• BetBegara.com
  • Buy
  • Rent
  • Sale
  • Services
  • Contact Us
Betegna - ቤተኛ | Ethiopian Housing and Real Estate News & Insights
Advertisement
  • Home
  • Guides
    • Buying Guide
    • Renting Guide
    • Selling Guide
    • Knowledge Base
  • Mortgage
  • Technology
  • Legal
    • Proclamations (አዋጅ)
    • Regulations (ደንብ)
    • Directives (መመሪያዎች)
    • Community Complaints
    • Corruption (ሙስና)
  • Tender
    • Auction (ሐራጅ)
    • Land Lease (የመሬት ሊዝ)
    • Request for EOI
  • Project Highlight
  • More
    • Community & CSR
    • Construction & Projects
    • Construction Material Supply
    • Design & Innovation
    • Public Housing
    • Insights & Profiles
    • Sales & Marketing
    • Property Handover
    • Global
    • Contact Us
No Result
View All Result
Sell, Buy, Rent
  • Home
  • Guides
    • Buying Guide
    • Renting Guide
    • Selling Guide
    • Knowledge Base
  • Mortgage
  • Technology
  • Legal
    • Proclamations (አዋጅ)
    • Regulations (ደንብ)
    • Directives (መመሪያዎች)
    • Community Complaints
    • Corruption (ሙስና)
  • Tender
    • Auction (ሐራጅ)
    • Land Lease (የመሬት ሊዝ)
    • Request for EOI
  • Project Highlight
  • More
    • Community & CSR
    • Construction & Projects
    • Construction Material Supply
    • Design & Innovation
    • Public Housing
    • Insights & Profiles
    • Sales & Marketing
    • Property Handover
    • Global
    • Contact Us
No Result
View All Result
Betegna - ቤተኛ | Ethiopian Housing and Real Estate News & Insights
No Result
View All Result
የውጭ ዜጎች የቤት ባለቤትነት መመሪያ

የውጭ ዜጎች የቤት ባለቤትነት መመሪያ

Desalegn Kebede by Desalegn Kebede
August 16, 2026
in Insights & Profiles
A A
0
0
SHARES
Share on FacebookShare on LinkedIn

እንደ አንድ በጉዳዩ የሁለተኛ ዲግሪ ማሟያ ጽሁፉን እንደሰራ ዜጋ ገርበብ ብሎ የተከፈተው የውጭ ሀገር ዜጎች በኢትዮጵያ ውስጥ የመኖሪያ ቤት ባለቤትነት መብት የሚሰጠው መመሪያ በዚህ ሳምንት በስራ ላይ መዋሉን ተከትሎ በውስጡ ከያዛቸው መሰረታዊ ጉዳዮች ወሳኞቹን ነቅሼ ከተወሰኑ ሀገራት መመሪያዎች ጋር አነጻጽሬ በሚከተለው መልክ አቅርቤዋለሁ።

ይህ ሰነድ በከተማና መሰረተ-ልማት ሚኒስቴር የወጣው መመሪያ ቁጥር 1147/2018 ሲሆን፤ የውጭ ሀገር ዜጎች በኢትዮጵያ ውስጥ የመኖሪያ ቤት ባለቤት የሚሆኑበትን ዝርዝር የህግ አሰራር እና መመሪያዎችን ያስቀምጣል።

ይህ መመሪያ የሀገሪቱን የሪል እስቴት ዘርፍ ለማነቃቃት እና የውጭ ምንዛሬ ክምችትን ለማሳደግ ታስቦ የወጣ ነው።

ሀ) ዋና ዋና መስፈርቶች
ማንኛውም የውጭ ሀገር ዜጋ በሀገሪቱ ውስጥ ቤት ለመግዛት ወይም ለመስራት ከሚኒስቴሩ ፈቃድ ማግኘት አለበት።
የሚከተሉትንም ማሟላት ይጠበቅበታል፡-

  • የጉዞ ሰነዶች፦ የፀና ፓስፖርት፣ የመግቢያ ቪዛ ወይም ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ።
  • የወንጀል ታሪክ፦ ከሚኖርበት ሀገር የተሰጠ ከወንጀል ነጻ የመሆን ማረጋገጫ ማስረጃ።
  • የገንዘብ ማስረጃ፦ ለቤቱ የሚያስፈልገውን አነስተኛ የገንዘብ መጠን በባንክ ገቢ ማድረጉን የሚያረጋግጥ ማስረጃ።
  • የሰላምና ደህንነት ማረጋገጫ፦ ከሀገር ሰላም፣ ደህንነት፣ ፀጥታና ከህዝብ ሞራል ጋር የተያያዘ ክልከላ የሌለበት መሆን።

