የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ 6ኛ ዓመት 3ኛ መደበኛ ስብሰባውን ማካሄዱን የከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ አስታወቀ።
ካቢኔው በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ሰፊ ውይይት በማድረግ ውሳኔዎችን አስተላልፏል።
በዚሁ መሠረት፣ የመሬት ይዞታ መብት ፈጠራ እና አገልግሎት አሰጣጥ ደንብ ቁጥር 163/2016 አንቀጽ 19 ንኡስ አንቀጽ 7 ላይ በቀረበው የማሻሻያ ሀሳብ ላይ ተወያይቶ አጽድቆታል።
ከዚህ በተጨማሪም አገራዊ ፋይዳ ላላቸው የቤት ልማት እና የሆቴል ግንባታ ፕሮጀክቶች የቀረቡትን የመሬት ምደባ ጥያቄዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አስተላልፏል።


















