ቢጂአይ ኢትዮጵያ ከፐርፐዝብላክ ኢትዮጵያ ጋር የነበረውን የዋናው መሥሪያ ቤት ሽያጭ መቋረጡን ትናንት አመሻሽ ላይ ለመገናኛ ብዙኃን በላከው መግለጫ አስታውቋል።
ይህን አስመልክቶ ፐርፐዝብላክ ኢትዮጵያ ዛሬ ረፋድ መግለጫ ሰጥቷል።
ሁለቱ ኩባንያዎች ባደረጉት ስምምነት መሠረት 1 ቢሊዮን ብር ፐርፐዝብላክ ቅድመ ክፍያ መፈጸሙን አስታውሷል።
ክፍያው በሦስት ዙር የሚፈፀም ሲሆን ሁለተኛው ዙር ክፍያ የሚፈጸመው በውልና ማስረጃ ሲፈራረሙ እንደሚሆን ቀድመው በፈጸሙት ውል ላይ መቀመጡን ነው ፐርፐዝብላክ ያስታወቀው።
ፐርፐዝብላክ በሳለፍነው ቅዳሜ የካቲት 23 2016 ዓ.ም በውልና ማስረጃ እንዋዋል የሚል ደብዳቤ ልኮላቸው እንደነበርና ቢጂአይ ከግብር ጋር በተያያዘ ሕጋዊ መስፈርቶችን ማሟላት ባለመቻላቸው ፈቃደኛ አለመሆናቸውን የፐርፐዝብላክ የቦርድ አባልና የሕግ አማካሪ ዶ/ር ኤርምያስ ብርሃኑ ገልጸዋል።
አንድ ቢልዮን ብር ቀብድ የተከፈለበት ህንፃ ሽያጭ ተቋረጠ::
ይህ ባለበት ሁኔታ ቢጂአይ ውሉን አቋርጫለሁ ማለቱ ተገቢ አለመሆኑንና ጉዳዩ በሕግ እንደሚታይ የፐርፐዝብላክ ኢትዮጵያ የሕግ አማካሪ ዶ/ር ኤርምያስ ብርሃኑ ገልጸዋል። ፐርፐዝብላክ አሁንም ግዢውን ለመፈጸም ፈቃደኛም ቁርጠኛም መሆኑን ነው የገለጹት።
ሁለቱ ኩባንያዎች ያደረጉት ውል በውልና ማስረጃ እንዲፈጸም ቢጂአይ ኢትዮጵያ ፈቃደኛ እንዳልነበረ ዶ.ር ኤርምያስ ገልጸዋል።
ስለ ጉዳዩ ዝርዝር መረጃ በቀጣይ አርብ የካቲት 29 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ ተገልጿል።
ምንጭ፦ ፐርፐዝብላክ ሚዲያ


















