• BetBegara.com
  • Buy
  • Rent
  • Sale
  • Services
  • Contact Us
Betegna - ቤተኛ | Ethiopian Housing and Real Estate News & Insights
Advertisement
  • Home
  • Guides
    • Buying Guide
    • Renting Guide
    • Selling Guide
    • Knowledge Base
  • Mortgage
  • Technology
  • Legal
    • Proclamations (አዋጅ)
    • Regulations (ደንብ)
    • Directives (መመሪያዎች)
    • Community Complaints
    • Corruption (ሙስና)
  • Tender
    • Auction (ሐራጅ)
    • Land Lease (የመሬት ሊዝ)
    • Request for EOI
  • Project Highlight
  • More
    • Community & CSR
    • Construction & Projects
    • Construction Material Supply
    • Design & Innovation
    • Public Housing
    • Insights & Profiles
    • Sales & Marketing
    • Property Handover
    • Global
    • Contact Us
No Result
View All Result
Sell, Buy, Rent
  • Home
  • Guides
    • Buying Guide
    • Renting Guide
    • Selling Guide
    • Knowledge Base
  • Mortgage
  • Technology
  • Legal
    • Proclamations (አዋጅ)
    • Regulations (ደንብ)
    • Directives (መመሪያዎች)
    • Community Complaints
    • Corruption (ሙስና)
  • Tender
    • Auction (ሐራጅ)
    • Land Lease (የመሬት ሊዝ)
    • Request for EOI
  • Project Highlight
  • More
    • Community & CSR
    • Construction & Projects
    • Construction Material Supply
    • Design & Innovation
    • Public Housing
    • Insights & Profiles
    • Sales & Marketing
    • Property Handover
    • Global
    • Contact Us
No Result
View All Result
Betegna - ቤተኛ | Ethiopian Housing and Real Estate News & Insights
No Result
View All Result
በኢትዮጵያ ቤቶች እየተገነቡበት ነው የተባለው ‘ስሪዲ’ ቴክኖሎጂ ምንድን ነው?

በኢትዮጵያ ቤቶች እየተገነቡበት ነው የተባለው ‘ስሪዲ’ ቴክኖሎጂ ምንድን ነው?

Betegna Team by Betegna Team
June 12, 2026
in Technology
A A
0
0
SHARES
Share on FacebookShare on LinkedIn

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ሰኔ 2/2018 ዓ.ም. ዘመናዊ እና ፈጣን ቴክኖሎጂን በመጠቀም የሚገነቡ ቤቶች ፕሮጀክትን መጎብኘታቸውን በማኅበራዊ ድረ ገጻቸው ላይ አጋርተዋል።

በጉብኝታቸው ወቅት ጎልቶ የታየው የስሪዲ ቴክኖሎጂ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህ አዲስ ቴክኖሎጂ ቤቶችን በወራት እና በዓመታት ሳይሆን በቀናት ውስጥ “በፍጥነት እና በጥራት” ገንብቶ የሚጨርስ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከካቢኔ አባላቶቻቸው ጋር ሆነው በጎበኝዋቸው የስሪዲ ዘመናዊ ቤቶች ማምረቻ ስፍራዎች ለተገጣጣሚ ቤቶች የሚያገለግሉ የሕንጻ የተለያዩ ክፍሎች የሚመረቱበት ስፍራ ነው።

በእነዚህ የስሪዲ ኮንስትራክሽን የሚመረቱ ቤቶች “ጥራት ያላቸው ቤቶች በቀናት እና በሳምንታት ውስጥ” ገንብቶ ማስረከብ እንደሚቻል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ ጽፈዋል።

ስሪዲ የግንባታ ቴክኖሎጂ ምንድን ነው? በርግጥ በቀናት ውስጥ ቤት ሰርቶ ያስረክባል ሲል ቢቢሲ የኢትዮጵያ አርክቴክቶች ማኅበር ፕሬዝዳንት የሆኑትን አቶ ሐብታሙ ጌታቸውን ጠይቋል።

እንደማንኛውም የስሪዲ ሕትመት ላይ እንደሚታየው “ኮንክሪት ፔስት የሚባል ነገር አለ” ይላሉ አቶ ሐብታሙ።

“ፔስት ማለት በተለያዩ ኬሚካሎች የዳበረ ኮንክሪት ቀጠን ብሎ ተዘጋጅቶ ኋላ ላይ ግን ጥንካሬውን ሙሉ በሙሉ የሚያገኝ ነው።”

