• BetBegara.com
  • Buy
  • Rent
  • Sale
  • Services
  • Contact Us
Betegna - ቤተኛ | Ethiopian Housing and Real Estate News & Insights
Advertisement
  • Home
  • Guides
    • Buying Guide
    • Renting Guide
    • Selling Guide
    • Knowledge Base
  • Mortgage
  • Technology
  • Legal
    • Proclamations (አዋጅ)
    • Regulations (ደንብ)
    • Directives (መመሪያዎች)
    • Community Complaints
    • Corruption (ሙስና)
  • Tender
    • Auction (ሐራጅ)
    • Land Lease (የመሬት ሊዝ)
    • Request for EOI
  • Project Highlight
  • More
    • Community & CSR
    • Construction & Projects
    • Construction Material Supply
    • Design & Innovation
    • Public Housing
    • Insights & Profiles
    • Sales & Marketing
    • Property Handover
    • Global
    • Contact Us
No Result
View All Result
Sell, Buy, Rent
  • Home
  • Guides
    • Buying Guide
    • Renting Guide
    • Selling Guide
    • Knowledge Base
  • Mortgage
  • Technology
  • Legal
    • Proclamations (አዋጅ)
    • Regulations (ደንብ)
    • Directives (መመሪያዎች)
    • Community Complaints
    • Corruption (ሙስና)
  • Tender
    • Auction (ሐራጅ)
    • Land Lease (የመሬት ሊዝ)
    • Request for EOI
  • Project Highlight
  • More
    • Community & CSR
    • Construction & Projects
    • Construction Material Supply
    • Design & Innovation
    • Public Housing
    • Insights & Profiles
    • Sales & Marketing
    • Property Handover
    • Global
    • Contact Us
No Result
View All Result
Betegna - ቤተኛ | Ethiopian Housing and Real Estate News & Insights
No Result
View All Result
ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞች ተጨማሪ 5 ሺህ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ሊገነባ መሆኑ ተገለፀ

መንግሥት የመኖሪያ ቤቶችን እየገነባ የቤት ባለቤት ማድረግ አይችልም – አዳነች አቤቤ

Betegna Team by Betegna Team
March 21, 2024
in Public Housing
A A
0
0
SHARES
Share on FacebookShare on LinkedIn

በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ያለውን የመኖሪያ ቤቶች ችግር ለማቃለል አስተዳደሩ በአማራጭነት ባቀረባቸው የተለያዩ አማራጮች በመጠቀም የመኖሪያ ቤቶችን መገንባት እንደሚቻልና ኅብረተሰቡም በዚህ ዕድል ተጠቃሚ መሆን እንደሚችል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ጥሪ አስተላለፉ፡፡ 

ከንቲባዋ ይህንን የገለጹት ሰሞኑን ሰንሻይን ኮንስትራክሽን የገነባቸውን አምስት ሺሕ ቤቶች ለተጠቃሚዎች ባስተላለፈበት ፕሮግራም ላይ ነው፡፡ እንደ ወ/ሮ አዳነች አበቤ ገለጻ፣ መንግሥት የመኖሪያ ቤቶችን እየገነባ የቤት ባለቤት ማድረግ የማይችል በመሆኑ አስተዳደሩ አዲስ በቀረጻቸው የመኖሪያ ቤቶች ግንባታ ፕሮግራም ላይ ተሳታፊ መሆን የሚቻልበት ዕድል ማመቻቸቱን አመልክተዋል፡፡ በከተማዋ ነዋሪዎች በዋነኛነት የሚነሳው የመኖሪያ ቤት ችግር መሆኑን ያመለከቱት ከንቲባዋ አስተዳደሩም ይህንን ጉዳይ ከሁሉም በላይ በአንገብጋቢነት እንደሚመለከተው ገልጸዋል፡፡ በመሆኑም የቤት ችግርን ለመቅረፍ የሚያስችሉ የተለያዩ የአማራጮች እየተተገበሩ መሆኑን በማስታወስ የከተማው ነዋሪም እነዚህን አማራጮች መጠቀም እንደሚችል አስረድተዋል፡፡ 

ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞች ተጨማሪ 5 ሺህ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ሊገነባ መሆኑ ተገለፀ

