• BetBegara.com
  • Buy
  • Rent
  • Sale
  • Services
  • Contact Us
Betegna - ቤተኛ | Ethiopian Housing and Real Estate News & Insights
Advertisement
  • Home
  • Guides
    • Buying Guide
    • Renting Guide
    • Selling Guide
    • Knowledge Base
  • Mortgage
  • Technology
  • Legal
    • Proclamations (አዋጅ)
    • Regulations (ደንብ)
    • Directives (መመሪያዎች)
    • Community Complaints
  • Tender
    • Auction (ሐራጅ)
    • Land Lease (የመሬት ሊዝ)
  • Project Highlight
  • More
    • Community & CSR
    • Construction & Projects
    • Construction Material Supply
    • Design & Innovation
    • Government Housing
    • Insights & Profiles
    • Sales & Marketing
    • Property Handover
No Result
View All Result
Sell, Buy, Rent
  • Home
  • Guides
    • Buying Guide
    • Renting Guide
    • Selling Guide
    • Knowledge Base
  • Mortgage
  • Technology
  • Legal
    • Proclamations (አዋጅ)
    • Regulations (ደንብ)
    • Directives (መመሪያዎች)
    • Community Complaints
  • Tender
    • Auction (ሐራጅ)
    • Land Lease (የመሬት ሊዝ)
  • Project Highlight
  • More
    • Community & CSR
    • Construction & Projects
    • Construction Material Supply
    • Design & Innovation
    • Government Housing
    • Insights & Profiles
    • Sales & Marketing
    • Property Handover
No Result
View All Result
Betegna - ቤተኛ | Ethiopian Housing and Real Estate News & Insights
No Result
View All Result
“የሊዝ ህግ ተላልፈዋል” የተባሉ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በሶስት ቀናት ውስጥ 45 ሺህ ብር ቅጣት እንዲከፍሉ ማስጠንቀቂያ ተሰጣቸው

“የሊዝ ህግ ተላልፈዋል” የተባሉ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በሶስት ቀናት ውስጥ 45 ሺህ ብር ቅጣት እንዲከፍሉ ማስጠንቀቂያ ተሰጣቸው

Betegna Team by Betegna Team
October 12, 2025
in Legal Updates
A A
0
0
SHARES
Share on FacebookShare on LinkedIn

በአዲስ አበባ ከተማ “የመኖሪያ ቤቶቻቸውን ለንግድ ስራ አውለዋል” የተባሉ ነዋሪዎች፤ በሶስት ቀናት ገደብ ውስጥ እስከ 45 ሺህ ብር ቅጣት እንዲከፍሉ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናገሩ። ነዋሪዎቹ የመኖሪያ ቤቶቻቸውን ለሌላ አገልግሎት ለማዋል የሚያስችላቸውን የሊዝ ውል ለውጥ ለማድረግ ከመቶ ሺህዎች እስከ ሚሊዮኖች ብር የሚቆጠር ክፍያ መጠየቃቸውንም ገልጸዋል።

በመዲናይቱ በሚገኙት በአቃቂ ቃሊቲ፣ በለሚ ኩራ፣ በንፋስ ስልክ ላፍቶ እና ጉለሌ ክፍለ ከተሞች የሚኖሩ ነዋሪዎች፤ ባለፉት ቀናት የማስጠንቀቂያ ደብዳቤዎች እንደደረሷቸው “ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” አረጋግጣለች። በአንዳንዶቹ ክፍለ ከተሞች በሚገኙ የንግድ ቤቶች እና አገልግሎት መስጪያዎች ላይ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤዎች መለጠፋቸውንም የየአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል።

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ዓለም ባንክ አዲሱ ሰፈር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚገኙ ነዋሪዎች፤ ከክፍለ ከተማ መምጣታቸውን የገለጹ ሰራተኞች ካለፈው ረቡዕ ጀምሮ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤውን ሲሰጡ እንደነበር ገልጸዋል። “ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” የተመለከተችው የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ፤ ነዋሪዎቹ መሬት የወሰዱት ለመኖሪያ አገልግሎት ለመዋል እንደሆነ ይጠቅሳል።

ሆኖም ነዋሪዎቹ “በገቡት የሊዝ ውል መሰረት ለተፈቀደላቸው አገልግሎት ብቻ እየተጠቀሙ አለመሆኑን” በመስክ ክትትል ማረጋገጥ መቻሉን ያትታል። ነዋሪዎቹ ማስጠንቀቂያው ከተሰጠበት አሊያም ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ ባሉት ሶስት የስራ ቀናት ውስጥ፤ ካርታቸውን፣ የሊዝ ውላቸውን፣ ለመጨረሻ ጊዜ የከፈሉበትን የሊዝ ክፍያ ደረሰኝ እንዲሁም የንግድ ፍቃዳቸውን በመያዝ ለክፍለ ከተማ እንዲያቀርቡም ቀነ ገደብ ያስቀምጣል።

