የሪል እስቴት የሽያጭ ሰራተኞች በገንዘብ አቅርቦት እጥረት በሚፈተነው የሪል እስቴት ልማት ውስጥ ለአልሚዎች በቅናሽ ገንዘብ አቅራቢ ባለውለታዎችም ጭምር ናቸው።
ከባንክ በዓመት በ18+% ወለድ ለማግኘት የከበደን ብድር አንድ ጊዜ ብቻ በሚከፈል በአማካኝ ከ5% በማይበልጥ የአንድ ጊዜ ክፍያ የሚያቀርቡ የሪል እስቴት ልማት አጋሮች ናቸው።
ብዙዎች የሚከፈለውን ክፍያ መጠን እንጂ የስራውን ክብደትና ያላውን ፍጋት ለማስተዋወቅ የሚወጣውን ወጪ አንድ ገዢ ለማግኘት በመቶዎች የሚቆጠር ዕጩ ገዢን ማነጋገር እንደሚፈልግ አይረዱትም።
የስራውን ዝርዝር በጥቂቱ ለማሳየት ያክል ጥቂት እንበል
አንድ የሽያጭ ሰራተኛ የሚከተሉትን እንዲተገብር ይጠበቅበታል:-
- ማስተዋወቅ:- በመደበኛ ሚዲያ ፣በማህበራዊ ሚዲያ፣ በጋዜጦች፣ በበራሪ ጽሁፎች፣ በአውደ ርዕይ፣ በተለያዩ መድረኮች
- ልየታ:- በማስተዋወቅ ሂደት የሚመጡትን ደንበኞች እውነተኛ ገዢዎችን መለየት፣ ይሽጥልኝ ብለው የሚመጡ ቤቶችን ገምግሞ ገበያው ሊቀበለው የሚችል መሆኑንና አለመሆኑን መለየት
- የጉብኝት ጉዞ:- ቤት ገዢዎች በመጡ ቁጥር ሳይቶችን ሄዶ ማስጎብኘት ይጠበቅባቸዋል
- ማስረዳት :- ለሽያጭ ስለሚያቀባቸው ቤቶች (ፕሮጀክት) ይዘት፣ ስለ አልሚው ድርጅት ፣ ስለ ክፍያ ሁኔታ፣ ስለ ሽያጭውል.. ጠንቅቆ አውቆ ለዕጩ ገዢዎች በስልክም በአካልም በጽሁፍም ማስረዳት ይጠበቅባቸዋል
- መርዳት:- የቤት ግብይት ሁል ጊዜ የሚተገበር ባለመሆኑ ለመግዛት የወሰኑ ሰዎች ስለቤት ግብይት ሂደት ግራ ሊጋቡና እርዳታ ሊፈልጉ ይችላሉ ። በዚህ ወቅት የሽያጭ ሰራተኞች በግብይት ሂደቱ ገዢዎችን እንዲረዱ ይጠበቅባቸዋል።
- ማደራደር:- ድርድር አንድ የሪል እስቴት ግብይት አካል ሲሆን በሻጭና ገዢ መካከል የሚደረገው ድርድር በ ሽያጭ ባለሙያዎች እንዲመራ ስለሚጠበቅ የማደራደር ሀላፊነት አለባቸው።
- ውል ማፈራረም:- የግብይት ሂደቱ በሽያጭ ባለሙያዎች በኩል ተጠናቀቀ የሚባለው ገዢና ሻጭ በቀረበው ውል ላይ ተስማምተው ሁለቱም የሽያጭ ውሉን ሲፈርሙ በመሆኑ የማፈራረም ሂደቱን የማስፈጸም (የመከታተል)ግዴታ አለባቸው።
- መከታተል:- ከግብይት በኋላም ቀጣይ ክፍያዎችም የመከታተል ሀላፊነት አለባቸው።
ይህ ሁሉ ሆኖ በቅናሽ ለአልሚዎች ከሚያስገቡት ገቢ የሚከፈላቸው መጠን ሲወራ ብዙ ቢመስልም ከልፋታቸው አንጻር እጅግ አናሳ የሚባል ነው።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የሰሩበት ኮሚሽን አከፋፈል ላይ ታማኝ ሆነው በጊዜ የሚከፍሉ አልሚዎች በጣም ጥቂቶች ናቸው። አንዳንዶቹ አዘግይተው በጣም ጥቂቶቹ ደግሞ እጅግ በጣም አዘግይተው ነው የሚከፍሏቸው።
ይህ ብዙ የተወራበት ብዙ የሚፈጋበት የስራ ዘርፍ የስራውን ክብደት ያገናዘበ በድርድር የሚወሰን ከፍ ያለ ኮሚሽን የሚከፈልበት ባለሙያዎቹም የላባቸውን ዋጋ በተገቢው ሁኔታ የሚከፈልበት አሰራር ሊኖር ይገባል። እነሱም ተባብረው ማህበር መስርተው ለመብቶቻቸው መከበር ሊታትሩ ይገባል እላለሁ።
በደሳለኝ ከበደ
ሲቪል መሀንዲስ፣ ሪል እስቴት አማካሪ፣ አሰልጣኝ እና ጸሀፊ


















