ጊፍት ሪል እስቴት የዘንድሮውን የተፅዕኖ ፈጣሪዎች አዋርድን በዋና ስራ አስፈፃሚው አቶ ገብረ እየሱስ ኢጋታና በብራንድ አምባሳደሩ አርቲስት አብርሃም ወልዴ አማካኝነት ሽልማቱን ለክብር ዶክተር አርቲስት መሃሙድ አህመድ ሰጥቷል።
ሽልማቱን ለመስጠት በወጡበት አጋጣሚ ጊፍት ሪል እስቴት በተጨማሪ የአንድ ሚሊዮን ብር ሽልማት ለመሐሙድ አህመድ በመስጠት ተመልካቹንም ተሸላሚውንም ሰርፕራይዝ አድርጓል።
የአፍሪካ ኢምፓክት አዋርድ (Africa Impact Award) በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ለትርፍ ያልተቋቋመው ኖቫ ኮኔክሽን የሚያዘጋጀው አመታዊ የእውቅና ሽልማት ሲሆን በአሜሪካና በአፍሪካ በሙያቸው ታላቅ ሥራ የሰሩ ግለሰቦችን ለማክበር የሚሰናዳ ነው።


