ይህን መሰል የሶስት ቀናት የማሳወቂያ ጊዜ፤ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ላሉ ነዋሪዎች መሰጠቱን አንድ የክፍለ ከተማው ኃላፊ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” አረጋግጠዋል። ሂደቱ “ቀጣይነት ያለው” እና “በከተማ አቀፍ ደረጃ በሌሎችም ክፍለ ከተሞች እየተተገበረ” ያለ መሆኑን ኃላፊው ተናግረዋል።

ከአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ለነዋሪዎች የተሰጠው ደብዳቤ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ለክፍለ ከተማው መሬት ልማትና አስተዳደር ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት መረጃዎችን አቅርበው ማስተካከያ ወይም የአገልግሎት ለውጥ ማድረግ እንዳለባቸው ያሳስባል። ይህን በማያደርጉ ነዋሪዎች፤ አሁን በስራ ላይ ባለው የሊዝ አዋጅ እና ደንብ መሰረት እርምጃ እንደሚወሰድባቸውም ያስጠነቅቃል።

ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ አንድ የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ነዋሪ፤ የመኖሪያ ቤታቸው አካል የሆነውን ቤት ለንግድ በማዋላቸው በሶስት ቀናት ውስጥ 45 ሺህ ብር ቅጣት እንዲከፍሉ ቀነ ገደብ እንደተሰጣቸው ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል። ነዋሪው የቅጣት መጠኑ የተገለጻላቸው፤ ከመኖሪያ ቤትነት ወደ ንግድ ለሚደረገው “የአገልግሎት ለውጥ” የተጠየቁትን በሚሊዮን ብር የሚቆጠር ገንዝብ ለመክፈል “አቅማቸው የማይችል” መሆኑን የሚያረጋግጥ ደብዳቤ ከተቀበሉ በኋላ እንደሆነ አስረድተዋል።

“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” የተመለከተችው ይህ ደብዳቤ “አገልግሎት ለውጥ ማድረግ የማንፈልግ በመሆኑ ቅጣት በመክፈል ንግድ ለማቆም ተሰማምተናል” ይላል። ደብዳቤው የተዘጋጀው በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር፣ በመሬት ልማትና አስተዳደር ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት፣ የወሰን ማስከበር፣ መሬት ባንክና ማስተላለፍ ዳይሬክቶሬት መሆኑም በግልጽ ተመልክቷል።

በዚሁ ደብዳቤ ላይ ነዋሪው ለመኖሪያ የተፈደቀላቸውን ካርታ (የይዞታ ማረጋገጫ) “ለንግድ እየተጠቀሙበት” እንደሆነ የሚገልጽ ዐረፍተ ነገር ተካትቷል። ነዋሪው “ያለ ፍቃድ” የሰሩበትን ቅጣት ከፍለው “በተፈቀደላቸው አገልግሎት ብቻ የሚገለገሉ መሆኑን” በፊርማቸው እንዲያረጋግጡም ደብዳቤው ያስገድዳል።

ተመሳሳይ ደብዳቤ ባለፈው ሐሙስ የተቀበሉ ሌላ የአካባቢው ነዋሪ፤ “አገልግሎት ለመለወጥ” የተጠየቁት 4.5 ሚሊዮን ብር ከአቅማቸው በላይ መሆኑን ይገልጻሉ። በመኖሪያ ቤታቸው ካሬ ሜትር ልክ የተሰላው የገንዝብ መጠን፤ በአካባቢያቸው በቅርቡ ከተካሄደ የሊዝ ጨረታ ዋጋ በላይ መሆኑንም ያስረዳሉ።

“በሊዝ ጨረታ አዲስ ቦታ ልግዛ ብትል እንኳ በካሬ ሜትር ይህን ያህል አይጠየቀበትም” የሚሉት ነዋሪው፤ ለአገልግሎት ለውጥም ሆነ ለቅጣት የተጠየቀው ቅጣት የነዋሪዎችን አቅም ያገናዘበ እንዳልሆነ ያብራራሉ። “ብዙ ቤተሰብ ታስተዳድራለህ፣ ግብር ተከፍላለህ፣ አራት አምስት ሰራተኛ አለህ፣ በሶስት ቀን መጥተህ [ክፈል ማለት] ይሄ በጣም ለመግለጽ የሚቸግር ሁኔታ ነው” ሲሉ ነዋሪው ስሜታቸውን አጋርተዋል።

