ይህ የተገለፀው ከንቲባ አዳነች አቤቤ በጉለሌ ክፍለ ከተማ የተገነቡ የተቀናጀ የልማት ስራዎችን መርቀው አገልግሎት ባስጀመሩት ሥነ ስርአት ነው፡፡
አገልግሎት የጀመሩት የልማት ስራዎች የመኖሪያ ቤት፣ የእንጀራ ፋብሪካ፣ የወተት ምርት፣ የምገባ ማዕከል እንዲሁም መንገድን ያካተቱ ናቸው።
ጉለሌ የመኖሪያ መንደር ተብሎ የመጠሪያ ሥም የተሰጠው ይህ የመኖሪያ መንደር በከተማ መስተዳድሩ የተገነባ ነው።
ስለ ጉለሌ የመኖሪያ መንደር
- ባለ 5 ወለል አምስት ህንፃዎች
- 200 አባወራዎችን የሚይዙ
- ሁሉም ቤቶች ዘመናዊ ሆነው የተሰሩ ሲሆን የመኖሪያ መንደሩ ውብ ምድረ ጊቢ አረንጏዴ ስፍራዎች ያካተተ ነው
- በአጠቃላይ 14 ሺሕ 625 ካሬ ላይ ያረፈ ነው

እንጦጦ አካባቢ ለሚገኙ የደሃ ደሃ ለሆኑ እና ጫካ ውስጥ በማይመቹ ቦታዎች ሲኖሩ ለነበሩ የተለዩ እናቶች የከተማ አስተዳደሩ ካስገነባቸው የጉለሌ የመኖሪያ ቤቶች ውስጥ 44 ቤቶችን በመግዛት ድጋፍ ያደረጉት የሚከተሉት ናቸው።
- ቲ ኤን ቲ ኮንስትራክሽን – በ16.8 ሚሊዮን ብር አሰር ስቱዲዮ
- ቶኩማ ስታር ቢዝነስ – በ8.5 ሚሊዮን ብር ሁለት ስቱዲዮ እና ሁለት ባለ አንድ መኝታ
- መሃመድ ሱጃጃ – በ10 ሚሊዮን ብር አምስት ስቱዲዮ
- ጌታመሳይ ዘመድኩን – በ8.5 ሚሊዮን አምስት ስቱዲዮ
- ኤም ደብልዩ አስ ትሬዲንግ – በ8.5 ሚሊዮን ብር አምስት ስቱዲዮ
- ቲ ኤፍ ጂ ጀኔራል ትሬዲንግ- በ8.5 ሚሊዮን ብር አምስት ስቱዲዮ
- ኖህ ሪል እስቴት- በ5.3 ሚሊዮን ብር ሁለት ባለአንድ መኝታ ቤቶች
- ዲሪባ ደፈርሻ – በ4.2 ሚሊዮን ብር አንድ ስቱዲዮ እና አንድ ባለ አንድ መኝታ
- ማህደር ገብረመድህን ኃ/የተ/የግ/ ኩባኒያ – 4.2 ሚሊዮን ብር አንድ ስቱዲዮ እና አንድ ባለ አንድ መኝታ
- አኮርዲያ ኢንቨስትመንት ግሩፕ- በ1.6 ሚሊዮን ብር አንድ ስቱዲዮ

ከላይ የተጠቀሱት ተቋማት እና ግለሰቦች በጠቅላላው 74.6 ሚሊዮን ብር የግንባታ ወጪ በመሸፈን 44 የመኖሪያ ቤቶችን ለአቅመ ደካማ የአካባቢው ነዋሪዎች ስላበረከቱ እያመሰገንን፣ በቀጣይም ድጋፍ ለማድረግ የምትፈልጉ ልበ-ቀና ባለሃብቶች የበኩላችሁን አስተዋፅዖ እንድትወጡ ጥሪያችንን እናቀርባለን ብለዋል ከንቲባ አዳነች አቤቤ።


















