• BetBegara.com
  • Buy
  • Rent
  • Sale
  • Services
  • Contact Us
Betegna - ቤተኛ | Ethiopian Housing and Real Estate News & Insights
Advertisement
  • Home
  • Guides
    • Buying Guide
    • Renting Guide
    • Selling Guide
    • Knowledge Base
  • Mortgage
  • Technology
  • Legal
    • Proclamations (አዋጅ)
    • Regulations (ደንብ)
    • Directives (መመሪያዎች)
    • Community Complaints
    • Corruption (ሙስና)
  • Tender
    • Auction (ሐራጅ)
    • Land Lease (የመሬት ሊዝ)
    • Request for EOI
  • Project Highlight
  • More
    • Community & CSR
    • Construction & Projects
    • Construction Material Supply
    • Design & Innovation
    • Public Housing
    • Insights & Profiles
    • Sales & Marketing
    • Property Handover
    • Global
    • Contact Us
No Result
View All Result
Sell, Buy, Rent
  • Home
  • Guides
    • Buying Guide
    • Renting Guide
    • Selling Guide
    • Knowledge Base
  • Mortgage
  • Technology
  • Legal
    • Proclamations (አዋጅ)
    • Regulations (ደንብ)
    • Directives (መመሪያዎች)
    • Community Complaints
    • Corruption (ሙስና)
  • Tender
    • Auction (ሐራጅ)
    • Land Lease (የመሬት ሊዝ)
    • Request for EOI
  • Project Highlight
  • More
    • Community & CSR
    • Construction & Projects
    • Construction Material Supply
    • Design & Innovation
    • Public Housing
    • Insights & Profiles
    • Sales & Marketing
    • Property Handover
    • Global
    • Contact Us
No Result
View All Result
Betegna - ቤተኛ | Ethiopian Housing and Real Estate News & Insights
No Result
View All Result
በአዲስ አበባ የቤት ግብር ማሻሻያ ተግባራዊ እንዳይሆን በፍርድ ቤት ያሳገደው ክስ ምን ይዟል?

በአዲስ አበባ የቤት ግብር ማሻሻያ ተግባራዊ እንዳይሆን በፍርድ ቤት ያሳገደው ክስ ምን ይዟል?

Betegna Team by Betegna Team
March 5, 2025
in Legal Updates
A A
0
0
SHARES
Share on FacebookShare on LinkedIn

ተቃዋሚው እናት ፓርቲ የቤት ግብር ማሻሻያን በተመለከተ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ ላይ የመሠረተውን ክስ መርታቱን ተከትሎ ውሳኔውን ለማስፈጸም መዝገብ እንደሚከፍት አስታወቀ።

ጉዳዩን ሲመለከተው የነበረው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የፌደራል አስተዳደር ሥነ ሥርዓት ፍትሐ ብሔር ችሎት “መመሪያው ተፈጻሚነት ሊኖረው አይገባም” ተብሎ መመሪያው እንዲሻር በሙሉ ድምጽ ውሳኔ ያስተላለፈው ጥር 9/2017 ዓ.ም. ነበር።

በዚሁ ዕለት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ሌሊሴ ደሳለኝ የዕግድ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል። ለ15 ቀናት የቆው የፕሬዝዳንቷ የዕግድ ትዕዛዝ፤ “ውሳኔው ከመፈጸም እና ውሳኔው ላይ ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ እንዳይሰጥ” የከለከለ ነበር።

ይህ የ15 ቀናት ዕግድ መጠናቀቁን ተከትሎ እናት ፓርቲ ሰኞ፣ ጥር 26/2017 ዓ.ም. መግለጫ ሰጥቷል። ፓርቲው በመግለጫው የፍርድ ቤት ውሳኔውን ለማስፈጸም የአፈጻጸም መዝገብ እንደሚከፍት አስታውቋል።

እናት ፓርቲ በክርክር የረታበትን አቤቱታ ለፍርድ ቤት ያቀረበው ከአንድ ዓመት ከሰባት ወራት በፊት ሐምሌ 2015 ዓ.ም. ነው።

ጉዳዩ የቀረበለት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሰጠው ብይን መሠረት አቤቱታውን አሻሽሎ ባለፈው ዓመት ጥቅምት 2016 ዓ.ም ለችሎቱ አቅርቧል።

ፓርቲው ያቀረበው አቤቱታ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ ያወጣው እና “ከሕግ ውጭ ሥራ ላይ የዋለ መመሪያ” እንዲሰረዝ የሚጠይቅ ነው።

