ቤቱ ፈቃድ እንዲሰጠን ሄደን ስንጠይቅ ተረድተውን ባለው ማዕቀፍ ውስጥ እንዴት አድርገን እንደምንሰራ አስረድተው ድጋፍ አድርገው እውቅና ሰጥተውናል።

አዲስ ዘመን፦ የሰሜን አሜሪካው ሪል እስቴት የታችኛውን ሕብረተሰብ የቤት ፍላጎት መመለስ ችሏል?

ኢንጂነር ደሳለኝ፦ የታችኛውን ሕብረተሰብ የቤት ችግር ለመቅረፍ የሚያስችል አሰራር አላቸው። ይህ ለእነሱ የሰው ልጆች መብት በመሆኑ መንግስታት ትኩረት ሰጥተው የሚሰሩት ስራ ነው። አስተማማኝ የገንዘብ አቅም የገነቡ ለቤት ግንባታና ግዥ የሚያበድሩ የሞርጌጅ ባንኮች አሏቸው። እንደየዘርፉ በፖሊሲና በፋይናንስ የተደገፈ ነው። የእኛ በፖሊሲም በፋይናንስም አይደገፍም። ከ2 አመት በፊት የሪል እስቴት የግብይት መመሪያ በሚል ፓርላማ ቀርቦ አልጸደቀም። በዚህ መንግስት ብዙ እያጣ ነው።

አዲስ ዘመን፦ መንግሥት የሚያጣው ምንድነው?

ኢንጂነር ደሳለኝ፡- አሁን እስኪ ልጠይቅ፤ መንግሥት ከሪል እስቴት ኢንቨስተሮች ይሄን ያህል ታክስ ሰበሰብኩ ሲል ተሰምቶ ይታወቃል ? ሪፖርትስ ላይ ያየ አለ ? የለም ። ቤት ሲገነባና ሲሸጥ እየዋለ እያደረ ዘርፉ ለሀገሪቱ እያደረገ ያለው አስተዋጽኦ እየተለካም እየተነገረም አይደለም ።

መንግሥት ምናልባት ቤቱ ሲሸጥ ከግብይቱ የሚያገኘው አለ። ስም ሲዟዟር ማለት ነው። ከኢንቨስተሮችም እንደ ትርፍ በታክስ መልክ የሚያገኘው ነገር ይኖራል። ተጠቃሚ ነው ብዬ ግን አላምንም። የመንግሥት መጠቀም ነው የሕዝብን መጠቀም የሚያሳየው።

አዲስ ዘመን፦ በሀገራችን ምን ያህል ሪል እስቴት አልሚዎች አሉ?

ኢንጂነር ደሳለኝ፦ የዛሬ ሁለት አመት አካባቢ ድረስ ከ1500 በላይ የተመዘገቡ ባለሀብቶች ነበሩ። ይለያያል። ተግባራዊ እንቅስቃሴ የጀመረ አለ። የተመዘገበው ቁጥር የነገርኩህን ቁጥር ቢያሳይም ባለን ጥናት መሰረት ስራ ላይ ያሉት ከ100 በታች ናቸው። አንደኛው በብዛት ያለው አዲስ አበባ ነው። ሁለተኛው ኦሮሚያ ፡ሶስተኛው አማራ ክልል ላይ ነው።

አዲስ ዘመን፦ ሪል እስቴት አልሚዎች ማሕበር መስርተዋል ?

ኢንጂነር ደሳለኝ፦ የላቸውም። ይሄ ባለመሆኑ መብታቸውን እንዲያስከብሩ አላደረጋቸውም ብዬ አምናለሁ። በአጠቃላይ የተመዘገቡት ማለት ፈቃድ ያወጡ እንጂ መሬት የወሰዱ አይደሉም። የእኛ ሕግ የሪል እስቴት ዘርፉን የማይከላከል መሆኑን የሚያሳየው ለትንሽ መሬት ሪል እስቴት አልሚ ነኝ ብሎ መመዝገብ ይችላል። 200 ካሬ ሜትር ቦታ ካለው ሪል እስቴት አልሚ ነኝ ብሎ መመዝገብ ይችላል። እዛ ቦታ ላይ ገንብቼ እሸጣለሁ ብለህ የሪል እስቴት ፈቃድ ማውጣት ትችላለህ። ፈቃድ ማውጣትና ግብር መገበር ይለያያል። ከሰራህ ነው የምትገብረው። ካልሰራህ አትገብርም። እነዚህ ሰዎች ፈቃዱ አላቸው፤ አልሰሩበትም። አይገብሩም። እኔ እንዲያውም የሪል እስቴት ፈቃድ መሰጠት አለበት የምለው በፕሮጀክት ነው። እንደ ካምፓኒ ብቻ ሳይሆን አንድ ፕሮጀክት ገምብቶ ሲጨርስ ፈቃድ አንድ ሁለተኛውን ሲጨርስ ፈቃድ ሁለት. . . ይሆናል ማለት ነው። የድርጅቱ ስኬታማነት መለካት ያለበት ባስረከበው ፕሮጀክት መሆን አለበት ብዬ ነው የማምነው።

