• BetBegara.com
  • Buy
  • Rent
  • Sale
  • Services
  • Contact Us
Betegna - ቤተኛ | Ethiopian Housing and Real Estate News & Insights
Advertisement
  • Home
  • Guides
    • Buying Guide
    • Renting Guide
    • Selling Guide
    • Knowledge Base
  • Mortgage
  • Technology
  • Legal
    • Proclamations (አዋጅ)
    • Regulations (ደንብ)
    • Directives (መመሪያዎች)
    • Community Complaints
    • Corruption (ሙስና)
  • Tender
    • Auction (ሐራጅ)
    • Land Lease (የመሬት ሊዝ)
    • Request for EOI
  • Project Highlight
  • More
    • Community & CSR
    • Construction & Projects
    • Construction Material Supply
    • Design & Innovation
    • Public Housing
    • Insights & Profiles
    • Sales & Marketing
    • Property Handover
    • Global
    • Contact Us
No Result
View All Result
Sell, Buy, Rent
  • Home
  • Guides
    • Buying Guide
    • Renting Guide
    • Selling Guide
    • Knowledge Base
  • Mortgage
  • Technology
  • Legal
    • Proclamations (አዋጅ)
    • Regulations (ደንብ)
    • Directives (መመሪያዎች)
    • Community Complaints
    • Corruption (ሙስና)
  • Tender
    • Auction (ሐራጅ)
    • Land Lease (የመሬት ሊዝ)
    • Request for EOI
  • Project Highlight
  • More
    • Community & CSR
    • Construction & Projects
    • Construction Material Supply
    • Design & Innovation
    • Public Housing
    • Insights & Profiles
    • Sales & Marketing
    • Property Handover
    • Global
    • Contact Us
No Result
View All Result
Betegna - ቤተኛ | Ethiopian Housing and Real Estate News & Insights
No Result
View All Result
ነባር ተመዝጋቢዎች እያሉ የኮንዶሚኒየም ቤቶች ለልማት ተነሽዎች መሰጠታቸው ቅሬታ አስነሳ

ነባር ተመዝጋቢዎች እያሉ የኮንዶሚኒየም ቤቶች ለልማት ተነሽዎች መሰጠታቸው ቅሬታ አስነሳ

Betegna Team by Betegna Team
September 29, 2024
in Community Complaints
A A
0
0
SHARES
Share on FacebookShare on LinkedIn

ለ21 ዓመታት ኮንዶሚኒየም ይደርሰናል ብለው ሲቆጥቡ የቆዩ የኮንዶሚኒየም ነባር ተመዝጋቢዎች ዕጣ ሳይወጣላቸው፣ ቤቶቹ ለልማት ተነሽዎች በመሰጠታቸው ቅሬታ አቀረቡ፡፡

ከ1997 ዓ.ም. ጀምሮ የኮንዶሚኒየም ቤቶችን በዕጣ ለማግኘት ሲጠባበቁ የቆዩ በርካታ ተመዝጋቢዎች እያሉ፣ ለልማት ተነሽዎች ቤቶች መሰጠታቸው ኢፍትሐዊ እንደሆነ ቅሬታ አቅራቢዎቹ ገልጸዋል፡፡

ለልማት ተነሽዎች ለምን ቤት ተሰጣቸው እንደማይሉ የተናገሩት ቅሬታ አቅራቢዎቹ፣ ለረዥም ዓመታት ፍትሐዊነት በጎደለው መንገድ ለእነሱ ሳይሰጣቸው መቅረቱ እንዳሳዘናቸው አሳድረዋል፡፡ ለልማት ተብሎ ቤታቸው የፈረሰባው ዜጎች ቤት ሲሰጣቸው የ1997 እና የ2005 ዓ.ም. የኮንዶሚኒየም ቤቶች ተመዝጋቢዎች ጉዳይ በዝምታ መታለፉ ቅሬታ እንደፈጠረባቸው ገልጸዋል፡፡

