የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ አካባቢዎች ለሚገኙ የቤቶች ፕሮጀክቶች የዲዛይን ማሻሻያ፣ ክለሳ፣ የኮንስትራክሽን ቁጥጥር፣ የውል አስተዳደር እና የጥራት ቁጥጥር ስራዎችን የሚያከናውኑ ብቁ የምህንድስና አማካሪ ድርጅቶች የፍላጎት መግለጫ(Expression of Iterest – EOI) እንዲያቀርቡ ጥሪ አቅርቧል።
የፕሮጀክቶቹ አስተዳደር የተቀላጠፈ እና ቴክኒካዊ ብቃትን የተከተለ እንዲሆን አገልግሎቱ እስከ G+4 ከፍታ ካላቸው ዝቅተኛ ህንፃዎች ጀምሮ G+12 እና ከዚያ በላይ ከፍታ እስካላቸው ከፍተኛ የህንፃ ኮምፕሌክሶች ድረስ በአራት የተለያዩ የህንፃ ከፍታ ምድቦች ተከፋፍሎ ቀርቧል።
በዚሁ መሰረት የደረጃ ሁለት እና ከዚያ በላይ የህንፃ ወይም የሲቪል ኢንጂነሪንግ አማካሪነት ፈቃድ ያላቸው ብቁ ድርጅቶች የፍላጎት መግለጫ ሰነዶቻቸውን በአንድ ኦሪጅናል እና በሶስት ኮፒዎች አዘጋጅተው ማቅረብ እንደሚችሉ ተገልል።
የፍላጎት መግለጫ ሰነዶቹ እስከ ህዳር 14 ቀን 2019 ዓ.ም (እ.አ.አ ህዳር 23፣ 2026) ከቀኑ 11:00 ሰዓት ድረስ ባምቢስ ወይም ደምበል አካባቢ ከግሪክ ትምህርት ቤት ፊት ለፊት በሚገኘው የኮርፖሬሽኑ የምህንድስና ግዥ ዳይሬክቶሬት ሶስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 0 መቅረብ አለባቸው።
ስለ እያንዳንዱ ምድብ ዝርዝር ሁኔታ፣ የአገልግሎት ቆይታ ጊዜ እና ተያያዥ መስፈርቶች ሙሉ መረጃውን ከተያያዘው ምስል ላይ መመልከት ይቻላል።


ምንጭ:- የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን















