• BetBegara.com
  • Buy
  • Rent
  • Sale
  • Services
  • Contact Us
Betegna - ቤተኛ | Ethiopian Housing and Real Estate News & Insights
Advertisement
  • Home
  • Guides
    • Buying Guide
    • Renting Guide
    • Selling Guide
    • Knowledge Base
  • Mortgage
  • Technology
  • Legal
    • Proclamations (አዋጅ)
    • Regulations (ደንብ)
    • Directives (መመሪያዎች)
    • Community Complaints
    • Corruption (ሙስና)
  • Tender
    • Auction (ሐራጅ)
    • Land Lease (የመሬት ሊዝ)
    • Request for EOI
  • Project Highlight
  • More
    • Community & CSR
    • Construction & Projects
    • Construction Material Supply
    • Design & Innovation
    • Public Housing
    • Insights & Profiles
    • Sales & Marketing
    • Property Handover
    • Global
    • Contact Us
No Result
View All Result
Sell, Buy, Rent
  • Home
  • Guides
    • Buying Guide
    • Renting Guide
    • Selling Guide
    • Knowledge Base
  • Mortgage
  • Technology
  • Legal
    • Proclamations (አዋጅ)
    • Regulations (ደንብ)
    • Directives (መመሪያዎች)
    • Community Complaints
    • Corruption (ሙስና)
  • Tender
    • Auction (ሐራጅ)
    • Land Lease (የመሬት ሊዝ)
    • Request for EOI
  • Project Highlight
  • More
    • Community & CSR
    • Construction & Projects
    • Construction Material Supply
    • Design & Innovation
    • Public Housing
    • Insights & Profiles
    • Sales & Marketing
    • Property Handover
    • Global
    • Contact Us
No Result
View All Result
Betegna - ቤተኛ | Ethiopian Housing and Real Estate News & Insights
No Result
View All Result
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመሃል ከተማ እና በመንገድ ኮሪደር መልሶ ማልማት ፕሮጀክት ያገኛቸውን ቦታዎች በሊዝ ጨረታ ሊሸጥ ነው

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመሃል ከተማ እና በመንገድ ኮሪደር መልሶ ማልማት ፕሮጀክት ያገኛቸውን ቦታዎች በሊዝ ጨረታ ሊሸጥ ነው

Betegna Team by Betegna Team
April 8, 2024
in Land Lease
A A
0
0
SHARES
Share on FacebookShare on LinkedIn

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመሃል ከተማ እና በመንገድ ኮሪደር መልሶ ማልማት ፕሮጀክት ያገኛቸውን ግንባር ቦታዎች ለግሉ ዘርፍ ለማስተላለፍ የጨረታ ሰነድ ዝግጅት እንዲጀመር ትዕዛዝ ሰጥቷል።

በዚህም ምክንያት የከተማው መሬት ልማት እና አስተዳደር ቢሮ የመሬት ስሪት ባለሙያዎች የጨረታ ሰነድ ዝግጅት ሥራ ላይ ተጠምደው ሰንብተዋል።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ፣ ለሊዝ ጨረታ የሚቀርቡ ቦታዎች በርካታ በመሆናቸው፣ መሬት ለማግኘት ደጅ ሲጠኑ የከራረሙ ባለሃብቶች ሁሉ ገዥ ቦታዎችን የማግኘት ዕድላቸው ሰፊ እንደሚሆን ታምኗል – በቅርቡ በሚወጣው ሊዝ ጨረታ የኮሪደር ልማቱ ሌላኛው ትሩፋት ይፋ ይሆናል።

በስድስት ክፍለ ከተሞች የሚከናወነው የመንገድ ኮሪደር ልማት በዋና ዋናዎቹ የከተማዋ አምስት አውራ ጎዳናዎች ላይ እና እንደ አካባቢው ነባራዊ ሁኔታ ከዋና መንገድ ወደ ውስጥ መቶ ሜትር ገባ ብሎ ጭምር የሚካሄድ በመሆኑ የከተማውን የተለመደ መልክ ይቀይራል ተብሎ ይጠበቃል።