የተሰጣቸው ቀነ ገደብ የደረሰባቸው የአካባቢው ነዋሪዎች በሰሚ ሰሚ የሰሙትን መረጃ ይዘው፤ የንግድ ቤቶቻቸውን ማፍረስ መጀመራቸውን ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል። ያልተረጋገጠው መረጃ “እያንዳንዱ ነዋሪ የይዞታውን 30 በመቶ ለንግድ አገልግሎት መዋል ይችላል” የሚል እንደሆነ የሚገልጹት ነዋሪዎቹ፤ የንግድ ቤታቸውን በዚሁ መልኩ ለማስተካከል እየሞከሩ እንደሆነ አስረድተዋል።

የነዋሪዎችን አቤቱታ እና ቅሬታ በተመለከተ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊዎች ምላሽ እና ዝርዝር መረጃ ለማግኘት ትላንት እና ዛሬ ያደረግነው ተደጋጋሚ ሙከራ አልተሳካም። ኃላፊዎቹ በሞባይል ስልኮቻቸው ላይ ለተላኩላቸው አጭር የጹሁፍ መልዕክቶችም ምላሽ ሳይሰጡ ቀርተዋል።

ምንጭ፡ ኢትዮጵያ ኢንሳይደር

Previous Post

በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ብቻ ለመንግስታዊ ተቋማት 551.96 ሄክታር የለማ መሬት መዘጋጀቱ ተገለጸ

Next Post

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የ7ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ: ማስታወቂያ

Betegna Team

Betegna Team

Betegna - ቤተኛ, powered by Betbegara.com, is a media platform that focuses on Ethiopian housing and real estate news, developments, technology, policies, and lifestyle.

ተዛማጅ ጽሑፎች

ለሕዝብ መዝናኛ የተዘጋጀን ይዞታ ላልተገባ አካል በሙስና ሰጥተዋል የተባሉ ተጠርጣሪዎች ተከሰሱ
Legal Updates

ለሕዝብ መዝናኛ የተዘጋጀን ይዞታ ላልተገባ አካል በሙስና ሰጥተዋል የተባሉ ተጠርጣሪዎች ተከሰሱ

March 11, 2026
ያለ ደረሰኝ ሽያጭ ሲፈፅሙ የተገኙ የኮንስትራክሽን ግብአት አከፋፋይ ነጋዴዎች በቁጥጥር መዋላቸው ተገለጸ
Legal Updates

ያለ ደረሰኝ ሽያጭ ሲፈፅሙ የተገኙ የኮንስትራክሽን ግብአት አከፋፋይ ነጋዴዎች በቁጥጥር መዋላቸው ተገለጸ

January 17, 2026
ቤታቸው ለልማት የፈረሰባቸው ነጋዴዎች የግብር ዕዳቸውን ክፍያ በተከፋፈለ ጊዜ እንዲፈጽሙ እየተደረገ መሆኑ ተገለጸ
Legal Updates

ቤታቸው ለልማት የፈረሰባቸው ነጋዴዎች የግብር ዕዳቸውን ክፍያ በተከፋፈለ ጊዜ እንዲፈጽሙ እየተደረገ መሆኑ ተገለጸ

January 15, 2026
Next Post
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የ7ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ: ማስታወቂያ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የ7ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ: ማስታወቂያ

  • Trending
  • Comments
  • Latest
የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የወጣ አዋጅ 721/2004

የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የወጣ አዋጅ 721/2004

April 23, 2024
በአዲስ አበባ የቤት ሽያጭ ዋጋ ተመን ላይ በድጋሚ ማሻሻያ ተደረገ

በአዲስ አበባ የቤት ሽያጭ ዋጋ ተመን ላይ በድጋሚ ማሻሻያ ተደረገ

April 3, 2024
ስለ ግብር የሚከፈልበት የቤት ኪራይ ገቢ

ስለ ግብር የሚከፈልበት የቤት ኪራይ ገቢ

April 6, 2024
ስለ ሪል እስቴት ምን ያውቃሉ?

ስለ ሪል እስቴት ምን ያውቃሉ?

August 18, 2023
የመሬት ልማትና አስተዳር ደንብ ቁጥር 163/2016

የመሬት ልማትና አስተዳር ደንብ ቁጥር 163/2016

April 22, 2024
Home pic

ቤት ለሚገዙ እና ለሚሸጡ አካላት ማሳሰቢያ ተሰጠ

0
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤት አቅርቦትን ለማሳደግ የሚያስችል ውይይት ከሪል እስቴት አልሚዎች ጋር ውይይት አደረገ!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤት አቅርቦትን ለማሳደግ የሚያስችል ውይይት ከሪል እስቴት አልሚዎች ጋር ውይይት አደረገ!