የኮንዶሚኒየም ቤቶች ግንባታ እስኪያልቅ ድረስ ለምን በመንግሥት የተሠሩ ቤቶች አይሰጡንም ያሉት ተመዝጋቢዎቹ፣ ለሁለት አሥርት ዓመታት ቤት ለማግኘት በመጠበቃቸው በተለየ ሁኔታ በከተማ አስተዳደሩ ሊስተናገዱ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

በአሁኑ ጊዜ የቤት ኪራይና የልጆች ትምህርት ቤት ክፍያዎች ጣራ በመንካታቸው፣ ለችግር ተዳርገናል ያሉት ተመዝጋቢዎች፣ የኢትዮጵያ ዜጋ አይደለንም ወይ ሲሉም ቅሬታቸውን አሰምተዋል፡፡

ለዓመታት ምላሽ በተነፈገው ጥያቄያቸው ምክንያት በመንግሥት ላይ ያላቸው እምነት መሟጠጡን ገልጸዋል፡፡

ተመዝጋቢዎቹ ለሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም፣ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን፣ ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤትና ሌሎች ተቋማት ቅሬታቸውን ቢያሰሙም እስካሁን መፍትሔ እንዳላገኙ አክለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሽመልስ ታምራት እንደተናገሩት፣ አጠቃላይ የቤቶች ግንባታ ከሁለትና ከሦስት ዓመት ተኩል በኋላ የብድር አቅርቦት ችግር ተጨማሪ ግንባታ ማድረግ አላስቻለም፡፡

ችግሩ እስኪፈታ ድረስ ግንባታ እንደማይካሄድ፣ ኮርፖሬሽኑ ያለበትን ውዝፍ ዕዳ እስኪከፈል ድረስም ሲያገኝ የነበረው ብድር መከልከሉን ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

ኮርፖሬሽኑ ካለበት ዕዳ ውስጥ 36 ቢሊዮን ብር ተመላሽ ማድረጉን ገልጸው፣ ቀሪ 37.7 ቢሊዮን ብር ያልተከፈለ ውዝፍ ዕዳ እንዳለበትና ለመክፈልም የተለያዩ አማራጮችን እያጤነ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብድር የሚሰጠው ለማጠናቀቂያ ሥራ ብቻ እንደሆነ፣ ለሰፊ የቤት ግንባታ ግን ተጨማሪ ብድር እንደማይሰጥ ጠቁመዋል፡፡

ዕጣ ያልወጣላቸው የኮንዶሚኒየም ተመዝጋቢዎች እያሉ ለምን ለሌሎች ይሰጣል ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፣ ለልማት ተነሽዎች ቅድሚያ መስጠትን መመርያው የሚያዝና የሚደግፈው መሆኑን ገልጸው፣ ነገር ግን የኮንዶሚኒየም ዕጣ ጠባቂዎችን ወደ ጎን ከመግፋት ጋር መገናኘት የለበትም ብለዋል፡፡

የቤት አቅርቦት ጉዳይ የ1997 እና የ2005 ዓ.ም. የቤት ተመዝጋቢዎች ችግር ብቻ ሳይሆን፣ በአጠቃላይ በቤት አቅርቦቱ በአማራጭ የቤት ልማት ላይ እየተሠሩ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡

ከተለመዱት 40/60 እና 20/80 ቤቶች በተጨማሪ በ70/30 ፕሮግራምና በማኅበር ቤቶች አቅም ያላቸው እንዲገነቡ የሚያስችል አሠራር መዘርጋቱን ተናግረዋል፡፡

ኮርፖሬሽኑ እስካሁን የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ሲገነባ የነበረው በቦንድ ግዥ እንደነበረ፣ አሁን ግን የከተማ አስተዳደሩ ካለው በጀት ላይ እየመደበ ብድሩን እየከፈለና ለኪራይ የሚሆኑ ቤቶች እየገነባ ነው ብለዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ መንግሥትና ባለሀብቶች ተቀናጅተው የሚገነቧቸው ቤቶች መኖራቸውንና ለዝቅተኛ የኅብረተሰብ ክፍሎች እየተሰጡ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

