የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በከተማ አስተዳደሩ በተለያዩ ክ/ከተሞች ተገንብተው በተጠናቀቁ የ40/60 የጋራ ህንጻዎች እና በካፒታል ፕሮጅክት የተገነቡ ንግድ ቤቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በሽያጭ ለማስተላለፍ ከነሃሴ 16 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ የጨረታ ሰነድ በመሸጥ ላይ መሆኑ ይታወቃል፡፡
በመሆኑም ከጨረታ ተሳታፊዎች ፍላጎት በመነሳት እና ለዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ መመለሻ በቂ ጊዜ ለመስጠት ሲባል የጨረታ ሰነድ መሸጫና መመለሻ ጊዜን ማራዘም አስፈላጊ መሆኑ በኮርፖሬሽኑ ስለታመነበት ከመስከረም 08 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለአስራ አምስት/15 ተከታታይ የሥራ ቀናት/ቅዳሜን ሙሉ ቀን ጨምሮ/ የተራዘመ መሆኑን እየገለጽን፤ ጨረታው መስከረም 26 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ተዘግቶ በቅደም ተከተሉ መሠረት ከመስከረም 27 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 1 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ የሚከፈት መሆኑን እናሳውቃለን፡፡



















