የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር በሶማሌ ብሔራዊ ክልል ደጋሀቡር ከተማ በ28 ሚሊዮን ብር ወጪ ያስገነባውን የአቅመ ደካሞች ቤት ዛሬ ለባለቤቶቹ አስረከበ፡፡
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በ2017 በጀት ዓመት በያዘው የሰው ተኮር ተግባር እቅድ በሶማሌ ብሔራዊ ክልል ደጋሀቡር ከተማ 20 የአቅመ ደካሞች መኖሪያ ቤቶችን ከነሙሉ ግቢያቸው ከ28 ሚሊዮን ብር በላይ በፈጀ ወጪ አስገንብቶ ማስረከቡን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር ገልጸዋል፡፡
ዛሬ ተመርቆ ርክክብ የተደረገው የቤቶች ግንባታ መንግስት እንደሀገር የያዘው የሰው ተኮር ተግባር አካል ነው የሉት ሚኒትሩ የዜጎችን ኢኮኖሚ ከማጠናከር ባለፈ የስነ ልቦና ጥንካሬንም የሚሰጥ ነው ብለዋል፡፡
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ መሰል ስራዎችን ሲሰራ ይህ 3ኛ ዙር ሲሆን በአጠቃላይ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ከ 97 መኖሪያ ቤቶችን አስገንብቶ ለአቅመ ደካሞች አስረክቧል፡፡
ምንጭ፡ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር


