የኮንዶሚኒየም ተመዝጋቢዎችን በተመለከተ ቁጠባ ያቋረጡ እንዳሉ ገልጸው፣ “ነገር ግን አሁንም ኮንዶሚኒየም ተመዝጋቢዎች የሉም ወይም ጨርሰን ሰጥተናል አላልንም” ብለዋል፡፡

የኮንዶሚኒየም ተመዝጋቢዎች ቅሬታ ትክክል መሆኑን የገለጹት አቶ ሽመልስ፣ ነገር ግን ከተማው ያለበትን የቤት አቅርቦት ችግር ሲፈታ የተመዝጋቢዎቹን ችግርም በዚያው እንደሚፈታ ገልጸዋል፡፡

“የነባሩ የዕጣ አወጣጥ ሒደት ቆሟል ወይም አልቆመም ብለን መናገር አንችልም” ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፣ ምናልባት የባንክ ብድር ከተመለሰ እንደገና በሌላ ብድር ቤቶች ተገንብተው ለዕጣ ጠባቂዎች ለመስጠት ጥረት እንደሚደረግ ጠቁመዋል፡፡ የተመዝጋቢዎች ዕጣ የማውጣት ሒደት ይቀጥላል ወይም አይቀጥልም የሚለው በቤት አቅርቦት ሁኔታው እንደሚወሰን ገልጸዋል፡፡

እንደ አቶ ሽመልስ ገለጻ፣ ከኮሪደር ልማት ተነሺዎች በአንድም በሌላም መንገድ ቢጣራ ተመዝጋቢዎች አሉ፡፡ ለኮሪደር ልማት ተነሽዎች የ40/60 እና የ20/80 ቤቶች ተሰጥተው አልቀው ወደ ኪራይ ቤት እየተገባ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም የሕግና የአስተዳደር በደል ምርመራ መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ መንግሥቱ ቀና በበኩላቸው፣ በ1997 ዓ.ም. ኮንዶሚኒየም ለማግኘት ተመዝግበው ዕጣ ያልወጣላቸውን በተመለከተ ኮርፖሬሽኑን በደብዳቤ መጠየቁን ገልጸዋል፡፡

ይሁን እንጂ በተደጋጋሚ ጥያቄ ቢቀርብም ምላሽ አለመገኘቱን አቶ መንግሥቱ ገልጸው፣ እንደገና በደብዳቤ ተጠይቆም ምላሽ ካልተገኘ ወደ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለማምራት መታቀዱን ተናግረዋል፡፡

“ኮርፖሬሽኑ ለኮንዶሚኒየም ተመዝጋቢዎች ዕጣ ያላወጣበት ምክንያት ይህ ነው ብለው ስላልነገረን ተጨማሪ ምርመራ ለማድረግ አልቻልንም” ብለዋል፡፡ ጉዳዩ ገና በሒደት ላይ እንደሚገኝና ለከተማ አስተዳደሩ ደብዳቤዎች እየተጻፉ መሆናቸውንና በሚፈለገው ልክ ምላሽ ካልተገኘ ግን ወደ ፓርላማ እንደሚያመሩ አስረድተዋል፡፡

የተመዝጋቢዎቹ ችግር ከዓመት ዓመት እየተላለፈ ያለ ችግር መሆኑን፣ ዜጎች ምላሽ እንዲያገኙ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሥራ መጀመርን ተቋማቸው እየተጠባበቀ እንደሚገኝ አቶ መንግሥቱ ገልጸዋል፡፡

ምንጭ፦ ሪፖርተር

Tags: Addis Ababa housingCondominiumcondominium allocationCorridorhousing complaintshousing developmentreal estate Ethiopia
Previous Post

ብዙአየሁ ታደለና ቤተሰቡ ፋውንዴሽን አነስተኛ ገቢ ላላቸው ነዋሪዎች በ50 ሚሊዮን ብር ያስገነባውን መኖሪያ ሕንጻ አስመረቀ

Next Post

በሙስና ወንጀል በተጠረጠሩት የፐርፐዝ ብላክ የቦርድ አስፈጻሚዎች ላይ ክስ መመስረቻ ጊዜ ተፈቀደ

Betegna Team

Betegna Team

Betegna - ቤተኛ, is a media platform that focuses on Ethiopian housing and real estate news, developments, technology, policies, and lifestyle.