አቤቱታው “ወቅቱን ግምት ውስጥ ያስገባ የንብረት ግብር ለማስከፈል” በሚል በቢሮው “የወጣው መመሪያ የሕግ መሠረት የሌለው” መሆኑን ጠቅሷል። ከዚህ በተጨማሪም ቢሮው “እንዲህ ዓይነት መመሪያ እንዲያወጣ በሕግ ሥልጣን ሳይሰጠው ያወጣው መመሪያ” መሆኑን የጠቀሰው ፓርቲው ይህ መመሪያ እንዲሰረዝ ክሱ ጠይቋል።

ለእናት ፓርቲ አቤቱታ ምክንያት የሆነው የአዲስ አበባ ከተማ ፋይናንስ ቢሮ ከሁለት ዓመታት ገደማ በፊት ያቋቋመው የንብረት ግብር ማስተባበሪያ ጊዜያዊ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ያዘጋጀው ጥናት ነው።

ቢሮው ጽህፈት ቤቱን ያቋቋመው በንጉሡ ጊዜ የወጣውን የከተማ ቦታ ኪራይ እና የከተማ ቤት ግብር አዋጅ መሠረት በማድረግ መሆኑን በወቅቱ ገልጾ ነበር።

የከተማዋ ፋይናንስ ቢሮ የፕሮጀክት ጽህፈት ቤቱ የጥናት ውጤት ለሌሎች የከተማ አስተዳደሩ መዋቅሮች በሚያዝያ 5/2015 ዓ.ም. በጻፈው ደብዳቤ አስተላልፏል። ቢሮው በዚህ ደብዳቤ የቤት ግብር ማሻሻያ ተግባራዊ እንዲደረግም ጠይቋል።

እናት ፓርቲ በአቤቱታው ቢሮው መመሪያውን ያስተላለፈው “የመመሪያ አወጣጥ ሥርዓትን ተከትሎ የወጣ አለመሆኑን” ጠቅሷል።

እናት ፓርቲ በአቤቱታው ያቀረበው የመጀመሪያ ፍሬ ነገር ቢሮው ያወጣው መመሪያ “የሕግ መሠረት የለውም” የሚል ነው።

ማንኛውም ተቋም መመሪያ ለማውጣት “በሕግ የተሰጠ ሥልጣን” ሊኖረው እንደሚገባ የጠቆመው የእናት ፓርቲ አቤቱታ ቢሮው መመሪያውን ለማውጣት የጠቀሰው አዋጅ “ስለ ንብረት ግብር የወጣ አይደለም” ብሏል።

ፓርቲው “በኢትዮጵያ የንብረት ግብር ለማስከፈል የወጣ ሕግ በሌለበት ሁኔታ “የንብረት ግብር ማስተባበሪያ ጊዜያዊ ፕሮጀክት ጽ/ቤት የሚባል የሕግ መሠረት አካል አቋቁሞ በማስጠናት የንብረት ግብር እንዲከፈል መመሪያ ማውጣት ፍፁም የሆነ የሕግ ጥሰት ነው” ሲል አቤቱታውን አቅርቧል።

ሁለተኛው የእናት ፓርቲ አቤቱታ ፍሬ ነገር መመሪያ ከማውጣት ሥልጣን ጋር የተያያዘ ነው። አቤቱታው በ1968 የወጣውን አዋጅ ለማስፈጸም የወጣው ደንብ “ማንኛውም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንቡን ለማስፈጸም መመሪያ ማውጣት እንደሚችል አንድም ሥልጣን አልሰጠም” ሲል ፍሬ ነገሩን አስረድቷል።

ፓርቲው በአቤቱታው “ደንቡ ሥልጣን ባልሰጠበት ሁኔታ ለዚያውም የንብረት ግብር እንዲከፈል የሚፈቅድ ሕግ በሌለበት ሁኔታ የንብረት ግብር ለማስከፈል መመሪያ ማውጣት የሕግ መሠረት ስለሌለው መመሪያው እንዲሰረዝ” ሲል ዳኝነት ጠይቋል።

ሦስተኛው የፓርቲው መከራከሪያ ቢሮው ያወጣው መመሪያ በ2012 ዓ.ም. የወጣውን የፌደራል የአስተዳደር ሥነ ሥርዓት አዋጅ ተከትሎ ያልወጣ መሆኑን በመጥቀስ የቀረበ ነው።

