የንግድ ቤት ኪራይ ጨረታ መራዘሙን ስለማሳወቅ፤
የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ በከተማው በተለያዩ አካባቢዎች በጋራ መኖሪያ ህንፃ ላይ እና የኮሪደር ልማት በተሰራባቸው አካባቢዎች የሚገኙ የመንግስት ንግድ ቤቶችን በጨረታ አወዳድሮ በኪራይ ለማስተላለፍ ከሐምሌ 18 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ የጨረታ ሰነድ በመሸጥ ላይ መሆኑ ይታወቃል፡፡
ይሁንና የተጫራቾችን ፍላጎት መነሻ በማድረግ እና ለዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ግዥ በቂ ጊዜ ለመስጠት ሲባል የጨረታ ሰነድ መግዣ እና መመለሻ ጊዜን ማራዘም አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡
በመሆኑም የጨረታ ሰነድ የመግዣ እና የመወዳደሪያ ሃሳብ የመመለሻ ጊዜ ከነሐሴ 03 ቀን 2017 ጀምሮ እስከ ነሐሴ 12 ቀን 2017 ድረስ ላሉት 10 ተከታታይ ቀናት (ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ) የተራዘመ ሲሆን ጨረታው ነሐሴ 12 ቀን 2017 ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ተዘግቶ ነሐሴ 13 ቀን 2017 ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ በጨረታ መመሪያው ክፍል አንድ አንቀጽ 17 በተገለፀው ቅደም ተከተል መሰረት የሚከፈት መሆኑን እየገለፅን፤
የንግድ ቤቶች በጨረታ ተወዳድሮ መከራየት የሚፈልግ ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት በቢሮ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በኦንላይን (https://addishousebid.gov.et/) ሲስተም ወይም በአካል ዘወትር በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ምሽት 1፡00 ሰዓት ድረስ የማይመለስ ብር 1,000.00 /አንድ ሺህ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት የሚችል መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ማሳሰቢያ፡-
በጨረታ ሰነዱ ክፍል አንድ አንቀጽ 16 ንዑስ አንቀጽ 16.6 መሰረት በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የሚገኙ ንግድ ቤቶች ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ማስገቢያ የነበረው ሳጥን ቁጥር 6 ወደ ሳጥን ቁጥር 5 የተቀየረ መሆኑን እና የመክፈቻው ቀንም ነሐሴ 14 ቀን 2017 የተደረገ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ


















