5ኛው የአርኪ የሪል እስቴቶች የቤትና የሱቅ ሽያጭ ኤክስፖ በዛሬው እለት በስካይ ላይት ሆቴል ተከፍቷል። ዘንድሮ ለአምስተኛ ጊዜ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ጥቅምት 16/2018 ዓ.ም በስካይ ላይት ሆቴል በሚካሄደው ኤክስፖ ሁሉም የሪል እስቴት አልሚዎች ታላቅ የቤት ዋጋ ቅናሽን ያደረጉበት መሆኑ ተነግሯል።
አርኪ ሆም ኤክስፖ በስካይ ላይት ሆቴል እና በሚሊንየም አዳራሽ ባዘጋጃቸው አራት ተከታታይ ኤክስፖዎቹ ከሃያ አምስት ሺ በላይ ሰዎች የጎበኙት እንዲሁም ከስምንት መቶ ያላነሱ ሰዎች ቤት የገዙበት ትልቅ የቤት ፈላጊና አልሚዎች የሚገናኙበት ኤክስፖ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
አርኪ ኤቨንት ኦርጋናይዘር ባዘጋጀው በዚህ ኤክስፖ በዘርፉ ላይ የተሰማሩ የቤት አልሚ ድርጅቶች እና አጋር አካላት የተሳተፉ ሲሆን ኤክስፖው መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማትን ፤ አንድ ላይ በማቀናጀት በከተማ እንዲሁም በአገር አቀፍ ደረጃ ሊሰሩ የታሰቡ መዋቅራዊ ቅንጅቶችን ለመፍጠር ምቹ ዕድል የሚፈጥር ገዥና ሻጭን በአንድ ላይ በማገናኘት በቀጥታ የሚፈልጉትን የቤት ዓይነት የሚመርጡበት ስለአጠቃላይ ሂደት በግልፅ መረጃ የሚለዋወጡበት በርካታ አማራጮች ያሉበት ለተረጋጋና ምክንያታዊ የቤት ግዥ ዉሳኔ ምቹና ዓይነተኛ አጋጣሚ ይፈጥራል ተብሏል።
በኢትዮ ሪል እስቴት አዋርድ 2017 ዓ.ም ውጤታማ የሆኑ አልሚዎች የተሳተፉበት መሆኑና በዚህ ኤክስፖ ቤትና ሱቅ የሚገዙ የቤት እቃ በነፃ የሚሸለሙበት መሆኑ እንደሆነ ተነግሯል።
ምንጭ፡ FastMereja


