ለ) ዝቅተኛ የገንዘብ መጠን እና የቤት ብዛት ገደብ:-
ማንኛውም የውጭ ሀገር ዜጋ ሊኖረው የሚችለው ከፍተኛው የቤት ብዛት አንድ (1) ብቻ ነው። ለመኖሪያ ቤት ባለቤትነት የሚያስፈልገው አነስተኛ የውጭ ምንዛሬ መጠን እንደየአካባቢው ይለያያል፦

  • 150,000 ዶላር፦ በአዲስ አበባ ከተማ እና በሸገር ከተማ።
  • 120,000 ዶላር፦ በድሬዳዋ አስተዳደር ፣ በኦሮሚያ፣ በአማራ፣ በትግራይ፣በሲዳማ እና በሌሎች ዋና ዋና ክልሎች። ( ሸገርና ኦሮሚያን የተለያየ መስፈርት ያስቀምጣል)
  • 100,000 ዶላር፦ በአፋር፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና በጋምቤላ ክልሎች።

ሐ) ከሌሎች ሀገራት ህጎች ጋር ማነጻጸሪያ (Comparative Analysis)
የኢትዮጵያን አዲሱን መመሪያ ከዓለም አቀፍ የሪል እስቴት ገበያዎች (ዱባይ፣ ቱርክ፣ ደቡብ አፍሪካ) እና ከጎረቤት ሀገራት (ኬንያ፣ ሩዋንዳ) ጋር ስናነጻጽረው የሚከተሉትን ህጎች እናገኛለን፦

፩) የመሬት ባለቤትነት (Land Tenure)፦
◦ ኢትዮጵያ፣ ኬንያ እና ሩዋንዳ፦ የውጭ ዜጎች ህንጻውን/ቤቱን ብቻ ነው በባለቤትነት መያዝ የሚችሉት፤ መሬቱ ግን የመንግስት ሆኖ በሊዝ (Leasehold) መብት ነው የሚተዳደረው። የኬኒያ በተለየ ሁኔታ ህንጻውንም በሊዝ ነው የሚያስተዳድረው)

◦ ዱባይ (UAE)፦ በልዩ ሁኔታ በተፈቀዱ ቀጠናዎች (Designated Freehold Areas) ውስጥ የውጭ ዜጎች መሬቱንም ሆነ ቤቱን 100% በቋሚነት (Freehold) ሙሉ በሙሉ መግዛት ይችላሉ።

◦ ደቡብ አፍሪካ፦ ለውጭ ዜጎች እጅግ ክፍት የሆነ ህግ አላት፤ ማንኛውም የውጭ ዜጋ በአፓርትመንትም ሆነ በከተማ መሬት ላይ ሙሉ የቋሚ (Freehold) ባለቤትነት መብት አለው

፪) የመግቢያ የገንዘብ ገደብ (Minimum Investment Threshold)፦
◦ ኢትዮጵያ፦ የ150,000 የእሜሪካን ዶላር ዝቅተኛ የዋጋ ገደብ (በአዲስ አበባ) በማስቀመጥ የውጭ ዜጎች ግዥ በከፍተኛው የገበያ ደረጃ ላይ እንዲገደብ አድርጋለች።

◦ ዱባይ (UAE)፦ ቤት ለመግዛት ምንም ዓይነት ዝቅተኛ የዋጋ ገደብ የለም። ነገር ግን የ2 ዓመት ነዋሪነት ቪዛ ለማግኘት ቢያንስ የ 750,000 AED (ወደ 204,000 ዶላር) ንብረት መግዛት ያስፈልጋል። የ10 ዓመት ወርቃማ ቪዛ (Golden Visa) ለማግኘት ደግሞ ቢያንስ 2 ሚሊዮን AED (544,000 ዶላር) ንብረት መግዛት ይጠይቃል።