ይህንንም ሲያስረዱ እያንዳንዱ ግድግዳ መጀመሪያ በሚሰጠው የኮምፒውተር ፕሮግራም መሠረት ‘ይጋገራል’ ብለዋል።

እንደ ባለሙያው ገለጻ ግድግዳውም፣ መዋቅሩም እየተጋገረ በስተመጨረሻ ሕንጻ ይሆናል።

ይህ ስሪዲ ኮንስትራክሽን በዋናነት ኮንክሪት በመጠቀም አካፋዩንም ቀድሞ በመሥራት፣ እየተጋገረ ወደላይ የሚወጣበት እና በስተመጨረሻ ሕንጻ የሚሆንበት ቴክኖሎጂ ነው።

ይህ አንድን ሕንጻ ከኮምፒውተር በቀጥታ በሚገነባበት ስፍራ ላይ ‘ኮንክሪት ፔስት’ በመጠቀም እየተጋገረ መዋቅሩ ራሱን የሚያጠናክርበት መንገድ አለው።

በዚያ መልኩ እየተጋገረ የሚጀራው ቤት ወይንም ሕንጻ እየተጠናከረ በስተመጨረሻ ሕንጻ ሆኖ ይወጣል።

ቤት በሦስት ቀን

የቤቶች ግንባታ ፍጥነት በየጊዜው የተለያዩ ሂደቶችን አልፏል። ብሎኬት ከመደርደር፣ አርማታ ከመቆርቆር፣ ከመለሰን ተሻግሮ የሕንጻውን የተለያዩ አካላት በሌላ ስፍራ አምርቶ በማምጣት መገጣጠም ተችሎ ቆይቷል።

አሁን ደግሞ ሕንጻው በሚሠራበት ስፍራ የስሪዲ ማሽኑን በማምጣት በኮምፒውተር ላይ የተቀመጠውን ቤት መጋገር ተችሏል።

ይህ የስሪዲ ቴክኖሎጂ ምን ያህል ፈጣን ነው? ምን ያህልስ በተቀረው ዓለም ይታወቃል?

አቶ ሐብታሙ ስሪዲ ቴክኖሎጂ በጣም አዲስ ቢሆንም በአንዳንድ አካባቢዎች እየተሠራበት መሆኑን ይናገራሉ።

በእርግጥ ቴክኖሎጂው አንዳንድ ገደቦች አሉበት። ለትላልቅ የግባታ መዋቅሮች እና ለባለብዙ ወለል ሕንጻዎች የመዋል አማራጩ ገና ነው። ነገር ግን እነዚህንም በዚሁ ቴክኖሎጁ ለመገንባት ሙከራዎች እየተካሄዱ መሆናቸውን ጨምረው አስረድተዋል።

“አሁን ባለ አንድ እና ባለ ሁለት ፎቅ የሆኑ መዋቅሮች እየተሠሩ ነው። በጠቅላላ አዲስ ቴክኖሎጂ ነው። በዓለም ገና እየተሞከረ ያለ እና ጥሩ ውጤት እያመጣ ያለ ነው።”

በዚህ ቴክኖሎጂ ተጠቅሞ ሕንጻዎቸን ለመገንባት ፈጣን መሆኑንም ሲያብራሩ “አንድ ቤት በሦስት ቀን ሊያልቅ ይችላል” ይላሉ።

ዲዛይኑ ከተመረጠ እና ቦታው ከተዘጋጀ እንዲሁም መሠረቱ ከተጣለ ከዚያ ተነስቶ ቴክኖሎጂውን በመጠቀም ሕንጻውን ‘የመጋገር’ ሥራ ነው የሚካሄደው ሲሉም ያብራራሉ።

አውሮፓ ውስጥ በተለይ ስካንዴኔቪያን አገራት ውስጥ በብዛት ይተገበራል። አሜሪካ ላይ በስፋት እየተሠራበት ነው። በእርግጥ ስሪዲ የሚያትመው ማሽን ራሱ ገና እየዳበረ ያለ በመሆኑ ቴክኖሎጂው በስፋት ገና አልተስፋፋም።

