የክቡር አርቲስት ፕሮፌሰር ተስፋዬ ገሰሰን የሕይወት ጉዞና የጥበብ ሥራዎች የሚዳስስ መጽሐፍ ይፋ የተደረገበት ልዩ የባህልና የሥነ ጥበብ መርሃ ግብር ጥቅምት 7 ቀን 2019 ዓ.ም. በኦቪድ ሆልዲንግስ ግቢ በሚገኘው የካቮድ ኮሜርሻል ሪል እስቴት መሰብሰቢያ አዳራሽ ተካሂዷል።
በደራሲና ጋዜጠኛ ደረጀ ትዕዛዙ የተዘጋጀው መጽሐፍ፣ የአርቲስቱን የሕይወት ታሪክ፣ የጥበብ ሥራዎችና በኢትዮጵያ የሥነ ጥበብ ዘርፍ ያበረከቱትን አስተዋጽኦ ለማስታወስና ለትውልድ ለማስተላለፍ ያለመ የባህል ሰነድ ነው።
በዝግጅቱ የአርቲስቱ የቅርብ ወዳጆች፣ የሙያ አጋሮችና የጥበብ ባለሙያዎች በመገኘት የግል ትውስታዎቻቸውንና ሙያዊ እይታዎቻቸውን አካፍለዋል።
የአዲስ አበባ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ የኪነጥበብ ዘርፍ ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ ሉባባ ጀማል በክብር እንግድነት ተገኝተው፣ የአርቲስቱን የግል ባሕርይና የሙያ ተጽዕኖ በማስታወስ ለጥበብ ዘርፍ የግሉ ዘርፍ ድጋፍ ያለውን ዋጋ አጉልተዋል።
ይህ ተሳትፎ የካቮድ ኮሜርሻል ሪል እስቴት ማኅበራዊ ኃላፊነትን ከተለመዱ የድጋፍ ተግባራት ባሻገር በባህል፣ በማንነትና በሀገራዊ የጥበብ ቅርስ ጥበቃ ላይ በተግባር ለመደገፍ ያለውን አቅጣጫ ያሳያል።
በመርሃ ግብሩ ላይ ጸሐፌ ተውኔትና ገጣሚ አያልነህ ሙላት፣ አርቲስት ተክሌ ደስታ፣ ደበሽ ተመስገንና ተስፋዬ ሲማ፣ ጋዜጠኛና የታሪክ ተመራማሪ ጥበቡ በለጠ እንዲሁም ደራሲ እዝራ እጅጉ ተሳትፈዋል።
ካቮድ ኮሜርሻል ሪል እስቴት በንግድ ልማት ብቻ ሳይወሰን ለማኅበረሰብ፣ ለባህልና ለሀገራዊ እሴቶች ዘላቂ አስተዋጽኦ ለማበርከት ቁርጠኛ ነው።
ምንጭ:- Kavod commercial


















