የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ፒያሳ ከአድዋ መታሰቢያ ፊት ለፊት የሚገኘውንና የኤሌክትሪክ ህንፃ በመባል የሚታወቀውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና መ/ቤት የነበረውን ህንጻ ከዚህ በፊት ፒያሳ አካባቢ የተለያዩ የንግድ አገልግሎት ሲሰጡ ለነበሩ የወርቅ መሸጫ ሱቆች፣ ባቅላባ ቤት፣ የመዋቢያ እቃ መሸጫ ሱቆች፣ የእጅ ሰዓት መሸጫ፣ አልባሳት መሸጫ ቤቶች፣ ኬክ ቤቶች፣ የቡና ቤቶች (Coffee House) እና ሌሎች በአካባቢው የንግድ አገልግሎት ሲሰጡ ለነበሩ ድርጅቶች ቅድሚያ በመስጠት ማከራየት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉና በዚሁ አካባቢ ከላይ በተገለጹት የንግድ ዘርፍ አገልግሎት ስትሰጡ ስለመሆኑ ከሚመለከተው አካል የተረጋገጠ ማስረጃ በማቅረብ ከሐምሌ 8 እስከ 12 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ፒያሳ በሚገኘው ኤሌክትሪክ ህንጻ ምድር ወለል ቢሮ ቁጥር 001 መከራየት የምትፈልጉትን የቦታ ስፋትና ወለል በመጥቀስ በንግድ ቤቱ ባለቤት/ህጋዊ ወኪል የተፈረመ የኪራይ ፍላጎት ማሳወቂያ ደብዳቤ እንድታስገቡ እያሳወቅን፤ መሟላት የማሚገባቸው
መስፈርቶችም፡-
- ከዚህ ቀደም በአካባቢው የንግድ አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩ ስለመሆኑ ማስረጃ የሚያቀርቡ፣
- የታደሰ ንግድ ፍቃድና የዘመኑ ግብር መክፈላቸው ማረጋገጫ የሚያቀርቡ፣
- ተቋማችን በሚያስቀምጠው የህንጻ አስተዳደር ህግና አሰራር ለመተዳደር ዝግጁ የሆኑ፣
- ምሽትን ጨምሮ የከተማ አስተዳደሩ በሚያስቀምጠው የጊዜ ገደብ አገልግሎት የሚሰጡ፣
- ተቋማችን በሚያወጣው የገበያ ኪራይ ዋጋ ተመን ኪራይ የሚከፍሉ፣
ተቋማችንም የሚቀርበውን የተከራዮች ብዛትና የቦታ ኪራይ ፍላጎት መሰረት በማድረግ ከሐምሌ 12 ቀን በኋላ ቀጣይ ሂደቱን የሚያሳውቅ ይሆናል፡፡
በዚህ አጋጣሚ ክቡራን ደንበኞቻችን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋናው መ/ቤት ሜክሲኮ አካባቢ በሚገኘው ንብ ባንክ ህንጻ ላይ የተዛወረ መሆኑን በአክብሮት እናሳውቃለን።
ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት


