ከእሳት አደጋ የተጠበቁ፣ እንደ ካምፖች ያሉ መኖሪያዎችን በፍጥነት ለመገንባት፣ በተለይ ረዣዥም ያልሆኑ ፎቆችን ቶሎ ሠርቶ ለማጠናቀቅ ጥሩ አቅም የሚሰጥ ቴክኖሎጂ መሆኑንም ጨምረው አስረድተዋል።

ቴክኖሎጂው ከአራት ፎቅ በላይ ያሉ ቤቶችን ለመገንባት እስካሁ ድረስ ገና አልተሞከረም። ከአራት ፎቅ በታች ያሉ ሕንጻዎች ላይ ግን በሚገባ መሥራት እንደሚችል ታይቷል።

ወጪ ቆጣቢ ነው?

የከተማ ልማት ሚኒስትሯ ጫልቱ ሳኒ በኢትዮጵያ የስሪዲ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ባለአራት ፎቅ ሕንጻ እየተገነባ መሆኑን ተናግረዋል።

ሚኒስትሯ ለአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን በሰጡት ማብራሪያ “በጣም ባጠረ ጊዜ፣ በጣም ጥራት ያለው፣ የብረት ግብዓትን ወደ 30 በመቶ መቀነስ የሚያስችል፣ የሲሚንቶ ፍጆታንም ከ35 አስከ 40 በመቶ በሚደርስ መጠን የሚቀንስ፣ በዋጋ ተወዳዳሪ መሆን የሚችሉ” ቤቶች እየተገነቡ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ቴክኖሎጂው በመጀመሪያ ላይ የስሪዲ ማሽኑን ለመሥራት ገንዘብ የሚጠይቅ ቢሆንም፤ በሂደት ወጪ ቆጣቢ የማይሆንበት ምክንያት አለመኖሩን አቶ ሐብታሙ ያስረዳሉ።

የግንባታው ዘርፍ በርካታ የሰው ኃይል በመቅጠር ይታወቃል።

አናጢ፣ ግንበኛ እና ሌሎች ሙያተኞች በስሪዲ ቴክኖሎጂ የግንባታ ሂደት ውስጥ ያላቸው ስፍራ እዚህ ግባ የሚባል አይደለም።

“ብክነትን ይቀንሳል። የሰው ኃይል ተሳትፎ ሊቀንስ ስለሚችል የሥራ ቅጥር ላይ ተጽዕኖ ሊኖረው ይችላል” ይላሉ አቶ ሐብታሙ።

የግንባታ ዘርፉ በርካታ የሰው ኃይል የሚቀጥር ቢሆንም በስሪዲ ቤቶች ግንባታ ግን ከፍተኛ የሙያ ክህሎት ያላቸው ባለሙያዎች ብቻ ሊያስፈልጉ ይችላል።

ባለ አራት ፎቅ ኮንደሚኒየም ለመሥራት ዋና የሚባለው መዋቅሩ በአንድ ወር ውስጥ ያልቃል የሚሉት ባለሙያው፣ ከዚያ ውጪ የፍሳሽ እና ኤሌትሪክ መስመር ዝርጋታ፣ የቀለም ቅብ እና ሌሎች ወለል ማንጠፍን የመሳሰሉ የማጠናቀቂያ ሥራዎች በሰው ኃይል የሚሠሩ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

ከቤት ልማት ጋር በተያያዘ ግንባታውን ሊያፈጥኑ የሚችሉ በርካታ ነገሮች መኖራቸውን የሚያነሱት አቶ ሐብታሙ፣ በርካታ ቤቶችን ሠርቶ ለማቅረብ ይህ ስሪዲ ኮንስትራክሽን እንደ አንድ ቴክኖሎጂ መታየት እንዳለበት ያስረዳሉ።

“በተለይ አጭር ቁመት ላላቸው ሕንጻዎች ጥሩ ቴክኖሎጂ ነው።”

ከቤቶች ልማት ጋር በተያያዘ የጥሬ እቃ አቅርቦት እጥረት ሊኖር ስለሚችል መጓተት ሊፈጠር እንደሚችልም ጠቅሰው፤ ይህ ቴክኖሎጂ ጥሩ የመሆኑን ያህል ሌላም ደግሞ መሞከር ጥሩ መሆኑን ይመክራሉ።

