ኤሮ አይረን ኮንስትራክሽን ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር በኮንስትራክሽኑ ዘርፍ ክህሎት ያላቸውን ባለሞያዎችን ለማፍራት “ሪቪዚት ኢንስቲቱሽን ኦፍ ዲዛይን” የተሰኘ ማሰልጠኛ ማዕከል መክፈታቸውን መጋቢት 5/2017 ዓም በቤስት ዌስተርን አዲስ ሆቴል በሰጡት መግለጫ አስታውቋል።
ዓለም አቀፍ ደረጃዎችን በተከተለ መልኩ ስልጠናዎችን እንደሚሰጥ የተገለጸ ሲሆን በዚህ የሥራ መስክ በሀገራችን ብዙ ማሰልጠኛ ተቋማት ባለመኖሩ ክፍተቱን ለመሙላት አስተዋጾ ያደርጋል ተብሏል።

ሰልጣኞቹ ስልጠናቸውን ሰልጥነው ሲያጠናቅቁ ተመሳስይ የግንባታ ስራ በሚሰሩ ድርጅቶችና በዚሁ ድርጅት ተቀጥረው የሚሰሩ ከመሆኑም ሌላ ከመቀጠር ይልቅ በራሳቸው መሥራት የሚያስችላቸውን ልምዶችና እውቀቶች እንዲኖሯቸው በማድረግ ስልጠናና ትምህርቱን የሚሰጡ ይሆናል ተብሏል።
ክፍያቸዉን መፈጸም ለማይችሉ ሰልጣኞች ከዳሽን ባንክ ጋር በመሆን እስከ 1 ዓመት የሚቆይ የብድር መክፈያ መንገድ እንዳመቻቸ አስታዉቋል፡፡
ስልጠናዎቹ በቀን፣ በማታ፣ ቅዳሜ እና እሁድን ጨምሮ በኦንላይን የሚሰጡ ናቸዉ፡፡


















