የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በተለያዩ ክፍለ ከተሞች ግንባታቸው የተጠናቀቁና መሠረተ ልማት የተሟላላቸውን 545 ባለ አራትና ባለአስራ አንድ ወለል ከፍታ ያላቸውን መኖሪያ ቤቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በሽያጭ ማስተላለፍ እንደሚፈልግ ገልጿል፡፡
ኮርፖሬሽኑ ለጨረታ ያቀረባቸውን መኖሪያ ቤቶች ተወዳድሮ መግዛት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከ04/02/2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 27/02/2017 ዓ.ም ድረስ ባሉት 21 የሥራ ቀናት (ቅዳሜን ሙሉ ቀን ጨምሮ) ከጠዋቱ 1፡30 እስከ ምሽት 12፡30 ድረስ በአካል በመቅረብ የማይመለስ ብር 1000.00/አንድ ሺህ በመክፈል ከዚህ በታች በተገለፁት ቦታዎች መግዛት እንደሚቻል ተገልጿል፡፡
የጨረታ ሰነድ መሽጫ ሥፍራዎች፦
- ቂርቆስ ክ/ከተማ (ባምቢስ አካባቢ)
- የካ ክ/ከተማ (መገናኛ)
- አራዳ ክ/ከተማ (አራት ኪሎ)
- ኮ/ቀራኒዮ ክ/ተማ (ቤተል)
- ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ደቡብ ቅርንጫፍ (ኮ/ቀራኒዮ ክ/ተማ አጃንባ ሳይት)
- ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ምስራቅ ቅርንጫፍ (ለሚ ኩራ ክ/ከተማ በሻሌ ሳይት)


