አዲስ ዘመን፦ መንግሥት ዘርፉን ለማሳደግ ምን ማድረግ አለበት ብለው ያምናሉ?

ኢንጂነር ደሳለኝ፦ በመንግስት በኩል የሪል እስቴት የግብይት መመሪያ ሸማቾቹን የቤት ገዢዎቹንም የሚጠብቅ የሚከላከል ቢኖር ፤ ሁለተኛ የቤት አቅርቦት በጣም አንገብጋቢ እየሆነ ስለመጣ በተለያዩ ማእቀፎች መሬት እያቆዩ መሸጥ (መሬት ማደለብ) እንዳይኖር ዝም ብለው አስቀምጠው እላዩ ላይ የተወሰነ ነገር እያደረጉ ከመሸጥ ይልቅ ቢሰራበት መልካም ነው።

ኪራይ ሰብሳቢነት የሚለው አባባል ተያይዞ የመጣው ከመሬት ጋር ነው። መሬቱን ያለስራ ዝም ብሎ ያስቀምጠዋል ማለት ነው። እንደዚህ ከሚሆን በተለያዩ ማዕቀፎች ለምሳሌ ከአንድ ሚሊዮን ብር በታች ለነዋሪው ቤት ማቅረብ ይቻላል። አንድ የፕሮጀክት ጥናት አጥንተናል። በቅርቡ አንድ ባለሀብት ተግባራዊ ያደርገዋል። መጠናቸው ጥሩ የሆኑ ቤቶችን መስራት ይቻላል።

ይሄን ማድረግ የሚቻለው እንዴት ነው ካልን መንግሥት መሬት በማቅረብ ባለሀብቱንና ትክክለኛ አልሚዎችን በመለየት ማበረታታት በፋይናንስ በባንክ ድጋፍ እንዲያገኙ ማገዝ አለበት። መንግሥት በዚህ መልኩ ቢያግዝ የተሻለ ውጤት ይገኛል። ሶስተኛው ነጥብ የእኛም ሀገር ባለሀብቶች ለብቻቸው ባያለሙ ለምሳሌ አንዱ አንድ ፕሮጀክት ብቻውን ከሚሰራ ባንክ ብድር ከመጠበቅ ሌላ ደግሞ ብር ያለው ሰው ይኖራል አብረው ቢሰሩ የጋራ ውጤት ያመጣሉ ማለት ነው።

የመሬት ይዞታ ያላቸው ሰዎች አሉ። እነዚህ ከሌሎች ባለሀብቶች ጋር ሆነው ለምን በጋራ አይሰሩም የሚለውንም ማየት ያስፈልጋል። መንግስት ማተኮር ያለበት በመሬት አቅርቦት ላይ መሆን አለበት ።

አዲስ አበባ ከተማ ከ70 ፐርሰንት በላይ ፈርሶ የሚሰራ ከተማ ነው። ዝም ብለህ ቆመህ ስታይ እኮ ባዶ ነው። አዲስ አበባ ውስጥ መሬት የለንም የሚባለውን ነገር አልስማማበትም። መቼ ተነካና፤ ከተማዋ ውስጥ ያልለማ ሰፊ መሬት አለ።

አንድ መንደርን በምሳሌነት እንውሰድ። 20 ወይንም 30 ሺህ ካሬ ሊሆን ይችላል። እዛ ውስጥ ለሚኖሩት ለተወሰኑት ቤት ሰርቶ ያነሳል። ደረጃ በደረጃ። የግለሰብ ይዞታ ለሆኑት ቤቶች መንግስት ተተኪ ቦታ ይሰጣቸዋል። የቀበሌ ነዋሪ ለሆኑት ግን ግለሰቡ ገንብቶ ካርታ እንዲሰጣቸው ቢደረግ አንደኛ ሰዎቹ ባለቤት ስለሆኑ ደስተኛ ይሆናሉ። ሁለተኛ ቦታውን በፈቃዳቸው ይለቃሉ። ኑሮአቸውም አይፈናቀልም። ባለሀብቱም ከአካባቢ ሰው ጋር በፍቅር ይሰራል። ሰፈሩም ደረጃ በደረጃ ይለማል ማለት ነው። መጀመሪያ ሰውን አንስቶ ከዛ በኋላ መገንባት ግን ትክክል ነው ብዬ አላምንም። አንድን ሰው ከልደታ አንስተህ ቦሌ አራብሳ መውሰድ ኑሮውን ያዛባዋል። ዋናው ነጥባችን የሪል እስቴት ጉዳይ ባለቤት ይኑረው የሚለው ነው።