አዲስ አበባ ከተማ ፋይናንስ ቢሮ በበኩሉ በፓርቲው ለቀረቡ አቤቱታዎች መልስ ሰጥቷል። ቢሮው በሰጠው መልስ የግብር መጠንን ከ47 ዓመት በኋላ ባለበት አግባብ ማስቀጠል “አሁናዊ እና ነባራዊ አገር አቀፍ ኢኮኖሚ ሁኔታዎች የማይፈቅዱ” መሆኑን ጠቅሷል።

ይህን ተከትሎም የእናት ፓርቲ አቤቱታ “የሕግም ሆነ የማስረጃ ድጋፍ የሌለው ከመሆኑን ባሻገር ተገቢነት ያለው አይደለም። ስለዚህ አቤቱታው ውድቅ ይደረግልን” ሲል ዳኝነት ጠይቋል።

ቢሮው አክሎም አመልካች “እንዲከለስላቸው የሚጠይቁትን መመሪያ ቁጥሩን ጠቅሰው ለፍርድ ቤቱ ያቀረቡት መመሪያ የሌለ መሆኑን” ጠቅሷል።

“በተጠሪ [ፋይናንስ ቢሮ] የወጣ እና ሥራ ላይ የሚገኝ መመሪያ የለም” ያለው ቢሮው፤ “መመሪያው ሊሰረዝ ወይም ሊከለስ ይገባል በማለት የቀረበው ክስ የሕግ መሠረት የሌለው ስለሆነ ውድቅ ይደረግልን” ብሏል።

ግራ ቀኙ የቃል ክርክር ባደረጉበት ወቅትም ቢሮው ይህን መከራከሪያ በአጽንኦት አሰምቷል።

በቃል ክርክሩ ወቅት “ማዘጋጃ ቤታዊ ታሪክ ማሻሻያ የማድረግ ሥልጣን በተሰጠው መሠረት ፋይናንስ ቢሮ ጥናቱን መሠረት አድረጎ [የታሪፍ] ማሻሻያ አደረገ እንጂ አዲስ መመሪያ ወይም የንብረት ግብርን በተመለከተ የሚከፈልበት ታክስ በሌለበት በእኛ በኩል የወጣ መመሪያ የለም” ሲል ተሟግቷል።

የግራ ቀኙን ክርክር የተመለከተው ፍርድ ቤቱም ሦስት ጭብጦችን ይዞ ውሳኔ ሰጥቷል።

የመጀመሪያው ጭብጥ የንብረት ግብር ማስተባበሪያ ጊዜያዊ ፕሮጀክት ጽ/ቤት የወጣው ሰነድ መመሪያ ነው? አይደለም? የሚለው ነው።

ፍርድ ቤቱ ይህን ጭብጥ በተመለከተ የአስተዳደር ሥነ ሥርዓት አዋጁን በመጥቀስ በአስተዳደር ተቋም የሚወጣ እና በሰዎች መብት ወይም ጥቅም ላይ ውጤት የሚያስከትል የሕግ ሰነድ መመሪያ መሆኑን ገልጿል።

ይህን ተከትሎ የጥናት ሰነዱ “ግብር ከፋዮች ግብር እና ታክስ እንዲከፍሉ ግዴታ የጣለ” መሆኑ እንዲሁም “ግብር እና ታክስ ሲከፈል የነበረ” መሆኑን በመጥቀስ፤ “የጥናት ሰነዱ እንደ መመሪያ ካልተቆጠረ በስተቀር ሌላ ትርጉም መስጠት አይቻልም” ሲል ሰነዱ መመሪያ ነው በማለት ደምድሟል።

ሁለተኛው ጭብጥ መመሪያው የመመሪያ አወጣጥ መርሆዎችን ተከትሎ መውጣቱን የተመለከተበት ነው።

ችሎቱ መመሪያው “የሕግ አስተያየት ሳይታከልበት የወጣ ስለሆነ በአጠቃላይ ያልተፈተነ እና የመመሪያ አወጣጥ ሥርዓቱን እና ሕጋዊነቱ ተመርምሮ ያልተመዘገበ ስለሆነ ሕጋዊነቱ እና ተፈጻሚነቱ ጥያቄ ውስጥ የሚገባ ነው” ብሏል።

ሦስተኛው እና የመጨረሻው ጭብጥ የፋይናንስ ቢሮው መመሪያ የማውጣት ሥልጣን ላይ ያተኮረ ነው። ችሎቱ ይህን ጭብጥ በተመለከተ “ተጠሪ [የፋይናንስ ቢሮ] መመሪያ በማውጣት ሥራ ላይ እንዲውል ማድረጉ ከሥልጣን ገደቡ ውጪ እና ያለ ሕግ መሠረት የወጣ መመሪያ መሆኑን መገንዘብ ይችላል” ብሏል።