በዚህ መሠረታዊ የመልክ ለውጥ ግዙፍ ንቅናቄ በድምሩ 1,033 ሔክታር መሬት ይለማል። በዚህ ሰፊ እና በከተማው ታሪክ ያልተለመደ ሰፊ ልማት የግሉ ዘርፍም በከፍተኛ ደረጃ ተሳታፊ እንደሚሆን ይጠበቃል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፒያሳን ጨምሮ በመንገድ ኮሪደር መልሶ ማልማት ፕሮጀክት ሊያመጣ ያቀደውን ልማት በዋናነት በራስ አቅም፣ በግልና የመንግስት አጋርነት እና በግሉ ዘርፍ ለማካሄድ ያቀደ ሲሆን፣ ለግሉ ዘርፍ በሊዝ ጨረታ እና በአገራዊ ፋይዳ (ድርድር) ቀመር በሽህ የሚቆጠሩ ቦታዎችን በማቅረብ ዕውን እንደሚያደርግ ዕቅድ ተይዟል።

ከፕሮጀክቱ ቀጣና እየተነሱ ለሚገኙ ነዋሪዎችም መኖሪያ ቤት፣ ምትክ ቦታ፣ ካሳ፣ የመሥሪያ ቦታ፣ የትራንስፖርት ወጪ፣ የሞራል ካሣ ተሰጥቷል፤ በመስጠት ላይም ይገኛል።
በኮሪደር ልማት ቀጣና የሚገኙ ማልማት ለሚችሉ ቅድሚያ የማልማት መብት ተጠብቆላቸው እና ለግል የመኖሪያ ቤት ተነሺዎች ቤታቸውን እስከሚገነቡ ድረስ የቤት ኪራይ ወጪ ጭምር አየተሰጠ መሆኑ ተመልክቷል።

በከተማው እየተካሄደ የሚገኘው ፕሮጀክት ስፋት እና ጥልቀት እንዲሁም ቅንጅት ከዚህ ቀደም በከተማው ታሪክ ታይቶ አያውቅም። የቀድሞው ኢሕአዴግ አመራር የነበሩ ሰው “በዚህ ደረጃ ልማት ማካሄድ እንደሚቻል እንዴት ማሰብ ሳንችል ቀረን!?” በማለት በፀፀት አስታውሰው “አፍራሽ ግብረ ኃይሉም ሆነ የግንባታ ተዋንያኑ በከፍተኛ ትኩረት መሥራታቸው፣ የአመራሮቹ ክትትል ፣ ድጋፍ እና ውሳኔ አሰጣጥ ልዩ ነው” ሲሉ አድናቆታቸውን ተናግረዋል።

በከተማው በአምስት አቅጣጫ የኮንስትራክሽን ማሽኖች ያፈርሳሉ፣ ይቆፍራሉ፣ ይገነባሉ፤ ባለሙያዎች ደፋ ቀና ይላሉ። ፕሮጀክቱም በከፍተኛ ፍጥነት እየተካሄደ ነው። የፕሮጀክቱን ጥድፊያ የዝናብ መጣል፣ የለሊት ቁር እና ድካምም ሊያስቆመው አልቻለም።
ፕሮጀክቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) በቀጥታ የሚከታተሉት ከመሆኑም ባሻገር በቅርበት አመራር እየሰጡበት ይገኛሉ። ከንቲባ አዳነች እና ካቢኔያቸው ሙሉ በሙሉ ትኩረቱን በዚህ የቢሊዮን ብሮች ፕሮጀክት ላይ ያደረገ ከመሆኑም ባሻገር፣ ከተለያዩ አቅጣጫዎች የሚቀርቡ የተደበላለቁ የኀብረተሰብ አስተያየቶችን በመልክ በመልኩ ለመመለስ እየጣረ መሆኑ እየታየ ነው።

ከኀብረተሰቡ ጎልተው ከሚነሱ ጉዳዮች መካከል የፒያሳ ታሪካዊ ዳራ ዕጣ ፈንታ መጨረሻ ተጠቃሽ ነው። አዲስ አበባ ከተማ የ140 ዓመት ታሪክ አላት ከተባለ ዋነኛ ተጠቃሽ ሰፈሮች አራዳ (ፒያሳ)፣ ለገሃር፣ አራት ኪሎ አለፍ ሲልም አዲስ ከተማ (መርካቶ) ናቸው። በነዚህ አካባቢዎች የሚካሄደው ልማት የጋራ ትውስታዎችን ያገናዘበ መሆን እንዳለበት ባለሙያዎች ይናገራሉ።

