የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ 381 የመኖሪያ ቤቶችን ለሀገር ባለውለታዎችና አቅመ ደካሞች አስተላልፈዋል።
ከንቲባዋ በንፋስ ስልክ ላፍቶ እና በቂርቆስ ክፍለ ከተሞች በተገነባ ባለ 5 ወለል ህንፃ የሚገኙ ቤቶችን ነው ያስተላለፉት፡፡
የቤት ስጦታ ከተሰጣቸው የሀገር ባለውለታዎች መካከል ታዋቂው ደራሲ ሀብታሙ አለባቸው እና የአብዲሳ አጋ ልጅ ኤልያስ አብዲሳ ይገኙበታል፡፡
ከንቲባ አዳነች በዚሁ ወቅት እንዳሉት÷ አዲስ አበባን ለኑሮ ምቹ ከማድረግ ባለፈ በሁለንተናዊ መልኩ ነዋሪዎቿን ተጠቃሚ ለማድረግ ዘርፈ ብዙ ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡
በዚህም የከተማዋን ነዋሪዎች የቤት ባለቤት የማድረግ ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።


















