የጨረታ ማስተካከያ እና የጨረታ ጊዜ ማራዘሚያ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካስገነባቸው ፕላዛና መኪና ማቆሚያ ውስጥ ለንግድ አግልግሎት የሚውሉ
- ሳርቤት ፕላዛና መኪና ማቆሚያ ውስጥ የሚገኙትን ንግድ ቤቶችን በአሜሪካ ዶላር ኪራይ ተመን፣
- ሳርቤት ፕላዛና መኪና ማቆሚያ ውስጥ የሚገኙትን መጋዘን፣
- የካ 2 መኪና ማቆሚያ ዉስጥ የሚገኙትን ንግድ ቤቶች፣
- 4 ኪሎ ፕላዛ ውስጥ የሚገኙትን ንግድ ቤቶች በኢትዮጵያ ብር የኪራይ ጨረታ አየር ላይ መዋሉ ይታወቃል፡፡
ሆኖም በወጣዉ ጨረታ ሰነድ ላይ ከዚህ በታች በተዘረዘረዉ መሰረት ማስተካኪያ መደረጉን እንገልፃለን፡፡
- የቤቶች መረጃ ላይ የእንግሊዝኛ ትርጉም ላይ የሳርቤት ሳይት ከቤት ቁጥር B1-10 እስከ ቤት ቁጥር B2-31 ድረስ shop በሚል የወጣዉ የቤቱ አይነት Store በሚል የተስተካከለ መሆኑን
- አራት ኪሎ ሳይት ላይ የቤት ቁጥር 031 እና 032 ከጨረታዉ የተሰረዘ መሆኑን
- የጨረታ ሰነድ ሽያጭ ቀን ለ15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ማለትም እስከ ሰኔ 10/2017 ድረስ የተራዘመ መሆኑን እናሳዉቃለን፡፡
ማሳሰቢያ፡- ጨረታዉ የሚከፈትበት ቀን ከ11/10/2017 እስከ 13/10/2017 ዓ.ም በጨረታ ሰነዱ ላይ በተቀመጠዉ ቅደም ተከተል መሰረት ይሆናል፡፡
ምንጭ፡ አዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ቢሮ



