በተለይ በፒያሳ እና ዙሪያዋ በድጋሚ የሚለማው 66 ሄክታር መሬት ተደጋጋሚ የባለሞያዎች ውይይት ይፈልጋል። ፒያሳ የቁም ነገሮች ጅማሮ እና ጅማሮውን ይዞ የዘለቀ እንደመሆኑ በአዲሱ ፕሮጀክት የወርቅ እና ጌጣጌጦች ክላስተር፣ የሉካንዳ ቤቶች ክላስተር፣ የጣፋጭ ምግቦች ክላስተር እንዲሁም ቴዎድሮስ አደባባይ የሚገኘው ሴጣን ቤት እና ዙሪያ ገባው የመዝናኛ ኢንዱስትሪ (ፊልም፣ ቴያትር እና ሙዚቃ) ክላስተር አካቶ መገንባት እንዳለበት ባለሙያዎች ይናገራሉ።
መንግስት እነዚህን ቁም ነገሮች ሳይረፍድ ከግንዛቤ እንዲያስገባ የሚጠይቁም በርካቶች ናቸው።

ምንጭ፦ ውድነህ ዘነበ

Tags: Addis Ababa Corridor projectCorridorመንገድ ኮሪደር መልሶ ማልማት
Previous Post

ስለ ግብር የሚከፈልበት የቤት ኪራይ ገቢ

Next Post

መሬት እናሰጣለን በሚል ሙስና ተቀብለዋል የተባሉ የመዲናዋ የቀድሞ ሠራተኞች እስከ 13 ዓመት በሚደርስ እስራት ተቀጡ

Betegna Team

Betegna Team

Betegna - ቤተኛ, is a media platform that focuses on Ethiopian housing and real estate news, developments, technology, policies, and lifestyle.

ተዛማጅ ጽሑፎች

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የ9ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ: ማስታወቂያ
Land Lease

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የ9ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ: ማስታወቂያ

November 9, 2026
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የ9ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ: ፕሬስ ሪሊዝ
Land Lease

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የ9ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ: ፕሬስ ሪሊዝ

November 7, 2026
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የ7ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ: ተጨማሪ የተሰረዙ ቦታዎች
Land Lease

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የ7ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ: ተጨማሪ የተሰረዙ ቦታዎች

November 5, 2025
Next Post
መሬት እናሰጣለን በሚል ሙስና ተቀብለዋል የተባሉ የመዲናዋ የቀድሞ ሠራተኞች እስከ 13 ዓመት በሚደርስ እስራት ተቀጡ

መሬት እናሰጣለን በሚል ሙስና ተቀብለዋል የተባሉ የመዲናዋ የቀድሞ ሠራተኞች እስከ 13 ዓመት በሚደርስ እስራት ተቀጡ

  • Trending
  • Comments
  • Latest
የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የወጣ አዋጅ 721/2004

የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የወጣ አዋጅ 721/2004

April 23, 2024
ስለ ግብር የሚከፈልበት የቤት ኪራይ ገቢ

ስለ ግብር የሚከፈልበት የቤት ኪራይ ገቢ

April 6, 2024
በአዲስ አበባ የቤት ሽያጭ ዋጋ ተመን ላይ በድጋሚ ማሻሻያ ተደረገ

በአዲስ አበባ የቤት ሽያጭ ዋጋ ተመን ላይ በድጋሚ ማሻሻያ ተደረገ

April 3, 2024
የመሬት ልማትና አስተዳር ደንብ ቁጥር 163/2016

የመሬት ልማትና አስተዳር ደንብ ቁጥር 163/2016

April 22, 2024
ስለ ሪል እስቴት ምን ያውቃሉ?

ስለ ሪል እስቴት ምን ያውቃሉ?

August 18, 2023
Home pic

ቤት ለሚገዙ እና ለሚሸጡ አካላት ማሳሰቢያ ተሰጠ

0
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤት አቅርቦትን ለማሳደግ የሚያስችል ውይይት ከሪል እስቴት አልሚዎች ጋር ውይይት አደረገ!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤት አቅርቦትን ለማሳደግ የሚያስችል ውይይት ከሪል እስቴት አልሚዎች ጋር ውይይት አደረገ!

0
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ያስተዋወቀበትን የገርጂ መኖሪያ መንደር ፕሮጀክት ሊያስመርቅ ነው

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ያስተዋወቀበትን የገርጂ መኖሪያ መንደር ፕሮጀክት ሊያስመርቅ ነው

0
ባለ 9 ወለል ህንፃ በተጀመረ በ69ኛ ቀኑ ተጠናቀቀ!!

ባለ 9 ወለል ህንፃ በተጀመረ በ69ኛ ቀኑ ተጠናቀቀ!!