ተዛማጅ ጽሑፎች

በኖህ ሪል እስቴት እና በቤት ገዢዎች መካከል ያለው አለመግባባት ወደ ፍርድ ቤት አመራ
Community Complaints

በኖህ ሪል እስቴት እና በቤት ገዢዎች መካከል ያለው አለመግባባት ወደ ፍርድ ቤት አመራ

July 21, 2026
ፍሊንትስቶንስ ለደንበኞቹ ከ282 ሚሊዮን ብር በላይ ካሳ እንዲከፍል ተወሰነ
Community Complaints

ፍሊንትስቶንስ ለደንበኞቹ ከ282 ሚሊዮን ብር በላይ ካሳ እንዲከፍል ተወሰነ

July 18, 2026
ኖህ ሪል እስቴት በቤት ገዥ ደንበኞቹ ቅሬታ ቀረበበት
Community Complaints

ኖህ ሪል እስቴት በቤት ገዥ ደንበኞቹ ቅሬታ ቀረበበት

May 28, 2026
Next Post
የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን

በሙስና ወንጀል በተጠረጠሩት የፐርፐዝ ብላክ የቦርድ አስፈጻሚዎች ላይ ክስ መመስረቻ ጊዜ ተፈቀደ

  • Trending
  • Comments
  • Latest
የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የወጣ አዋጅ 721/2004

የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የወጣ አዋጅ 721/2004

April 23, 2024
ስለ ግብር የሚከፈልበት የቤት ኪራይ ገቢ

ስለ ግብር የሚከፈልበት የቤት ኪራይ ገቢ

April 6, 2024
በአዲስ አበባ የቤት ሽያጭ ዋጋ ተመን ላይ በድጋሚ ማሻሻያ ተደረገ

በአዲስ አበባ የቤት ሽያጭ ዋጋ ተመን ላይ በድጋሚ ማሻሻያ ተደረገ

April 3, 2024
የመሬት ልማትና አስተዳር ደንብ ቁጥር 163/2016

የመሬት ልማትና አስተዳር ደንብ ቁጥር 163/2016

April 22, 2024
ስለ ሪል እስቴት ምን ያውቃሉ?

ስለ ሪል እስቴት ምን ያውቃሉ?

August 18, 2023
Home pic

ቤት ለሚገዙ እና ለሚሸጡ አካላት ማሳሰቢያ ተሰጠ

0
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤት አቅርቦትን ለማሳደግ የሚያስችል ውይይት ከሪል እስቴት አልሚዎች ጋር ውይይት አደረገ!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤት አቅርቦትን ለማሳደግ የሚያስችል ውይይት ከሪል እስቴት አልሚዎች ጋር ውይይት አደረገ!

0
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ያስተዋወቀበትን የገርጂ መኖሪያ መንደር ፕሮጀክት ሊያስመርቅ ነው

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ያስተዋወቀበትን የገርጂ መኖሪያ መንደር ፕሮጀክት ሊያስመርቅ ነው

0
ባለ 9 ወለል ህንፃ በተጀመረ በ69ኛ ቀኑ ተጠናቀቀ!!

ባለ 9 ወለል ህንፃ በተጀመረ በ69ኛ ቀኑ ተጠናቀቀ!!

0
ስለ ሪል እስቴት ምን ያውቃሉ?

ስለ ሪል እስቴት ምን ያውቃሉ?