ይህን ተከትሎ በሦስት ዳኞች የተሰየመው ችሎት “በፋይናንስ ቢሮ በኩል ወደ ተግባር እንዲለወጥ የተጻፈው የንብረት ግብር ማሻሻያ ጥናት ሰነዱ በፍርድ ቤቱ መመሪያ መሆኑ” መረጋገጡን አስታውሷል።

በመሆኑም “መመሪያው ተፈጻሚነት ሊኖረው አይገባም” ተብሎ መመሪያው እንዲሻር በሙሉ ድምጽ ውሳኔ ሰጥቷል።

ምንጭ፡ BBC Amharic

Tags: Addis Ababa City administrationAddis Ababa Property TaxEnat PartyFederal High CourtProperty TaxSupreme Court Ethiopia
Previous Post

በሱፍቃድ ሪልእስቴት ለመቄዶኒያ የ 4 ሚሊዮን ብር ቤት አበረከተ

Next Post

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የ5ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ: ማስታወቂያ

Betegna Team

Betegna Team

Betegna - ቤተኛ, is a media platform that focuses on Ethiopian housing and real estate news, developments, technology, policies, and lifestyle.

ተዛማጅ ጽሑፎች

በጋዜቦ አደባባይ አካባቢ በግንባታ ሂደት ላይ ከነበረ ሕንጻ ላይ የወደቁ ሦስት ሠራተኞች ሕይወታቸውን አጡ
Legal Updates

በጋዜቦ አደባባይ አካባቢ በግንባታ ሂደት ላይ ከነበረ ሕንጻ ላይ የወደቁ ሦስት ሠራተኞች ሕይወታቸውን አጡ

November 14, 2026
የመሬት ይዞታ ደንብ ማሻሻያ እና የልማት ፕሮጀክቶች መሬት ምደባ ጸደቁ
Legal Updates

የመሬት ይዞታ ደንብ ማሻሻያ እና የልማት ፕሮጀክቶች መሬት ምደባ ጸደቁ

October 27, 2026
በ2015 ዓ.ም ወደ መሬት ባንክ በገባ ይዞታ ላይ የቀረቡ ቅሬታዎችን ለመፍታት አዲስ የአሰራር ስርዓት ተዘረጋ
Legal Updates

በ2015 ዓ.ም ወደ መሬት ባንክ በገባ ይዞታ ላይ የቀረቡ ቅሬታዎችን ለመፍታት አዲስ የአሰራር ስርዓት ተዘረጋ

September 28, 2026
Next Post

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የ5ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ: ማስታወቂያ

  • Trending
  • Comments
  • Latest
የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የወጣ አዋጅ 721/2004

የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የወጣ አዋጅ 721/2004

April 23, 2024
ስለ ግብር የሚከፈልበት የቤት ኪራይ ገቢ

ስለ ግብር የሚከፈልበት የቤት ኪራይ ገቢ

April 6, 2024
በአዲስ አበባ የቤት ሽያጭ ዋጋ ተመን ላይ በድጋሚ ማሻሻያ ተደረገ

በአዲስ አበባ የቤት ሽያጭ ዋጋ ተመን ላይ በድጋሚ ማሻሻያ ተደረገ

April 3, 2024
የመሬት ልማትና አስተዳር ደንብ ቁጥር 163/2016

የመሬት ልማትና አስተዳር ደንብ ቁጥር 163/2016

April 22, 2024
ስለ ሪል እስቴት ምን ያውቃሉ?

ስለ ሪል እስቴት ምን ያውቃሉ?

August 18, 2023
Home pic

ቤት ለሚገዙ እና ለሚሸጡ አካላት ማሳሰቢያ ተሰጠ

0
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤት አቅርቦትን ለማሳደግ የሚያስችል ውይይት ከሪል እስቴት አልሚዎች ጋር ውይይት አደረገ!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤት አቅርቦትን ለማሳደግ የሚያስችል ውይይት ከሪል እስቴት አልሚዎች ጋር ውይይት አደረገ!

0
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ያስተዋወቀበትን የገርጂ መኖሪያ መንደር ፕሮጀክት ሊያስመርቅ ነው

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ያስተዋወቀበትን የገርጂ መኖሪያ መንደር ፕሮጀክት ሊያስመርቅ ነው

0
ባለ 9 ወለል ህንፃ በተጀመረ በ69ኛ ቀኑ ተጠናቀቀ!!