0
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ያስተዋወቀበትን የገርጂ መኖሪያ መንደር ፕሮጀክት ሊያስመርቅ ነው

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ያስተዋወቀበትን የገርጂ መኖሪያ መንደር ፕሮጀክት ሊያስመርቅ ነው

0
ባለ 9 ወለል ህንፃ በተጀመረ በ69ኛ ቀኑ ተጠናቀቀ!!

ባለ 9 ወለል ህንፃ በተጀመረ በ69ኛ ቀኑ ተጠናቀቀ!!

0
ስለ ሪል እስቴት ምን ያውቃሉ?

ስለ ሪል እስቴት ምን ያውቃሉ?

0
ቴምር ሪል እስቴት ለደራሲና ዳይሬክተር ዳግማዊ አመለወርቅ ፈይሣ የቤት ስጦታ አበረከተለት

ቴምር ሪል እስቴት ለደራሲና ዳይሬክተር ዳግማዊ አመለወርቅ ፈይሣ የቤት ስጦታ አበረከተለት

March 18, 2026
አልሚዎች በተገደበ የጊዜ ሰሌዳ የተላለፉ ቦታዎችን አልምተው ለአገልግሎት ዝግጁ እንዲያደርጉ ማሳሰቢያ ተሰጠ

አልሚዎች በተገደበ የጊዜ ሰሌዳ የተላለፉ ቦታዎችን አልምተው ለአገልግሎት ዝግጁ እንዲያደርጉ ማሳሰቢያ ተሰጠ

March 18, 2026
በለንደን የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ለዲያስፖራ ባለሀብቶች የሪል እስቴት ኤክስፖ ማዘጋጀቱን ገለጸ

በለንደን የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ለዲያስፖራ ባለሀብቶች የሪል እስቴት ኤክስፖ ማዘጋጀቱን ገለጸ

March 17, 2026
ከተማ አስተዳደሩ 315 የንግድ ሱቆችን ለኮሪደር ልማት ተነሺዎች በዕጣ አስተላለፈ

ከተማ አስተዳደሩ 315 የንግድ ሱቆችን ለኮሪደር ልማት ተነሺዎች በዕጣ አስተላለፈ

March 17, 2026
የጊፍት ሪል እስቴት ባለቤት አንድ ሱቅ እና ሁለት ሚሊዮን ብር ለመቄዶንያ

የጊፍት ሪል እስቴት ባለቤት አንድ ሱቅ እና ሁለት ሚሊዮን ብር ለመቄዶንያ

March 16, 2026

ብዙ የተነበቡ

  • የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የወጣ አዋጅ 721/2004

    የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የወጣ አዋጅ 721/2004

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአዲስ አበባ የቤት ሽያጭ ዋጋ ተመን ላይ በድጋሚ ማሻሻያ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ስለ ግብር የሚከፈልበት የቤት ኪራይ ገቢ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ስለ ሪል እስቴት ምን ያውቃሉ?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የመሬት ልማትና አስተዳር ደንብ ቁጥር 163/2016

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Categories

  • Community & CSR (20)
  • Construction & Projects (25)
  • Construction Material Supply (6)
  • Design & Innovation (12)
    • Architecture (1)
    • Technology (10)
  • Global (1)
  • Government Housing (47)
  • Insights & Profiles (12)
  • Legal Updates (75)
    • Community Complaints (5)
    • Proclamations (አዋጅ) (7)
    • Regulations (ደንብ) (2)
  • Mortgages & Finance (10)
  • Property Handover (9)
  • Real Estate Guides (11)
    • Buying Guide (3)
    • Knowledge Base (1)
    • Renting Guide (2)
    • Selling Guide (6)
  • Sales & Marketing (35)
  • Tenders & Bids (54)
    • Land Lease (27)
  • Home
  • Guides
  • Mortgage
  • Highlights
  • Legal Updates
  • Tenders & Bids

Betegna – ቤተኛ, powered by Betbegara.com, is a media platform that focuses on Ethiopian housing and real estate news, developments, technology, policies, and lifestyle.

© 2024 Betegna – ቤተኛ | Ethiopian Housing and Real Estate News & Insights

  • Home
  • Guides
    • Buying Guide
    • Renting Guide
    • Selling Guide
    • Knowledge Base
  • Mortgage
  • Technology
  • Legal
    • Proclamations (አዋጅ)
    • Regulations (ደንብ)
    • Directives (መመሪያዎች)
    • Community Complaints
  • Tender
    • Auction (ሐራጅ)
    • Land Lease (የመሬት ሊዝ)
  • Project Highlight
  • More
    • Community & CSR
    • Construction & Projects
    • Construction Material Supply
    • Design & Innovation
    • Government Housing
    • Insights & Profiles
    • Sales & Marketing
    • Property Handover
No Result
View All Result
Sell, Buy, Rent