0
የሪል እስቴት አልሚዎች ማህበር የ7% የብድር ወለድ ጥያቄ በባለሙያዎች መካከል ያስነሳው ክርክር

የሪል እስቴት አልሚዎች ማህበር የ7% የብድር ወለድ ጥያቄ በባለሙያዎች መካከል ያስነሳው ክርክር

November 18, 2026
በጋዜቦ አደባባይ አካባቢ በግንባታ ሂደት ላይ ከነበረ ሕንጻ ላይ የወደቁ ሦስት ሠራተኞች ሕይወታቸውን አጡ

በጋዜቦ አደባባይ አካባቢ በግንባታ ሂደት ላይ ከነበረ ሕንጻ ላይ የወደቁ ሦስት ሠራተኞች ሕይወታቸውን አጡ

November 14, 2026
በ5 ዓመታት ቤቶችን ገንብተን ለማስረከብ የገባነውን ቃል በተግባር ለማረጋገጥ እየተጋን ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

በ5 ዓመታት ቤቶችን ገንብተን ለማስረከብ የገባነውን ቃል በተግባር ለማረጋገጥ እየተጋን ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

November 13, 2026
የ1.5 ሚሊዮን መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት ወደ ተግባር ምዕራፍ ተሸጋግሯል

የ1.5 ሚሊዮን መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት ወደ ተግባር ምዕራፍ ተሸጋግሯል

November 12, 2026
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከዩኤን ሃቢታት ዋና ዳይሬክተር አናክላውዲያ ሮስባክ ጋር መወያየታቸውን ገለፁ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከዩኤን ሃቢታት ዋና ዳይሬክተር አናክላውዲያ ሮስባክ ጋር መወያየታቸውን ገለፁ

November 11, 2026

ብዙ የተነበቡ

  • የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የወጣ አዋጅ 721/2004

    የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የወጣ አዋጅ 721/2004

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ስለ ግብር የሚከፈልበት የቤት ኪራይ ገቢ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአዲስ አበባ የቤት ሽያጭ ዋጋ ተመን ላይ በድጋሚ ማሻሻያ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የመሬት ልማትና አስተዳር ደንብ ቁጥር 163/2016

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ስለ ሪል እስቴት ምን ያውቃሉ?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Categories

  • Community & CSR (28)
  • Construction & Projects (29)
  • Construction Material Supply (9)
  • Design & Innovation (18)
    • Architecture (2)
    • Technology (14)
  • Global (4)
  • Insights & Profiles (20)
  • Legal Updates (89)
    • Community Complaints (8)
    • Corruption (ሙስና) (2)
    • Directives (መመሪያዎች) (1)
    • Proclamations (አዋጅ) (7)
    • Regulations (ደንብ) (2)
  • Mortgages & Finance (14)
  • Property Handover (16)
  • Public Housing (71)
  • Real Estate Guides (13)
    • Buying Guide (3)
    • Knowledge Base (1)
    • Renting Guide (2)
    • Selling Guide (7)
  • Sales & Marketing (67)
  • Tenders & Bids (60)
    • Land Lease (29)
    • Request for EOI (1)
  • Home
  • Guides
  • Mortgage
  • Highlights
  • Legal Updates
  • Tenders & Bids
Betegna Logo Footer

Betegna – ቤተኛ, powered by Betbegara.com, is a media platform that focuses on Ethiopian housing and real estate news, developments, technology, policies, and lifestyle.

© 2026 Betegna – ቤተኛ | Ethiopian Housing and Real Estate News & Insights

  • Home
  • Guides
    • Buying Guide
    • Renting Guide
    • Selling Guide
    • Knowledge Base
  • Mortgage
  • Technology
  • Legal
    • Proclamations (አዋጅ)
    • Regulations (ደንብ)
    • Directives (መመሪያዎች)
    • Community Complaints
    • Corruption (ሙስና)
  • Tender
    • Auction (ሐራጅ)
    • Land Lease (የመሬት ሊዝ)
    • Request for EOI
  • Project Highlight
  • More
    • Community & CSR
    • Construction & Projects
    • Construction Material Supply
    • Design & Innovation
    • Public Housing
    • Insights & Profiles
    • Sales & Marketing
    • Property Handover
    • Global
    • Contact Us
No Result
View All Result
Sell, Buy, Rent