◦ ቱርክ፦ የውጭ ዜጎች ለማንኛውም ዋጋ ቤት መግዛት ይችላሉ፤ ነገር ግን በሪል እስቴት ኢንቨስትመንት የቱርክን ዜግነት (Citizenship by Investment) በቀጥታ ለማግኘት ቢያንስ የ400,000 ዶላር ንብረት መግዛት እና ንብረቱን ለ3 ዓመታት አለመሸጥ ግዴታ ያስቀምጣሉ።

◦ ደቡብ አፍሪካ፣ ኬንያ እና ሩዋንዳ፦ የውጭ ዜጎች ንብረት ለመግዛት የሚጠየቁበት ምንም ዓይነት ዝቅተኛ የዶላር የዋጋ ገደብ የለም፤ እንደየአካባቢው የገበያ ዋጋ በነጻነት መግዛት ይችላሉ።

፫) የቤት ብዛት ገደብ (Property Quantity)፦
◦ ኢትዮጵያ እና ሩዋንዳ፦ የውጭ ዜጋን በግል ስሙ በአንድ (1) የመኖሪያ ቤት ብቻ ይገድባሉ።
◦ ዱባይ፣ ቱርክ እና ደቡብ አፍሪካ፦ የውጭ ዜጎች የገንዘብ አቅማቸው እስከፈቀደ ድረስ ምንም ዓይነት የቤት ብዛት ገደብ ሳይደረግባቸው በርካታ ቤቶችን እና አፓርትመንቶችን መግዛት፣ ማከራየት እንዲሁም መልሰው መሸጥ ይችላሉ።

መ) የፈቃድ ቆይታ እና ምዝገባ

  • የአንድ ዓመት ገደብ፦ የሚሰጠው ፈቃድ የሚያገለግለው ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ ለአንድ ዓመት ብቻ ነው።
  • ማራዘሚያ፦ ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ቤት መግዛት ካልተቻለ ተጨማሪ የ1 ዓመት ማራዘሚያ ሊሰጥ ይችላል።
  • የገንዘብ መመለስ፦ ፈቃዱ ተራዝሞለት ግዥ ካልፈጸመ፣ በዝግ የባንክ ሂሳብ የተቀመጠው ገንዘብ ይመለስለታል።
  • ባለቤትነትን ማስመዝገብ፦ ቤት ከገዛበት ቀን ጀምሮ በ30 የስራ ቀናት ውስጥ ለሚኒስቴሩ ማሳወቅ አለበት。

ሠ) ክልከላዎች እና በባለቤትነት ሊያዙ የማይችሉ ቤቶች
የሚከተሉትን የቤት አይነቶች በውጭ ሀገር ዜጋ በባለቤትነት ሊያዙ አይችሉም፦

  • በመንግስት ቀጥተኛ ድጎማ የተገነቡ የጋራ መኖሪያ ቤቶች (ኮንዶሚኒየም)።
  • ለመንግስት ወይም ለትርፍ ያልተቋቋሙ ህዝባዊ መኖሪያ ቤቶች።
  • መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች (NGO) ወይም በመንግስት ድጋፍ የተገነቡ ቤቶች።
  • በህብረት ስራ ማህበራት የተገነቡ መኖሪያ ቤቶች።
    እንዲሁም በሽብር፣ በህገወጥ የሰዎች ወይም የጦር መሳሪያ ዝውውር፣ በዕጽ፣ በገንዘብ ማጭበርበር፣ በከባድ ሙስና እና በሳይበር ወንጀል የተጠረጠረ ወይም ጥፋተኛ የተባለ ሰው ቤት መግዛት አይችልም።

ረ) አስተዳደራዊ እርምጃዎች እና የገንዘብ መቀጮዎች
መመሪያውን መጣስ በዶላር የሚቀጣ ከፍተኛ የገንዘብ መቀጮዎችን ያስከትላል፦

  • ቤቱን ላልተፈቀደ ወይም ለህገ-ወጥ ዓላማ መጠቀም፦ ከ1,000 እስከ 3,000 ዶላር መቀጮ።
  • ያለ ሚኒስቴሩ ፈቃድ ቤት ወይም መሬት ይዞ መገኘት፦ ከ2,000 እስከ 5,000 ዶላር መቀጮ።
  • አነስተኛውን የካፒታል መጠን ሳያሟሉ ቤት ገዝቶ መገኘት፦ ከ500 እስከ 2,000 ዶላር መቀጮ።
  • ሀሰተኛ ማስረጃ ማቅረብ ወይም ለመጠቀም መሞከር፦ ከ3,000 እስከ 5,000 ዶላር መቀጮ።
  • ህገ-ወጥ የቤት ባለቤትነትን የፈቀደ፣ የረዳ ወይም የተባበረ ማንኛውም ሰው፦ ከ30,000 እስከ 50,000 የኢትዮጵያ ብር መቀጮ።

