የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ በ2005 ዓ.ም በአዲስ እና በነባር ኮንደሚኒም ቤት ተመዝግበው ሲቆጥቡ ከነበሩ ቤት ፈላጊዎች ውስጥ አቅም እና ፍላጎት ያላቸውን ተመዝጋቢዎች በጋራ መኖሪያ ህንፃ የቤት ማህበር ተደራጅተው ቤት መገንባት እንዲችሉ መዝግቦ በማህበር መሬት ማስረከቡ ይታወቃል፡፡
በመሆኑም ተደራጅተው መሬት ከተረከቡ እና መሬት ለመረከብ ከሚጠባበቁ ማህበራት ውስጥ በተለያዩ ምክንያቶች አባላት ሲወጡ ለመተካት እንዲቻል የተጠባባቂዎች ምዝገባ ማድረግ አስፈልጓል፡፡
በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ እና በቤት ማህበር ተደራጅታችሁ ቤት ለመስራት / ፍላጎት ያላችሁ የ2005 ዓ.ም ተመዝጋቢዎች ብቻ በተዘጋጀው ሲስተም በቢሮ ቴሌግራም ገፅ ላይ ሊንኩን በመጠቀም ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናቶች ውስጥ እስከ ጥቅምት 8/2018 ዓ.ም ድረስ ብቻ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ለመመዝገብ የሚስፈልጉ መስፈርቶች
- በ2005 ዓ.ም በነባር እና አዲስ ኮንደሚኒየም ቤት የተመዘገበ እና እየቆጠበ የሚገኝ፡፡
- ለቤት ግንባታ የሚውለውን 70 በመቶ ገንዘብ በወቅታዊው ማህበራቱ እያስገነቡ በሚገኝበት የገበያ ዋጋ መሰረት መክፈል የሚችል እና ቀሪውን 30 በመቶ ቢሮው ባመቻቸው መሰረት ከባንክ ለመበደር ፍቃደኛ የሆነ።
ማሳሰቢያ
1 ምዝገባው
የሚደረገሁ በኦንላይን ብቻ በመሆኑ ቢሮ መምጣት አያስፈልግም (የሞባይል ስልክን ተጠቅሞ መመዝገብ ይችላሉ)
የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ
በ70/30 የጋራ ህንፃ ማህበር ቤት በተጠባባቂነት መመዝገቢያ የኦንላይን ሊንክ:
https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSfPZUc1SrNdhK9sETiypT9cjZT7jebHtAWnLmP43EhXPDjwuQ/viewform
ምንጭ፡ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ


















