የጨረታ ጊዜ ማራዘሚያ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካስገነባቸው ፕላዛና መኪና ማቆሚያ ውስጥ ለንግድ አግልግሎት የሚውሉ ሳርቤት ፕላዛና መኪና ማቆሚያ ውስጥ የሚገኙትን ንግድ ቤቶችን በአሜሪካ ዶላር ኪራይ ተመን፣ ሳርቤት ፕላዛና መኪና ማቆሚያ ውስጥ የሚገኙትን መጋዘን ፣የካ 2 መኪና ማቆሚያ ዉስጥ የሚገኙትን ንግድ ቤቶች፣4 ኪሎ ፕላዛ ውስጥ የሚገኙትን ንግድ ቤቶች በኢትዮጵያ ብር የኪራይ ጨረታ አየር ላይ መዋሉ ይታወቃል፡፡
የጨረታ ሰነድ ሽያጭ በድጋሚ ማራዘም በማስፈለጉ የጨረታ ሰነድ ሽያጭ እስከ ሰኔ 16/2017 ዓ.ም ጠዋት 4፡00 ድረስ የተራዘመ መሆኑን እናሳዉቃለን፡፡ ጨረታዉ ሰኔ 16/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ( አራት ሰዓት) ተዘግቶ በዚሁ እለቱ 5፡00 (አምስት ሰዓት) ላይ ይከፈታል፡፡
ማሳሰቢያ፡- ጨረታዉ የሚከፈተዉ
- በቀን ሰኔ 16/2017 ዓ.ም ጠዋት 5፡00 የሚከፈተው በጨረታ ሳጥን ቁጥር 1 በየካ ክ/ከተማ የካ 2 ሳይት የሚገኙ ንግድ ቤቶች፣ በሙሉ ይሆናሉ፡፡
- በቀን ሰኔ 17/2017 ዓ.ም ጠዋት 3፡00 የሚከፈተው በጨረታ ሳጥን ቁጥር 2 በልደታ ክ/ከተማ ሳርቤት ፕላዛ እና መኪና ማቆሚያ የሚገኘው ሳርቤት ፕላዛ እና ንግድ ቤቶች በሙሉ ይሆናሉ፡፡
- በቀን ሰኔ 18/2017 ዓ.ም ጠዋት 3፡00 የሚከፈተው በጨረታ ሳጥን ቁጥር 3 በአራዳ ክ/ከተማ አራት ኪሎ ፕላዛ እና ንግድ ቤቶች በሙሉ ይሆናሉ፡፡
ምንጭ፡ አዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ቢሮ



