“በተለይ ቴክኖሎጂውን ከውጭ አገር ከማስገባት ይልቅ ራሳችንን አበልጽገን መሥራት ከቻልን ብዙ ነገሮችን ሊያቀልን ይችላል የሚል ሃሳብ አለኝ።”

ምንጭ: ቢቢሲ አማርኛ

Tags: 3D printing
Previous Post

የሪል እስቴት ኩባንያዎች ቤት የሚሸጡበትን አማካይ ዋጋ መተመን የሚያስችል ጥናት እየተካሄደ መሆኑ ተነገረ

Next Post

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በጁባ የቤቶች ግንባታ ለመጀመር ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታወቀ

Betegna Team

Betegna Team

Betegna - ቤተኛ, is a media platform that focuses on Ethiopian housing and real estate news, developments, technology, policies, and lifestyle.

ተዛማጅ ጽሑፎች

የኮንስትራክሽን ዘርፉን በዲጂታል ለማዘመን የተዘጋጀው ኢቫኮኔት (EvaConnect) ፕላትፎርም በይፋ ተመረቀ
Technology

የኮንስትራክሽን ዘርፉን በዲጂታል ለማዘመን የተዘጋጀው ኢቫኮኔት (EvaConnect) ፕላትፎርም በይፋ ተመረቀ

July 26, 2026
ለመኖሪያ ቤት ፈላጊዎች አዲስ ተስፋን ይዘው የመጡት ዘመናዊ የግንባታ ቴክኖሎጂዎች
Technology

ለመኖሪያ ቤት ፈላጊዎች አዲስ ተስፋን ይዘው የመጡት ዘመናዊ የግንባታ ቴክኖሎጂዎች

July 13, 2026
ጃፓን የመሬት መንቀጥቀጥ ሲከሰት ከምድር ተነስተው የሚንሳፈፉ ቤቶችን እየሞከረች ነው
Technology

ጃፓን የመሬት መንቀጥቀጥ ሲከሰት ከምድር ተነስተው የሚንሳፈፉ ቤቶችን እየሞከረች ነው

November 22, 2025
Next Post
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በጁባ የቤቶች ግንባታ ለመጀመር ዝግጅት  ማጠናቀቁን አስታወቀ

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በጁባ የቤቶች ግንባታ ለመጀመር ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታወቀ

  • Trending
  • Comments
  • Latest
የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የወጣ አዋጅ 721/2004

የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የወጣ አዋጅ 721/2004

April 23, 2024
ስለ ግብር የሚከፈልበት የቤት ኪራይ ገቢ

ስለ ግብር የሚከፈልበት የቤት ኪራይ ገቢ

April 6, 2024
በአዲስ አበባ የቤት ሽያጭ ዋጋ ተመን ላይ በድጋሚ ማሻሻያ ተደረገ

በአዲስ አበባ የቤት ሽያጭ ዋጋ ተመን ላይ በድጋሚ ማሻሻያ ተደረገ

April 3, 2024
የመሬት ልማትና አስተዳር ደንብ ቁጥር 163/2016

የመሬት ልማትና አስተዳር ደንብ ቁጥር 163/2016

April 22, 2024
ስለ ሪል እስቴት ምን ያውቃሉ?

ስለ ሪል እስቴት ምን ያውቃሉ?

August 18, 2023
Home pic

ቤት ለሚገዙ እና ለሚሸጡ አካላት ማሳሰቢያ ተሰጠ

0
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤት አቅርቦትን ለማሳደግ የሚያስችል ውይይት ከሪል እስቴት አልሚዎች ጋር ውይይት አደረገ!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤት አቅርቦትን ለማሳደግ የሚያስችል ውይይት ከሪል እስቴት አልሚዎች ጋር ውይይት አደረገ!

0
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ያስተዋወቀበትን የገርጂ መኖሪያ መንደር ፕሮጀክት ሊያስመርቅ ነው

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ያስተዋወቀበትን የገርጂ መኖሪያ መንደር ፕሮጀክት ሊያስመርቅ ነው

0
ባለ 9 ወለል ህንፃ በተጀመረ በ69ኛ ቀኑ ተጠናቀቀ!!

ባለ 9 ወለል ህንፃ በተጀመረ በ69ኛ ቀኑ ተጠናቀቀ!!

0
ስለ ሪል እስቴት ምን ያውቃሉ?

ስለ ሪል እስቴት ምን ያውቃሉ?