0
ስለ ሪል እስቴት ምን ያውቃሉ?

ስለ ሪል እስቴት ምን ያውቃሉ?

0
የሪል እስቴት አልሚዎች ማህበር የ7% የብድር ወለድ ጥያቄ በባለሙያዎች መካከል ያስነሳው ክርክር

የሪል እስቴት አልሚዎች ማህበር የ7% የብድር ወለድ ጥያቄ በባለሙያዎች መካከል ያስነሳው ክርክር

November 18, 2026
በጋዜቦ አደባባይ አካባቢ በግንባታ ሂደት ላይ ከነበረ ሕንጻ ላይ የወደቁ ሦስት ሠራተኞች ሕይወታቸውን አጡ

በጋዜቦ አደባባይ አካባቢ በግንባታ ሂደት ላይ ከነበረ ሕንጻ ላይ የወደቁ ሦስት ሠራተኞች ሕይወታቸውን አጡ

November 14, 2026
በ5 ዓመታት ቤቶችን ገንብተን ለማስረከብ የገባነውን ቃል በተግባር ለማረጋገጥ እየተጋን ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

በ5 ዓመታት ቤቶችን ገንብተን ለማስረከብ የገባነውን ቃል በተግባር ለማረጋገጥ እየተጋን ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

November 13, 2026
የ1.5 ሚሊዮን መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት ወደ ተግባር ምዕራፍ ተሸጋግሯል

የ1.5 ሚሊዮን መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት ወደ ተግባር ምዕራፍ ተሸጋግሯል

November 12, 2026
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከዩኤን ሃቢታት ዋና ዳይሬክተር አናክላውዲያ ሮስባክ ጋር መወያየታቸውን ገለፁ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከዩኤን ሃቢታት ዋና ዳይሬክተር አናክላውዲያ ሮስባክ ጋር መወያየታቸውን ገለፁ

November 11, 2026

ብዙ የተነበቡ

  • የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የወጣ አዋጅ 721/2004

    የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የወጣ አዋጅ 721/2004

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ስለ ግብር የሚከፈልበት የቤት ኪራይ ገቢ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአዲስ አበባ የቤት ሽያጭ ዋጋ ተመን ላይ በድጋሚ ማሻሻያ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የመሬት ልማትና አስተዳር ደንብ ቁጥር 163/2016

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ስለ ሪል እስቴት ምን ያውቃሉ?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Categories

  • Community & CSR (28)
  • Construction & Projects (29)
  • Construction Material Supply (9)
  • Design & Innovation (18)
    • Architecture (2)
    • Technology (14)
  • Global (4)
  • Insights & Profiles (20)
  • Legal Updates (89)
    • Community Complaints (8)
    • Corruption (ሙስና) (2)
    • Directives (መመሪያዎች) (1)
    • Proclamations (አዋጅ) (7)
    • Regulations (ደንብ) (2)
  • Mortgages & Finance (14)
  • Property Handover (16)
  • Public Housing (71)
  • Real Estate Guides (13)
    • Buying Guide (3)
    • Knowledge Base (1)
    • Renting Guide (2)
    • Selling Guide (7)
  • Sales & Marketing (67)
  • Tenders & Bids (60)
    • Land Lease (29)
    • Request for EOI (1)
  • Home
  • Guides
  • Mortgage
  • Highlights
  • Legal Updates
  • Tenders & Bids
Betegna Logo Footer

Betegna – ቤተኛ, powered by Betbegara.com, is a media platform that focuses on Ethiopian housing and real estate news, developments, technology, policies, and lifestyle.

© 2026 Betegna – ቤተኛ | Ethiopian Housing and Real Estate News & Insights

  • Home
  • Guides
    • Buying Guide
    • Renting Guide
    • Selling Guide
    • Knowledge Base
  • Mortgage
  • Technology
  • Legal
    • Proclamations (አዋጅ)
    • Regulations (ደንብ)
    • Directives (መመሪያዎች)
    • Community Complaints
    • Corruption (ሙስና)
  • Tender
    • Auction (ሐራጅ)
    • Land Lease (የመሬት ሊዝ)
    • Request for EOI
  • Project Highlight
  • More
    • Community & CSR
    • Construction & Projects
    • Construction Material Supply
    • Design & Innovation
    • Public Housing
    • Insights & Profiles
    • Sales & Marketing
    • Property Handover
    • Global
    • Contact Us
No Result
View All Result
Sell, Buy, Rent