በጥቅሉ ሲገመገም ተዘግቶ ለነበረ የቤት ባለቤትነት መብት ጥሩ የሚባል መመሪያ ነው። ይህ መመሪያ በቀጣይ ለቤት ገዢዎች የሚሰጡ እንደ በአምስት ዓመት በቪዛ የተገደቡ የመኖሪያ መብቶች እየተሻሻሉ ሲሄዱ

  • የሪል እስቴት ዘርፉ ለሀገራችን የውጭ ገንዘብ ፍሰት ( FDI) ጥሩ አስተዋጽኦ ያደርጋል።
  • በቤት ግብይት ከሚገኘው ገቢ ባሻገር ግንባታ የሚታየውን የግንባታ ጥራት ደረጃ በማሻሻል በኢንተርናሽናል ደረጃ ተመራጭ የሆኑ ቤቶች ግንባታን ያላምዳል፣
  • የግንባታ ቴክኖሎጂና የእውቀት ሽግግርን ያበረታታል
  • በአንድ ዓመት ገደብ የተወሰነው የግብይት ጊዜ የግንባታ ፍጥነትን ያሻሽላል
  • ተገንብተው ገዢ ላጡ በንጽጽር ቅንጡ ለሚባሉ ቤቶች ገበያውን ያሞቅላቸዋል
  • የታክስ ግኝትን ያሳድጋል
  • ቤት ገዢዎች በሀገራችን በሌሎች ኢንቨስትመንቶች ውስጥ ተሳታፊ ለመሆን ያነሳሳቸዋል
Tags: Ethiopiaforeign nationalsforeign property ownershipHousingproperty lawreal estate regulationየውጭ ዜጎች
Previous Post

የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ለማግኘት ምን ምን ሰነዶች ያስፈልጋሉ?

Next Post

የፌስቡኩ መስራች ማርክ ዙከርበርግ በአየርላንድ የ19ኛው ክፍለ ዘመን ታሪካዊ ቤተ-መንግስት (ካስል) ገዙ

Desalegn Kebede

Desalegn Kebede

ኢንጂነር ደሳለኝ ከበደ የሲቪል ምህንድስና ባለሙያ፣ የሪል እስቴት አማካሪ፣ አሰልጣኝ እና ጸሐፊ ሲሆኑ፤ በግንባታ፣ በሪል እስቴት ስልጠና እና በገበያ ጥናት ዘርፎች የሚታወቀውን አቡቀለምሲስ ግሩፕ (Abukelemsis Group) መሥራችና ዋና ሥራ አስኪያጅ ናቸው።

ተዛማጅ ጽሑፎች

የሪል እስቴት አልሚዎች ማህበር የ7% የብድር ወለድ ጥያቄ በባለሙያዎች መካከል ያስነሳው ክርክር
Insights & Profiles

የሪል እስቴት አልሚዎች ማህበር የ7% የብድር ወለድ ጥያቄ በባለሙያዎች መካከል ያስነሳው ክርክር

November 18, 2026
በከፊል የተጠናቀቁ አፓርትመንቶች መኖሪያ ቤቶች አይደሉም
Insights & Profiles

በከፊል የተጠናቀቁ አፓርትመንቶች መኖሪያ ቤቶች አይደሉም

September 25, 2026
ተሾመ ግርማ በቴምር ፕሮፐርቲስ የሽያጭና ማርኬቲንግ ሥራ አስኪያጅ፤ ቀደም ሲል የሀሞና መስራችና በአያት ሪል እስቴት የሽያጭ ሰራተኛ
Insights & Profiles

በስምንት ዓመታት የሪል እስቴት ጉዞዬ ከ1,000 በላይ ቤቶችን ለመሸጥ የቻልኩበት ሚስጥር

September 25, 2026
Next Post
የፌስቡኩ መስራች ማርክ ዙከርበርግ በአየርላንድ የ19ኛው ክፍለ ዘመን ታሪካዊ ቤተ-መንግስት (ካስል) ገዙ