ባለ 9 ወለል ህንፃ በተጀመረ በ69ኛ ቀኑ ተጠናቀቀ!!

0
ስለ ሪል እስቴት ምን ያውቃሉ?

ስለ ሪል እስቴት ምን ያውቃሉ?

0
የሪል እስቴት አልሚዎች ማህበር የ7% የብድር ወለድ ጥያቄ በባለሙያዎች መካከል ያስነሳው ክርክር

የሪል እስቴት አልሚዎች ማህበር የ7% የብድር ወለድ ጥያቄ በባለሙያዎች መካከል ያስነሳው ክርክር

November 18, 2026
በጋዜቦ አደባባይ አካባቢ በግንባታ ሂደት ላይ ከነበረ ሕንጻ ላይ የወደቁ ሦስት ሠራተኞች ሕይወታቸውን አጡ

በጋዜቦ አደባባይ አካባቢ በግንባታ ሂደት ላይ ከነበረ ሕንጻ ላይ የወደቁ ሦስት ሠራተኞች ሕይወታቸውን አጡ

November 14, 2026
በ5 ዓመታት ቤቶችን ገንብተን ለማስረከብ የገባነውን ቃል በተግባር ለማረጋገጥ እየተጋን ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

በ5 ዓመታት ቤቶችን ገንብተን ለማስረከብ የገባነውን ቃል በተግባር ለማረጋገጥ እየተጋን ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

November 13, 2026
የ1.5 ሚሊዮን መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት ወደ ተግባር ምዕራፍ ተሸጋግሯል

የ1.5 ሚሊዮን መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት ወደ ተግባር ምዕራፍ ተሸጋግሯል

November 12, 2026
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከዩኤን ሃቢታት ዋና ዳይሬክተር አናክላውዲያ ሮስባክ ጋር መወያየታቸውን ገለፁ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከዩኤን ሃቢታት ዋና ዳይሬክተር አናክላውዲያ ሮስባክ ጋር መወያየታቸውን ገለፁ

November 11, 2026

ብዙ የተነበቡ

  • የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የወጣ አዋጅ 721/2004

    የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የወጣ አዋጅ 721/2004

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ስለ ግብር የሚከፈልበት የቤት ኪራይ ገቢ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአዲስ አበባ የቤት ሽያጭ ዋጋ ተመን ላይ በድጋሚ ማሻሻያ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የመሬት ልማትና አስተዳር ደንብ ቁጥር 163/2016

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ስለ ሪል እስቴት ምን ያውቃሉ?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Categories

  • Community & CSR (28)
  • Construction & Projects (29)
  • Construction Material Supply (9)
  • Design & Innovation (18)
    • Architecture (2)
    • Technology (14)
  • Global (4)
  • Insights & Profiles (20)
  • Legal Updates (89)
    • Community Complaints (8)
    • Corruption (ሙስና) (2)
    • Directives (መመሪያዎች) (1)
    • Proclamations (አዋጅ) (7)
    • Regulations (ደንብ) (2)
  • Mortgages & Finance (14)
  • Property Handover (16)
  • Public Housing (71)
  • Real Estate Guides (13)
    • Buying Guide (3)
    • Knowledge Base (1)
    • Renting Guide (2)
    • Selling Guide (7)
  • Sales & Marketing (67)
  • Tenders & Bids (60)
    • Land Lease (29)
    • Request for EOI (1)
  • Home
  • Guides
  • Mortgage
  • Highlights
  • Legal Updates
  • Tenders & Bids
Betegna Logo Footer

Betegna – ቤተኛ, powered by Betbegara.com, is a media platform that focuses on Ethiopian housing and real estate news, developments, technology, policies, and lifestyle.

© 2026 Betegna – ቤተኛ | Ethiopian Housing and Real Estate News & Insights

  • Home
  • Guides
    • Buying Guide
    • Renting Guide
    • Selling Guide
    • Knowledge Base
  • Mortgage
  • Technology
  • Legal
    • Proclamations (አዋጅ)
    • Regulations (ደንብ)
    • Directives (መመሪያዎች)
    • Community Complaints
    • Corruption (ሙስና)
  • Tender
    • Auction (ሐራጅ)
    • Land Lease (የመሬት ሊዝ)
    • Request for EOI
  • Project Highlight
  • More
    • Community & CSR
    • Construction & Projects
    • Construction Material Supply
    • Design & Innovation
    • Public Housing
    • Insights & Profiles
    • Sales & Marketing
    • Property Handover
    • Global
    • Contact Us
No Result
View All Result
Sell, Buy, Rent