0
የሪል እስቴት አልሚዎች ማህበር የ7% የብድር ወለድ ጥያቄ በባለሙያዎች መካከል ያስነሳው ክርክር

የሪል እስቴት አልሚዎች ማህበር የ7% የብድር ወለድ ጥያቄ በባለሙያዎች መካከል ያስነሳው ክርክር

November 18, 2026
በጋዜቦ አደባባይ አካባቢ በግንባታ ሂደት ላይ ከነበረ ሕንጻ ላይ የወደቁ ሦስት ሠራተኞች ሕይወታቸውን አጡ

በጋዜቦ አደባባይ አካባቢ በግንባታ ሂደት ላይ ከነበረ ሕንጻ ላይ የወደቁ ሦስት ሠራተኞች ሕይወታቸውን አጡ

November 14, 2026
በ5 ዓመታት ቤቶችን ገንብተን ለማስረከብ የገባነውን ቃል በተግባር ለማረጋገጥ እየተጋን ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

በ5 ዓመታት ቤቶችን ገንብተን ለማስረከብ የገባነውን ቃል በተግባር ለማረጋገጥ እየተጋን ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

November 13, 2026
የ1.5 ሚሊዮን መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት ወደ ተግባር ምዕራፍ ተሸጋግሯል

የ1.5 ሚሊዮን መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት ወደ ተግባር ምዕራፍ ተሸጋግሯል

November 12, 2026
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከዩኤን ሃቢታት ዋና ዳይሬክተር አናክላውዲያ ሮስባክ ጋር መወያየታቸውን ገለፁ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከዩኤን ሃቢታት ዋና ዳይሬክተር አናክላውዲያ ሮስባክ ጋር መወያየታቸውን ገለፁ

November 11, 2026

ብዙ የተነበቡ

  • የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የወጣ አዋጅ 721/2004

    የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የወጣ አዋጅ 721/2004

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ስለ ግብር የሚከፈልበት የቤት ኪራይ ገቢ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአዲስ አበባ የቤት ሽያጭ ዋጋ ተመን ላይ በድጋሚ ማሻሻያ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የመሬት ልማትና አስተዳር ደንብ ቁጥር 163/2016

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ስለ ሪል እስቴት ምን ያውቃሉ?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Categories

  • Community & CSR (28)
  • Construction & Projects (29)
  • Construction Material Supply (9)
  • Design & Innovation (18)
    • Architecture (2)
    • Technology (14)
  • Global (4)
  • Insights & Profiles (20)
  • Legal Updates (89)
    • Community Complaints (8)
    • Corruption (ሙስና) (2)
    • Directives (መመሪያዎች) (1)
    • Proclamations (አዋጅ) (7)
    • Regulations (ደንብ) (2)
  • Mortgages & Finance (14)
  • Property Handover (16)
  • Public Housing (71)
  • Real Estate Guides (13)
    • Buying Guide (3)
    • Knowledge Base (1)
    • Renting Guide (2)
    • Selling Guide (7)
  • Sales & Marketing (67)
  • Tenders & Bids (60)
    • Land Lease (29)
    • Request for EOI (1)
  • Home
  • Guides
  • Mortgage
  • Highlights
  • Legal Updates
  • Tenders & Bids
Betegna Logo Footer

Betegna – ቤተኛ, powered by Betbegara.com, is a media platform that focuses on Ethiopian housing and real estate news, developments, technology, policies, and lifestyle.

© 2026 Betegna – ቤተኛ | Ethiopian Housing and Real Estate News & Insights

  • Home
  • Guides
    • Buying Guide
    • Renting Guide
    • Selling Guide
    • Knowledge Base
  • Mortgage
  • Technology
  • Legal
    • Proclamations (አዋጅ)
    • Regulations (ደንብ)
    • Directives (መመሪያዎች)
    • Community Complaints
    • Corruption (ሙስና)
  • Tender
    • Auction (ሐራጅ)
    • Land Lease (የመሬት ሊዝ)
    • Request for EOI
  • Project Highlight
  • More
    • Community & CSR
    • Construction & Projects
    • Construction Material Supply
    • Design & Innovation
    • Public Housing
    • Insights & Profiles
    • Sales & Marketing
    • Property Handover
    • Global
    • Contact Us
No Result
View All Result
Sell, Buy, Rent