እንደ ከንቲባዋ ገለጻ የተቀየሱት አማራጮችን በመጠቀም የመኖሪያ ቤት ችግርን ለመፍታት በመንግሥትና በግሉ ዘርፍ በርካታ ሥራዎች እየተሠሩ ቢሆንም አሁንም የመኖሪያ ቤት አቅርባትና ፍላጎቱ ግን ሊጣጣም አልቻለም፡፡ በመሆኑም ይህንን ለማጣጣምና የመኖሪያ ቤት አቅርቦቱን ለመጨመር በርካታ የቤት አቅርቦት ፕሮግራሞች በመቅረጽና አስፈላጊው የፖሊሲና የሕግ ማዕቀፍ ወጥቶለት አብሮ የማልማት እንቅሰቃሴ መጀመሩን ተናግረዋል። በዚህም መሠረት የከተማ አስተዳደሩ አቅም ላላቸው የከተማው ነዋሪዎች፣ ለባለሀብቶች፣ ለግል አልሚዎችና ሌሎችም በዚህ ሥራ መሳተፍ የሚችሉትን ሁሉ በማበረታታት ላይ የሚገኙ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡ 

በእነዚህ የቤት ግንባታ አማራጮች ለመሳተፍ የሚፈልጉ በሩ ክፍት ስለመሆኑ በመግለጽም አስተዳደሩ በአማራጭነት ባቀረባቸው የቤት ግንባታ አሠራሮች ኅብረተሰቡ ተሳታፊ ይሆን ዘንድም ጥሪ አቅርበዋል፡፡ አስተዳደሩ በአማራጭነት ካቀረባቸው የቤት ማልሚያ ፕሮግራም ውስጥ አንዱ በፓርትነርሺፕ ወይም በአጋርነት አብሮ መሥራት በቀዳሚነት ጠቅሰዋል፡፡ ሁለተኛ በሪል እስቴት መሬት ሳይሸጥ ዓላማው ሳይቀር በዕለቱ አምስት ሺሕ ቤቶችን እንዳስተላለፈው ሰንሻይን ኮንስትራክሽን የተሰጠውን መሬት አልምቶ ለተፈለገው ዓላማ ማዋል መቻል እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

የተረከቡት መሬት ዓላማው ሳይቀር ለተፈለገው ዓላማ መዋል የሚችል ከሆነ አስተዳደሩ የሚያበረታታ ስለመሆኑም ጠቅሰዋል፡፡ ኅብረተሰቡ በአማራጭነት ሊጠቀምበት ይችላል ብለው ሦስተኛ አማራጭ ብለው የገለጹት በማኅበር ተደራጅቶ ቤት መሥራትን ነው፡፡ አራተኛው አማራጭ ደግሞ ከሦስቱ አማራጮች ለየት ባለ መንገድ የሚተገበር ነው፡፡ ይህም ቤት የሚፈልጉ መሬት ያላቸው ገንዘብ ግን የሌላቸው ነዋሪዎች ገንዘብ ካለው አልሚ ጋር በአጋርነት አብረው ማልማት የሚችሉበት ዕድል የተመቻቸ መሆኑ ነው፡፡ አምስተኛ አማራጭ ደግሞ መንግሥት ራሱ እንዲገነባ የሚያቀርበው እንደሆነ ጠቅሰዋል፡፡ እነዚህ አማራጮች የከተማዋን ዲዛይን በጠበቀ መልኩ የሚገነቡ እስከሆነ ድረስ አስተዳደሩ ድጋፍ የሚያደርግባቸው አዳዲስ አሠራር ስለመሆናቸው ከገለጻቸው ለመረዳት ተችሏል፡፡ 

‹‹በየትም አገር የቤት አቅርባት እየጨመረ እንዲሄድ ይደረጋል እንጂ መንግሥት እየገነባ ሁሉንም ነዋሪ የቤት ባለቤት ማድረግ አይችልም፣ በየትኛውም ዓለም አልተደረገም፤›› ያሉት ከንቲባዋ ነገር ግን አዲስ አበባ የቤት አቅርባትን የሚያስችሉ አቅሞቻችንን ማቀናጀት በጋራ ማልማት የሚቻል ስለመሆኑም ገልጸዋል፡፡ 

