ኩባንያው በተመጣጣኝ ዋጋ ቤቶች ፕሮጀክቱ ቤት ለሌላቸው ዜጎች እጅግ ተመጣጣኝ በሆነ ዋጋ ቤት ለማቅረብ 30 ሺ ቤቶችን በአንድ ዓመት ለመገንባት ውጥን የያዘ ሲሆን በዛሬው ዕለት 1ሺ 800 ካሬ ላይ ባለ 6 ፎቅ ቤት ለመስራት የመሰረት ድንጋይ አስቀምጧል።
በመርሐግብሩ ላይ የመሠረት ድንጋይ ያስቀመጡት የፐርፐዝብላክ ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ፍስሐ እሸቱ እለቱ 365 ሕንጻዎች በዓመት ውስጥ አጠናቀን ለቤት ፈለጊዎች ለማስረከብ የመጀመሪያውን እርምጃ በምንራመድበት ለዚህ ቀን ስላደረሰን እንኳን ደስ አለን ብለዋል።
ስፍራው 1802 ካሬ እንደሆነና ባለ 6 ፎቅ ሕንጻ እንደሚሠራ የገለጹት የፐርፐዝብላክ ኢትዮጵያ የከገበሬው ሪል እስቴት ቺፍ ናኦሊ ዳዲ የመጀመሪያው የተመጣጣኝ ቤቶች የመሠረት ድንጋይ ለማስቀመጥ እንዲቻል ከሐሳብ ጥንሰሳ ጀምሮ መርሐግብሩ እንዲካሔድ የበኩላቸውን ለተወጡ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።
በመርሐግብሩ ላይ የፐርፐዝብላክ ኢትዮጵያ የቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር ኤርሚያስ ብርሃኑ፣ የቦርድ አባላት እና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችም ተገኝተዋል።

















