7ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ ለተጨማሪ 10 የስራ ቀናት ተራዘመ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ያሰናዳው 7ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ ለተጨማሪ 10 ሥራ ቀናት መራዘሙን የመሬት ሊዝ ጨረታ አስፈጻሚ ኮሚቴ አሳውቋል፡፡
አስፈጻሚ ኮሚቴው በ7ኛ ዙር የሊዝ ጨረታ ሂደት ላይ ባደረገው ውይይትም ከጥቅምት 3/2018 እስከ 14/2018 ዓ.ም በተቋሙ ድረ ገፅ በኦንላይን ሲካሄድ የሰነበተው የጨረታ ሰነድ ሽያጭ በተለያየ ምክንያት ሰነድ ላልገዙ የህብረተሰብ ክፍሎች ተጨማሪ እድል ለመስጠትና የተሳታፊ ቁጥርን ለማሳደግ እንዲቻል በደንብ ቁጥር 162/2016 አንቀጽ 20 መሰረት ከጥቅምት 17/2018 እስከ ጥቅምት 28/2018 ዓ.ም እንዲራዘም ወስኗል፡፡
ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ግለሰብ ሆነ ድርጅት የጨረታ ሰነዱን ከጥቅምት 17/2018 እስከ 28/2018 ዓ.ም እስከ ቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ የተራዘመ መሆኑን በመረዳት የጨረታ ሰነዱን ከቴሌ ብር አካውንት ተቀናሽ አደርጎ ክፍያ በመፈፀም ሰነዱን በlandleasedocument.aalb.gov.et: በኦንላይን በመግዛት እንዲወዳደሩ ጥሪ እያቀረበ የጨረታ ሰነድ መመላሻ ጊዜ በ28/02/2018 ከ2፡30 እስከ 11፡30 ድረስ መሆኑን አሳውቋል፡፡


