አሁንም አስተዳዳሩ ይህንን ሥራ ለማጠናከር እየሠራ ሲሆን በዕለቱ የሰንሻይን ኮንስትራክሽን አምስት ሺሕ ቤቶች ሠርቶ በማስረከቡ በከተማችን በዚህን ያህል ቁጥር የቤት አቅርቦት መጨመር ያስቻለ መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡ ሰንሻይን ይህንን ያህል ገንብቶ ቤቶቹን ማስተላለፍ የቻለው መሬቱ ስላልተለወጠ ለተፈለው ዓላማ ስለዋለ መሆኑና ይህም 3.8 ሔክታር መሬት በነፃ አስተዳደሩ የቀረበ መሆኑን አስታውሰዋል፡፡ እንዲህ በትብብር ከተሠራ ውጤታማ መሆን ይቻላልም ማለትም አሁንም ወደፊትትም ቤት ለማልማት አቅሙና ፍላጎቱ ያላቸው በትክክል ማቅረብና መተግበር ለሚችሉ አስተዳደሩ በነፃ መሬት ባያቀርብም በበርካታ ማበረታቻዎችን የሚሰጡና የሚደግፉ መሆናቸውም አስታውቀዋል፡፡ ከንቲባዋ እነዚህ አማራጮች ሌላ ኩባንያዎች ለሠራተኞቻቸው ቤት መገንባት የሚችሉ ከሆነ ይህንን ለማበረታታት ቦታ የሚያቀርቡ እንደሆነም በሰሞኑ ንግግራቸው አስታውቀዋል፡፡ 

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለሠራተኞቹ አምስት ሺሕ ቤቶችን ለማስገንባት የመሠረት ድንጋይ የማስቀመጥ ፕሮግራም ላይ የተገኙት ወ/ሮ አዳነች ኩባንያዎች ለሠራተኞች ቤት መገንባት የሚፈልጉ ከሆነ ይበረታታሉ ብለዋል፡፡ 

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የወሰደውን ዕርምጃ በምሳሌነት በመጥቀስ በከተማ ውስጥ በርካታ ትልልቅ ኩባንያዎች ስላሉ ለሠራተኞቻቸው ቤት በመገንባት የቤት አቅርባትን ችግር ለማቃለል ለሚያደርጉት ጥረት አስተዳደሩ መሬት የሚያቀርብ በመሆኑ ኩባንያዎች ይህንንም የቤት ማልሚያ መንገድ በመጠቀም መገንባት እንደሚችሉ ተናግረዋል፡፡ 

አስተዳደሩ በአማራጭነት ካቀረባቸው አሠራሮች ውስጥ በተለይ ከግሉ ዘርፍ ጋር በጋራ ለማልማት በተቀረጸው ፕሮግራም 70 የሚሆኑ አልሚዎች ከአስተዳደሩ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ያደረጉ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ የተወሰኑት ወደ ሥራ የገቡ ሲሆን ቀሪዎቹም በዝግጅት ላይ እንደሆኑ ለማወቅ ተችሏል፡፡ እንዲህ ላሉ የቤት ልማቶች አስተዳደሩ 1,500 ሔክታር መሬት መዘጋጀቱም መገለጹ ይታወሳል፡፡ 

አስተዳደሩ ባለፈው ዓመት መጨረሻ ላይ እንዳስታወቀው በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ የተመዘገቡ ቤት ፈላጊዎች ቁጥር ከ600 ሺሕ በላይ ደርሰዋል፡፡ ባለፉት 20 ዓመታት ደግሞ በመንግሥት የተገነቡ ቤቶች 316 ሺሕ ሲሆኑ በዚህ የግንባታ ሒደት የቤት ፍላጎትን መሙላት እንደማይችልም በመታሰቡ አስተዳደሩ በአማራጭነት በቀረቡ የቤት ማልሚያ ፕሮግራሞች እየተሳተፉ ያሉ አልሚዎች የቤት ችግርን ለማቃለል ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋሉ ተብሎም ታምኖበታል፡፡ 

ከዚሁ አንፃር በከተማዋ እየተካሄደ ያለውን የቤቶች ልማት በተመለከተ በ2016 በሙሉ በጀት ዓመቱ ግንባታቸውን ለማስጀመር ከታቀዱት 120 ሺሕ ቤቶች በግማሽ ዓመቱ ውስጥ 99113 ቤቶች ማልማት መቻሉን ከንቲባዋ በቅርቡ የስድስት ወር የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት መጥቀሳቸው ይታወሳል፡፡ 

ከዚህም ሌላ በበጀት ዓመቱ 111 ሺሕ ቤቶችን ለመገንባት የሚያስችል የአጋርነት ውልና የመሬት ዝግጅት እየተከናወኑ ስለመሆናቸውም ጠቅሰዋል፡፡ እንዲህ ባሉ በአጋርነት ቤት በማልማት ሥራዎች በሪል እስቴት ኩባንያዎችና በግለሰብ አልሚዎች በግማሽ ዓመቱ ውስጥ አሥር ሺሕ ቤቶች መገንባታቸውን ጠቅሰዋል፡፡ 