አዲስ ዘመን፦ ስለሰጡን ቃለ ምልልስ እናመሰግናለን።

ኢንጂነር ደሳለኝ ከበደ ፦ እኔም አመሰግናለሁ።

አዲስ ዘመን መጋቢት 25 ቀን 2013 ዓ.ም

Tags: Real estate
Previous Post

በአዲስ አበባ የመሬት አገልግሎቶች ታገዱ

Next Post

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን 3,452 የመኖሪያና የንግድ ቤቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለሽያጭ ማቅረቡን ገለጸ

Betegna Team

Betegna Team

Betegna - ቤተኛ, is a media platform that focuses on Ethiopian housing and real estate news, developments, technology, policies, and lifestyle.

ተዛማጅ ጽሑፎች

የሪል እስቴት አልሚዎች ማህበር የ7% የብድር ወለድ ጥያቄ በባለሙያዎች መካከል ያስነሳው ክርክር
Insights & Profiles

የሪል እስቴት አልሚዎች ማህበር የ7% የብድር ወለድ ጥያቄ በባለሙያዎች መካከል ያስነሳው ክርክር

November 18, 2026
በከፊል የተጠናቀቁ አፓርትመንቶች መኖሪያ ቤቶች አይደሉም
Insights & Profiles

በከፊል የተጠናቀቁ አፓርትመንቶች መኖሪያ ቤቶች አይደሉም

September 25, 2026
ተሾመ ግርማ በቴምር ፕሮፐርቲስ የሽያጭና ማርኬቲንግ ሥራ አስኪያጅ፤ ቀደም ሲል የሀሞና መስራችና በአያት ሪል እስቴት የሽያጭ ሰራተኛ
Insights & Profiles

በስምንት ዓመታት የሪል እስቴት ጉዞዬ ከ1,000 በላይ ቤቶችን ለመሸጥ የቻልኩበት ሚስጥር

September 25, 2026
Next Post
የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን 3,452 የመኖሪያና የንግድ ቤቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለሽያጭ ማቅረቡን ገለጸ

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን 3,452 የመኖሪያና የንግድ ቤቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለሽያጭ ማቅረቡን ገለጸ

  • Trending
  • Comments
  • Latest
የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የወጣ አዋጅ 721/2004

የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የወጣ አዋጅ 721/2004

April 23, 2024
ስለ ግብር የሚከፈልበት የቤት ኪራይ ገቢ

ስለ ግብር የሚከፈልበት የቤት ኪራይ ገቢ

April 6, 2024
በአዲስ አበባ የቤት ሽያጭ ዋጋ ተመን ላይ በድጋሚ ማሻሻያ ተደረገ

በአዲስ አበባ የቤት ሽያጭ ዋጋ ተመን ላይ በድጋሚ ማሻሻያ ተደረገ

April 3, 2024
የመሬት ልማትና አስተዳር ደንብ ቁጥር 163/2016

የመሬት ልማትና አስተዳር ደንብ ቁጥር 163/2016

April 22, 2024
ስለ ሪል እስቴት ምን ያውቃሉ?

ስለ ሪል እስቴት ምን ያውቃሉ?

August 18, 2023
Home pic

ቤት ለሚገዙ እና ለሚሸጡ አካላት ማሳሰቢያ ተሰጠ

0
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤት አቅርቦትን ለማሳደግ የሚያስችል ውይይት ከሪል እስቴት አልሚዎች ጋር ውይይት አደረገ!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤት አቅርቦትን ለማሳደግ የሚያስችል ውይይት ከሪል እስቴት አልሚዎች ጋር ውይይት አደረገ!

0
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ያስተዋወቀበትን የገርጂ መኖሪያ መንደር ፕሮጀክት ሊያስመርቅ ነው

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ያስተዋወቀበትን የገርጂ መኖሪያ መንደር ፕሮጀክት ሊያስመርቅ ነው

0
ባለ 9 ወለል ህንፃ በተጀመረ በ69ኛ ቀኑ ተጠናቀቀ!!

