የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ መስከረም 7 ቀን 2019 ዓ.ም ባወጣው የተጠባባቂ ምዝገባ ማስታወቂያ በ70/30 ማህበር ቤት ተደራጅተው ለመስራት ፍላጎት ያላቸውን የ2005 ተመዝጋቢዎች በተጠባባቂነት በኦንላይን መመዝገቡ ይታወሳል።
በዚህም መሠረት ከዚህ በታች ስም ዝርዝራቸው የተገለጸው ተመዝጋቢዎች ከጥቅምት 9 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ሰባት የሥራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት በመገኘት አስፈላጊውን መረጃ እንድታሟሉ ጥሪ ቀርቧል።
ተመዝጋቢዎቹ ባምቢስ ግሪክ ትምህርት ቤት ፊት ለፊት በሚገኘው የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ስድስተኛ ፎቅ በሚገኘው የጋራ መኖሪያ እና ቤት ማህበራት ክትትል ዳይሬክቶሬት በአካል በመገኘት ቅጽ 01 መውሰድ እና መረጃዎችን ማሟላት እንዳለባችሁ ተገልጿል።
ምንጭ:- የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ


