በግለሰብና በሪል እስቴት ኩባንያዎች ከተገነቡት አሥር ሺሕ ቤቶች ሌላ በመንግሥት በጀት 4,200 በበጎ አድራጊ ግለሰቦችና ኩባንያዎች በኩል ደግሞ 5023 ቤቶች በአጠቃላይ 19,223 ቤቶች ስለመገንባታቸውም ጠቅሰዋል፡፡ 

Tags: Adanech Abiebie
Previous Post

የመሬት ይዞታ የሚለቀቅበትን ሁኔታ ለመወሰን የወጣው አዋጅ ለቋሚ ኮሚቴው ተመራ

Next Post

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ተተኪ ቦታ ሳይሰጠው 980 ቤቶች እንደፈረሱበት ተገለጸ

Betegna Team

Betegna Team

Betegna - ቤተኛ, is a media platform that focuses on Ethiopian housing and real estate news, developments, technology, policies, and lifestyle.

ተዛማጅ ጽሑፎች

በ5 ዓመታት ቤቶችን ገንብተን ለማስረከብ የገባነውን ቃል በተግባር ለማረጋገጥ እየተጋን ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
Public Housing

በ5 ዓመታት ቤቶችን ገንብተን ለማስረከብ የገባነውን ቃል በተግባር ለማረጋገጥ እየተጋን ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

November 13, 2026
የ1.5 ሚሊዮን መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት ወደ ተግባር ምዕራፍ ተሸጋግሯል
Public Housing

የ1.5 ሚሊዮን መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት ወደ ተግባር ምዕራፍ ተሸጋግሯል

November 12, 2026
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከዩኤን ሃቢታት ዋና ዳይሬክተር አናክላውዲያ ሮስባክ ጋር መወያየታቸውን ገለፁ
Public Housing

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከዩኤን ሃቢታት ዋና ዳይሬክተር አናክላውዲያ ሮስባክ ጋር መወያየታቸውን ገለፁ

November 11, 2026
Next Post
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ተተኪ ቦታ ሳይሰጠው 980 ቤቶች እንደፈረሱበት ተገለጸ

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ተተኪ ቦታ ሳይሰጠው 980 ቤቶች እንደፈረሱበት ተገለጸ

  • Trending
  • Comments
  • Latest
የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የወጣ አዋጅ 721/2004

የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የወጣ አዋጅ 721/2004

April 23, 2024
ስለ ግብር የሚከፈልበት የቤት ኪራይ ገቢ

ስለ ግብር የሚከፈልበት የቤት ኪራይ ገቢ

April 6, 2024
በአዲስ አበባ የቤት ሽያጭ ዋጋ ተመን ላይ በድጋሚ ማሻሻያ ተደረገ

በአዲስ አበባ የቤት ሽያጭ ዋጋ ተመን ላይ በድጋሚ ማሻሻያ ተደረገ

April 3, 2024
የመሬት ልማትና አስተዳር ደንብ ቁጥር 163/2016

የመሬት ልማትና አስተዳር ደንብ ቁጥር 163/2016

April 22, 2024
ስለ ሪል እስቴት ምን ያውቃሉ?

ስለ ሪል እስቴት ምን ያውቃሉ?

August 18, 2023
Home pic

ቤት ለሚገዙ እና ለሚሸጡ አካላት ማሳሰቢያ ተሰጠ

0
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤት አቅርቦትን ለማሳደግ የሚያስችል ውይይት ከሪል እስቴት አልሚዎች ጋር ውይይት አደረገ!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤት አቅርቦትን ለማሳደግ የሚያስችል ውይይት ከሪል እስቴት አልሚዎች ጋር ውይይት አደረገ!

0
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ያስተዋወቀበትን የገርጂ መኖሪያ መንደር ፕሮጀክት ሊያስመርቅ ነው

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ያስተዋወቀበትን የገርጂ መኖሪያ መንደር ፕሮጀክት ሊያስመርቅ ነው

0
ባለ 9 ወለል ህንፃ በተጀመረ በ69ኛ ቀኑ ተጠናቀቀ!!

ባለ 9 ወለል ህንፃ በተጀመረ በ69ኛ ቀኑ ተጠናቀቀ!!

