ዘነበ ፍሬው ሪል እስቴት በትናንትናው ዕለት በሸራተን ሆቴል በተካሄደ ፕሮግራም የጎተራ ቁጥር 2 ፕሮጀክቱን ይፋ አደረገ።
በፕሮጀክቱ ማብሰሪያ መርሐ ግብር ላይ የተገኙት የዘነበ ፍሬው ሆልዲንግ ምክትል የበላይ ኃላፊ አቶ በረከት አለሙ፤ “በሪል እስቴት ዘርፉ በስፋት የሚነሳውን የታማኝነትና የጥራት ጉድለት ለመቅረፍ ዘመናዊ የግንባታ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ፕሮጀክቱን በተያዘለት የጊዜ ገደብ አጠናቆ ማስረከብ ዋነኛ ትኩረታችን ነው” ሲሉ ተናግረዋል።
በፕሮግራሙ ላይ የኩባንያው የቺፍ ማርኬቲንግ ኦፊሰር (Chief Marketing Officer) የሆኑት አቶ ዳግም ዘነበ ንግግር ያደረጉ ሲሆን፣ ድርጅቱ ላለፉት 40 ዓመታት በተለያዩ ኢንዱስትሪዎች እና በሪል እስቴት ዘርፍ ሲንቀሳቀስ መቆየቱን ገልጸዋል።
በሚስማር፣ በእምነበረድ፣ በፕላስቲክ ከረጢት እንዲሁም በሲሚንቶ ውጤቶች ማምረት ለሀገራዊ እድገት የበኩሉን ሚና የተጫወተው ድርጅቱ፣ በሪል እስቴት ዘርፍም ብዙዎችን የቤት ባለቤት እንዳደርገ ገልፀዋል።
ድርጅቱ በወለቴ 90,000 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ ኮምፓውንድ አፓርትመንት ውስጥ ከ200 በላይ ቪላ እና ጂ + 1 ቤቶችን እንዲሁም በጎተራ 1,000 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ ባለ 11 ወለል ሕንፃ ላይ ከ70 በላይ ቤቶችን ገንብቶ አስረክቧል።


የዘነበ ፍሬው ሆልዲንግ የመንግሥትን የ1.5 ሚሊዮን ቤቶችን የማልማት ዕቅድ ለመደገፍ የበኩሉን አስተዋፅዖ ለማድረግ በጎተራ ግዙፍ ፕሮጀክት ይዞ መምጣቱን አቶ ዳግም ዘነበ ገልጸዋል።
ይህ ዕለት የአዲስ ፕሮጀክት መጀመሪያ ብቻ ሳይሆን ለድርጅታቸውም አዲስ ምዕራፍ መጀመሪያ መሆኑን ጠቁመዋል።
ድርጅታችን የሪል እስቴት ሴክተሩ ላይ ሙሉ ትኩረቱን በማድረግ በጎተራ ቁጥር 2 የሚገነባው ግዙፍ የሆነ የገበያ ማዕከልና ዘመናዊ ቤቶች ግንባታ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ማለትም ቢልዲንግ ኢንፎርሜሽን ሞዴሊንግ (Building Information Modeling) ያሉ ዘመናዊ የአሠራር ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም በጥራትና በፍጥነት እንደሚያስረከብ አስታውቀዋል።
በዕለቱ የድርጅቱ ባለቤት አቶ ዘነበ ፍሬው በልጅነታቸው ወደ አዲስ አበባ በመግባት ያገኙትን የሥራ እድሎች በታማኝነት በመሥራት፣ ያገኙትን ዕድል በመጠቀም ወደ ሪል እስቴት ዘርፍ ለመግባት እንደቻሉና ዘነበ ፍሬው ሪል እስቴት እንደተመሠረተ ገልጸዋል።
ከመጀመሪያው ጀምሮ ከጎናቸው ለነበሩ፣ በራዕያቸው እምነት ላሳደሩ፣ በችግር ጊዜ ለደገፏቸው እና በስኬት ከእነሱ ጋር ለተደሰቱት ያላቸው ምስጋና ከፍተኛ መሆኑንም ተናግረዋል።
በዕለቱም የአዲሱ ፕሮጀክት 3D ሞዴል ዲዛይን ለእይታ የበቃ ሲሆን፣ የድርጅቱ የሽያጭና የማርኬቲንግ ዳይረክቶር አቶ ዳዊት ስለሽ ስለፕሮጀክቱ ሰፊ ገለፃ አድርገዋል።

በመጨረሻም በዕለቱ ለተገኙ እና እንዲሁም ቀድመው ለሚገዙ ደንበኞች የዋጋ ቅናሽ የቀረበ ሲሆን በዚህም መሰረት ሱቅ ለሚገዙ 350 ሺህ ብር የነበረው ዋጋ ወደ 295 ሺህ ብር ዝቅ ብሎ በ15 በመቶ ቅናሽ የቀረበ ሲሆን ክፍያውን 100 በመቶ ለሚከፍሉ ደግሞ የ25 በመቶ ቅናሽ ተደርጓል።
መኖሪያ ቤት ለሚገዙ ደንበኞች ደግሞ 118 ሺህ ብር የነበረው ዋጋ ከ95 ሺህ እስከ 99 ሺህ ብር ዝቅ ተደርጎ የቀረበ ሲሆን ክፍያውን 100 በመቶ ለሚከፍሉ የ30 በመቶ ቅናሽ ተደርጎ ለሽያጭ ቀርቧል።
የጎተራ ቁጥር 2 ፕሮጀክት 7,313 ካሬ ሜትር አጠቃላይ ስፋት ያለው ሲሆን 3B+G+21 የሆኑ ሶስት መንትያ ሕንፃዎችን፣ ከ400 በላይ ሱቆች እና ከ66 ካሬ ሜትር ስቱዲዮ ጀምሮ እስከ 234 ካሬ ሜትር የሚደርሱ የመኖሪያ ቤቶችን የያዘና በሶስት ዓመት ውስጥ የሚረከብ ግዙፍ ፕሮጀክት ነው።
በስነ-ስርዓቱ ላይ የመንግስት ባለስልጣናት፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ ባለሀብቶች እና የድርጅቱ ደንበኞች በክብር እንግድነት ተገኝተዋል።


