ባለ 9 ወለል ህንፃ በተጀመረ በ69ኛ ቀኑ ተጠናቀቀ!!

0
ስለ ሪል እስቴት ምን ያውቃሉ?

ስለ ሪል እስቴት ምን ያውቃሉ?

0
የሪል እስቴት አልሚዎች ማህበር የ7% የብድር ወለድ ጥያቄ በባለሙያዎች መካከል ያስነሳው ክርክር

የሪል እስቴት አልሚዎች ማህበር የ7% የብድር ወለድ ጥያቄ በባለሙያዎች መካከል ያስነሳው ክርክር

November 18, 2026
በጋዜቦ አደባባይ አካባቢ በግንባታ ሂደት ላይ ከነበረ ሕንጻ ላይ የወደቁ ሦስት ሠራተኞች ሕይወታቸውን አጡ

በጋዜቦ አደባባይ አካባቢ በግንባታ ሂደት ላይ ከነበረ ሕንጻ ላይ የወደቁ ሦስት ሠራተኞች ሕይወታቸውን አጡ

November 14, 2026
በ5 ዓመታት ቤቶችን ገንብተን ለማስረከብ የገባነውን ቃል በተግባር ለማረጋገጥ እየተጋን ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

በ5 ዓመታት ቤቶችን ገንብተን ለማስረከብ የገባነውን ቃል በተግባር ለማረጋገጥ እየተጋን ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

November 13, 2026
የ1.5 ሚሊዮን መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት ወደ ተግባር ምዕራፍ ተሸጋግሯል

የ1.5 ሚሊዮን መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት ወደ ተግባር ምዕራፍ ተሸጋግሯል

November 12, 2026
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከዩኤን ሃቢታት ዋና ዳይሬክተር አናክላውዲያ ሮስባክ ጋር መወያየታቸውን ገለፁ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከዩኤን ሃቢታት ዋና ዳይሬክተር አናክላውዲያ ሮስባክ ጋር መወያየታቸውን ገለፁ

November 11, 2026

ብዙ የተነበቡ

  • የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የወጣ አዋጅ 721/2004

    የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የወጣ አዋጅ 721/2004

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ስለ ግብር የሚከፈልበት የቤት ኪራይ ገቢ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአዲስ አበባ የቤት ሽያጭ ዋጋ ተመን ላይ በድጋሚ ማሻሻያ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የመሬት ልማትና አስተዳር ደንብ ቁጥር 163/2016

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ስለ ሪል እስቴት ምን ያውቃሉ?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Categories

  • Community & CSR (28)
  • Construction & Projects (29)
  • Construction Material Supply (9)
  • Design & Innovation (18)
    • Architecture (2)
    • Technology (14)
  • Global (4)
  • Insights & Profiles (20)
  • Legal Updates (89)
    • Community Complaints (8)
    • Corruption (ሙስና) (2)
    • Directives (መመሪያዎች) (1)
    • Proclamations (አዋጅ) (7)
    • Regulations (ደንብ) (2)
  • Mortgages & Finance (14)
  • Property Handover (16)
  • Public Housing (71)
  • Real Estate Guides (13)
    • Buying Guide (3)
    • Knowledge Base (1)
    • Renting Guide (2)
    • Selling Guide (7)
  • Sales & Marketing (67)
  • Tenders & Bids (60)
    • Land Lease (29)
    • Request for EOI (1)
  • Home
  • Guides
  • Mortgage
  • Highlights
  • Legal Updates
  • Tenders & Bids
Betegna Logo Footer

Betegna – ቤተኛ, powered by Betbegara.com, is a media platform that focuses on Ethiopian housing and real estate news, developments, technology, policies, and lifestyle.

© 2026 Betegna – ቤተኛ | Ethiopian Housing and Real Estate News & Insights

  • Home
  • Guides
    • Buying Guide
    • Renting Guide
    • Selling Guide
    • Knowledge Base
  • Mortgage
  • Technology
  • Legal
    • Proclamations (አዋጅ)
    • Regulations (ደንብ)
    • Directives (መመሪያዎች)
    • Community Complaints
    • Corruption (ሙስና)
  • Tender
    • Auction (ሐራጅ)
    • Land Lease (የመሬት ሊዝ)
    • Request for EOI
  • Project Highlight
  • More
    • Community & CSR
    • Construction & Projects
    • Construction Material Supply
    • Design & Innovation
    • Public Housing
    • Insights & Profiles
    • Sales & Marketing
    • Property Handover
    • Global
    • Contact Us
No Result
View All Result
Sell, Buy, Rent