0
ስለ ሪል እስቴት ምን ያውቃሉ?

ስለ ሪል እስቴት ምን ያውቃሉ?

0
የሪል እስቴት አልሚዎች ማህበር የ7% የብድር ወለድ ጥያቄ በባለሙያዎች መካከል ያስነሳው ክርክር

የሪል እስቴት አልሚዎች ማህበር የ7% የብድር ወለድ ጥያቄ በባለሙያዎች መካከል ያስነሳው ክርክር

November 18, 2026
በጋዜቦ አደባባይ አካባቢ በግንባታ ሂደት ላይ ከነበረ ሕንጻ ላይ የወደቁ ሦስት ሠራተኞች ሕይወታቸውን አጡ

በጋዜቦ አደባባይ አካባቢ በግንባታ ሂደት ላይ ከነበረ ሕንጻ ላይ የወደቁ ሦስት ሠራተኞች ሕይወታቸውን አጡ

November 14, 2026
በ5 ዓመታት ቤቶችን ገንብተን ለማስረከብ የገባነውን ቃል በተግባር ለማረጋገጥ እየተጋን ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

በ5 ዓመታት ቤቶችን ገንብተን ለማስረከብ የገባነውን ቃል በተግባር ለማረጋገጥ እየተጋን ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

November 13, 2026
የ1.5 ሚሊዮን መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት ወደ ተግባር ምዕራፍ ተሸጋግሯል

የ1.5 ሚሊዮን መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት ወደ ተግባር ምዕራፍ ተሸጋግሯል

November 12, 2026
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከዩኤን ሃቢታት ዋና ዳይሬክተር አናክላውዲያ ሮስባክ ጋር መወያየታቸውን ገለፁ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከዩኤን ሃቢታት ዋና ዳይሬክተር አናክላውዲያ ሮስባክ ጋር መወያየታቸውን ገለፁ

November 11, 2026

ብዙ የተነበቡ

  • የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የወጣ አዋጅ 721/2004

    የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የወጣ አዋጅ 721/2004

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ስለ ግብር የሚከፈልበት የቤት ኪራይ ገቢ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአዲስ አበባ የቤት ሽያጭ ዋጋ ተመን ላይ በድጋሚ ማሻሻያ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የመሬት ልማትና አስተዳር ደንብ ቁጥር 163/2016

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ስለ ሪል እስቴት ምን ያውቃሉ?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Categories

  • Community & CSR (28)
  • Construction & Projects (29)
  • Construction Material Supply (9)
  • Design & Innovation (18)
    • Architecture (2)
    • Technology (14)
  • Global (4)
  • Insights & Profiles (20)
  • Legal Updates (89)
    • Community Complaints (8)
    • Corruption (ሙስና) (2)
    • Directives (መመሪያዎች) (1)
    • Proclamations (አዋጅ) (7)
    • Regulations (ደንብ) (2)
  • Mortgages & Finance (14)
  • Property Handover (16)
  • Public Housing (71)
  • Real Estate Guides (13)
    • Buying Guide (3)
    • Knowledge Base (1)
    • Renting Guide (2)
    • Selling Guide (7)
  • Sales & Marketing (67)
  • Tenders & Bids (60)
    • Land Lease (29)
    • Request for EOI (1)
  • Home
  • Guides
  • Mortgage
  • Highlights
  • Legal Updates
  • Tenders & Bids
Betegna Logo Footer

Betegna – ቤተኛ, powered by Betbegara.com, is a media platform that focuses on Ethiopian housing and real estate news, developments, technology, policies, and lifestyle.

© 2026 Betegna – ቤተኛ | Ethiopian Housing and Real Estate News & Insights

  • Home
  • Guides
    • Buying Guide
    • Renting Guide
    • Selling Guide
    • Knowledge Base
  • Mortgage
  • Technology
  • Legal
    • Proclamations (አዋጅ)
    • Regulations (ደንብ)
    • Directives (መመሪያዎች)
    • Community Complaints
    • Corruption (ሙስና)
  • Tender
    • Auction (ሐራጅ)
    • Land Lease (የመሬት ሊዝ)
    • Request for EOI
  • Project Highlight
  • More
    • Community & CSR
    • Construction & Projects
    • Construction Material Supply
    • Design & Innovation
    • Public Housing
    • Insights & Profiles
    • Sales & Marketing
    • Property Handover
    • Global
    • Contact Us
No Result
View All Result
Sell, Buy, Rent