በከተማዋ የቤት ሽያጭ ዋጋ ተብሎ በገዥ እና ሻጭ መካከል የሚደረግ ውል ላይ የሚቀርበው ዋጋ እጅግ በተጋነነ መልኩ ዝቅተኛ በመሆኑ እና በባለሙያ የሚወሰድ የቤት ግምት ዋጋ ወቅታዊ ባመሆኑ መንግስት ከቤት ሽያጭ ተገቢውን ገቢ እየሰበሰበ እንዳልነበረ ቢሮው ገልጿል።
ይህንን ችግር ለመፍታት እንዲቻል ካለፈው ዓመት ሰኔ 8 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ ወቅታዊ የቤት ሽያጭ ዋጋ ተግባራዊ መሆኑን ጠቅሷል፡፡
የቤት ባለንብረቶች የሚከፍሉትን ዓመታዊ የንብረት ታክስ የሚተምን ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀ
ይሁን እንጂ በከተማ ደረጃ ተጠንቶ ተግባራዊ የተደረገ የቤት ሽያጭ ዋጋ እና አሰራሩ ላይ ከህብረተሰቡ በርካታ ቅሬታዎች እየቀረቡ በመሆኑ በመሬት ልማትና አስተዳደተር ቢሮ እና የመሬት ይዞታ ምዝገበና መረጃ አጄንሲ በጋራ ጥናት በማድረግ የተለዩ ክፍተቶችና እና የቤት ሽያጭ ግምት ላይ ማሻሻያ ተደርጓል ብሏል።
በዚህም መሰረት መጋቢት 23 ቀን 2016 ዓ.ም በተሠራጨው አዲስ መመሪያ በኮንዶሚኒየም ቤቶች እና በአፓርታማዎች ሽያጭ የካሬ ሜትር ዋጋ ላይ በአማካኝ 34 በመቶ ቅናሽ ተደርጓል። በአፓርታማና በኮንዶሚኒየም ቤቶች ሽያጭ ስሌት ላይም እንዲሁ ጉልህ ቅናሽ ተደርጓል።
በተሻሻለው የቤት ሽያጭ ዋጋ ተመን መሰረት ከኮንደሚንየም እና አፓርትመንት ውጪ ለሆኑ ግንባታዎች፦
- የግንባታ ነጠላ ዋጋ በጭቃ የተሰራ ቪላ ቤት (G+0) ነጠላ ዋጋ በካሬ 15,000 ብር፣
- በብሎኬት የተሰራ የቪላ ቤት (G+0) ነጠላ ዋጋ በካሬ 20,000 ብር፣
- የህንጻ ወለላቸው ከG+1 እስከ G+5 25,000 ብር እና፣
- G+6 እና በላይ የሆኑ ቤት ወይም ህንጻ ነጠላ ዋጋ በካሬ 30,000 ተደርጓል፡፡

ለኮንዶሚኒየም ቤቶች

ለአፓርትመንት ይዞታዎች የተቀመጡ አማራጭ ሀሳቦች

የቦታው መገኛ ዋጋ (‘location value’) ለከተማው የቦታ ደረጃ የጸደቀው ወቅታዊ አማካይ የሊዝ ጨረታ ዋጋ እንዲሆን መደረጉም ተገልጿል።
የቤት ስም ንብረት ዝውውር ክፍያ ማለትም አሹራ 4 በመቶ እና የቴምብር ቀረጥ 2 በመቶ ከጠቅላላ የቤቱ ሽያጭ ዋጋ ተሰልቶ ከ ከመጋቢት 17 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ እንዲከፈልም ቢሮ አዟል።
ባለፈው ዓመት ሰኔ ወር ጀምሮ ተግባራዊ የተደረገው የቤት ሽያጭ ዋጋ ተመን መሻሩንም ቢሮ ጠቅሷል።
በፍርድ ቤት እና በባንክ ሃራጅ ሽያጭ የስም ንብረት ዝውውር የሚጠየቅባቸው ይዞታዎችን በተመለከተ ይዞታ አገልግሎትና መብት ፈጠራ ደንብ ላይ በተቀመጠው አግባብ ተፈጻሚ ይሆናል ተብሏል።
ይህ ማሻሻያ መምሪያ ከመውጣቱ በፊት የስም ንብረት ዝውውር አገልግሎት ጠይቀው በሂደት ላይ ሆኖ ክፍያ የፈጸሙ ተጋልጋዮች በቀድሞ አሰራር በከፈሉት ክፍያ መሰረት ይስተናገዳሉ ተብሏል።
ግንባታቸው ያልተጠናቀቁ ህንፃዎች የትመና ስራ የሚሰራላቸው ግንባታው በደረሰበት ወይም አሁን ላይ ባለበት ግንባታ ደረጃ እንደሚሆን ተገልጿል።
ለሚመለከታቸው አካላት የተላለፈው ሙሉ መረጃ ከታች ተያይዟል።
















