ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከ500 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመተው “ዝማምነሽ ታወር” ከወይዘሮ አፀደወይን በቀለ በሥጦታ ተበረከተለት

ዩኒቨርሲቲው የ60ኛ ዓመት ክብረ በዓሉን ሲያከብር ሕዝቡ ተቋሙን ለመደገፍ ትብበር ሊያደርግ እንደሚገባ ያስተላለፈውን መልዕክት ምክንያት በማድረግ የተለያዩ ማኅበረሰብ ክፍሎች ድጋፋቸውን እያበረከቱለት ነው።

ከደጋፊዎቹ መካከል ደግሞ ወይዘሮ አፀደወይን በቀለ እና ቤተሰቦቻቸው ቀዳሚዎቹ ናቸው።

በባሕር ዳር ከተማ ተወልደው ያደጉት ወይዘሮ አፀደወይን በቀለ በባሕር ዳር ከተማ የሚገኘውን እና ከእናታቸው ወይዘሮ ዝማምነሽ ወልደየሱስ በውርስ ያገኙትን ከ500 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመተውን ዙማምነሽ ታወር ለባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በስጦታ አበርክተዋል።

ስጦታውን ለመስጠት ያነሣሣቸውም ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በጤናው ዘርፍ የሚሰጠውን አገልግሎት ለመደገፍ መሆኑን የወይዘሮ አፀደወይን ቤተሰቦች ተናግረዋል።

ስጦታውን የተረከቡት የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ፍሬው ተገኘ፣ ዩኒቨርሲቲው ትልቅ ኃላፊነት እንዳለበት በመገንዘብ ነው ብለዋል።

ማኅበረሰቡ ያለውን ሃብት ለሕዝብ አገልግሎት ለሚሰጡ ተቋማት በማካፈል ተቋማት ሰፊ አገልግሎት እንዲሰጡ መደገፍ እንዳለበትም አሳስበዋል።

ለሀገር እና ለወገን ተጠቃሚነት በሚደረገው የልማት ሥራ ከወይዘሮ አፀደወይን ቤተሰብ ትምህርት በመውሰድ ሁሉም ትብብሩን አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ፍሬው ተገኘ መጥቀሳቸውን ከዩኒቨርሲቲው የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በስጦታ የተበረከተለት ዝማምነሽ ታወር በባሕር ዳር ከተማ ጊዮርጊስ አካባቢ አወርስ ካፌ /አወርስ ገስት ሐውስ/ እንዲሁም የተለዩ መሰል የቢዝነስ ማዕከልነት በማገልገል ላይ የሚገኘው ሕንፃ ነው።

Source: አሚኮ

Share to your Network:

16 thoughts on “ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከ500 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመተው “ዝማምነሽ ታወር” ከወይዘሮ አፀደወይን በቀለ በሥጦታ ተበረከተለት”

 1. Pingback: how often can i take tizanidine 4mg

 2. Pingback: protonix davis pdf

 3. Pingback: synthroid complications

 4. Pingback: sitagliptin for

 5. Pingback: no period on spironolactone reddit

 6. Pingback: voltaren gel and warfarin interactions

 7. Pingback: tamsulosin 0.4mg for women

 8. Pingback: abilify injection dosage

 9. Pingback: robaxin side effects dogs

 10. Pingback: how long does amitriptyline take to work

 11. Pingback: duloxetine vs venlafaxine

 12. Pingback: actos esotericos

 13. Pingback: repaglinide sulfonylurea

 14. Pingback: stromectol coronavirus

 15. Pingback: gluconase acarbose

 16. Pingback: remeron serotonin

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *