የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በከተማ አስተዳደሩ በተለያዩ ክፍለ ከተሞች ተገንብተው በተጠናቀቁ የ40/60 የጋራ ህንጻዎች ላይ የሚገኙ 1,735 ንግድ ቤቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በሽያጭ ማስተላለፍ ይፈልጋል።
በመሆኑም ኮርፖሬሽኑ ለጨረታ ያቀረባቸውን የ40/60 ንግድ ቤቶች ተወዳድሮ መግዛት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከሚያዝያ 20 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 21 የሥራ ቀናት (ቅዳሜን ሙሉ ቀን ጨምሮ) ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ምሽት 11፡30 ድረስ በአካል በመቅረብ የማይመለስ ብር 1000.00/አንድ ሺህ በመክፈል መግዛት ይችላል፡፡



















