በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማት እና አስተዳደር ቢሮ የተዘረጋው የዲጂታል አገልግሎት አሰጣጥ ስርዓት በዘርፉ የሚታየውን ብልሹ አሰራር እና የተገልጋይ እንግልት ለመቅረፍ የሚያስችል መሆኑን ከንቲባ ወ/ሮ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናገሩ፡፡
ዘርፉ ላይ ያለውን የባለ ጉዳይ እንግልት እና ብልሹ አሰራሮችን የሚያስቀር እንዲሁም ለተገልጋዮች ቀላልና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል የዲጂታላይዜሽን ስርዓት በልፅጎ ለአገልግሎት ዝግጁ መሆኑን ገልፀዋል።

የዲጂታላይዜሽን ስራው ከማዕከል እስከ ክፍለ ከተሞች ያለውን መሬት በአንድ ማዕከል እንድናስተዳድር አቅም የሚፈጥርልን ሲሆን ሲስትሙ በየደረጃ ያለውን አገልግሎት ክትትል ለማድረግ እና ለተገልጋዮች ፍትሃዊ እና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት ያስችላል ብለዋል።
የአዲስ አበባ የመሬት ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ አቶ ሲሳይ ጌታቸው አዲሱ የመሬት ዘርፍ አገልግሎት አሰጣጥ ሥራዓት ከሁለት ሳምንት በኋላ ወደ ሙሉ ትግበራ እንደሚገባ ገልፀዋል።


















