አቶ ዘላለም ክፍሌ ይባላሉ።
ሰይፉ ፋንታሁን ባዘጋጀው ለመቄዶንያ ገንዘም የማሰባሰብ በቀጥታ ስርጭቱ ወደ መቄዶኒያ ግቢ ደርሰው ከቢኒ ጎን ሆነው እንዲህ አሉ:-“ከዶ/ር ቢኒ ጋር 5ዓመት አንድ ክፍል ውስጥ ሆነን ህግ ተምረናል። ቢኒያም ደግነትን የጀመረው ያኔ ነው፣ በነበረው መኪና እኛ የክፍልሀገር ልጆችን ይሸኘን ነበር፣ኪሳችን ሲጎድልም ያግዘን ነበር።
ከአሜሪካ እንደመጣ ተገናኝተን ልሸኘው ስወጣ መንገድ ላይ ሰው አንስተው ልብሱ ሽንት ሽንት ይል ነበርና ፣ “ቢኒ ሰውን መርዳትህ አንድነገር ነው፣ ግን ትክክል አይደለህም….” ስለው እንዳትጨርሰው ብሎ ተቆጣኝ፣ ይህ ንግግሩ ከአዕምሮዬ አይወጣም።
ቢኒ አንተ የባቹ በረከት ነህ፣ከአንተ ጋር መማር መባረክ ነው፣ከ7500ሰው በላይ አኑሮ ሰንመለከት ሁሌም ይገርመናል!እኛም የአቅማችንን እናድርግ በማለት በሚያስደንቅ ሁኔታ ከባለቤታቸው ጋር ተማክረው እስከ20ሚሊዮን ብር የሚገመት 700ካሬ መኖሪያ ቤት ለግሰዋል።
ምንጭ፡ ጌጡ ተመስገን


