የፌስቡኩ መስራች ማርክ ዙከርበርግ በአየርላንድ የ19ኛው ክፍለ ዘመን ታሪካዊ ቤተ-መንግስት (ካስል) ገዙ

  • Trending
  • Comments
  • Latest
የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የወጣ አዋጅ 721/2004

የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የወጣ አዋጅ 721/2004

April 23, 2024
ስለ ግብር የሚከፈልበት የቤት ኪራይ ገቢ

ስለ ግብር የሚከፈልበት የቤት ኪራይ ገቢ

April 6, 2024
በአዲስ አበባ የቤት ሽያጭ ዋጋ ተመን ላይ በድጋሚ ማሻሻያ ተደረገ

በአዲስ አበባ የቤት ሽያጭ ዋጋ ተመን ላይ በድጋሚ ማሻሻያ ተደረገ

April 3, 2024
የመሬት ልማትና አስተዳር ደንብ ቁጥር 163/2016

የመሬት ልማትና አስተዳር ደንብ ቁጥር 163/2016

April 22, 2024
ስለ ሪል እስቴት ምን ያውቃሉ?

ስለ ሪል እስቴት ምን ያውቃሉ?

August 18, 2023
Home pic

ቤት ለሚገዙ እና ለሚሸጡ አካላት ማሳሰቢያ ተሰጠ

0
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤት አቅርቦትን ለማሳደግ የሚያስችል ውይይት ከሪል እስቴት አልሚዎች ጋር ውይይት አደረገ!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤት አቅርቦትን ለማሳደግ የሚያስችል ውይይት ከሪል እስቴት አልሚዎች ጋር ውይይት አደረገ!

0
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ያስተዋወቀበትን የገርጂ መኖሪያ መንደር ፕሮጀክት ሊያስመርቅ ነው

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ያስተዋወቀበትን የገርጂ መኖሪያ መንደር ፕሮጀክት ሊያስመርቅ ነው

0
ባለ 9 ወለል ህንፃ በተጀመረ በ69ኛ ቀኑ ተጠናቀቀ!!

ባለ 9 ወለል ህንፃ በተጀመረ በ69ኛ ቀኑ ተጠናቀቀ!!

0
ስለ ሪል እስቴት ምን ያውቃሉ?

ስለ ሪል እስቴት ምን ያውቃሉ?

0
የሪል እስቴት አልሚዎች ማህበር የ7% የብድር ወለድ ጥያቄ በባለሙያዎች መካከል ያስነሳው ክርክር

የሪል እስቴት አልሚዎች ማህበር የ7% የብድር ወለድ ጥያቄ በባለሙያዎች መካከል ያስነሳው ክርክር

November 18, 2026
በጋዜቦ አደባባይ አካባቢ በግንባታ ሂደት ላይ ከነበረ ሕንጻ ላይ የወደቁ ሦስት ሠራተኞች ሕይወታቸውን አጡ

በጋዜቦ አደባባይ አካባቢ በግንባታ ሂደት ላይ ከነበረ ሕንጻ ላይ የወደቁ ሦስት ሠራተኞች ሕይወታቸውን አጡ

November 14, 2026
በ5 ዓመታት ቤቶችን ገንብተን ለማስረከብ የገባነውን ቃል በተግባር ለማረጋገጥ እየተጋን ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

በ5 ዓመታት ቤቶችን ገንብተን ለማስረከብ የገባነውን ቃል በተግባር ለማረጋገጥ እየተጋን ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

November 13, 2026
የ1.5 ሚሊዮን መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት ወደ ተግባር ምዕራፍ ተሸጋግሯል

የ1.5 ሚሊዮን መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት ወደ ተግባር ምዕራፍ ተሸጋግሯል

November 12, 2026
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከዩኤን ሃቢታት ዋና ዳይሬክተር አናክላውዲያ ሮስባክ ጋር መወያየታቸውን ገለፁ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከዩኤን ሃቢታት ዋና ዳይሬክተር አናክላውዲያ ሮስባክ ጋር መወያየታቸውን ገለፁ

November 11, 2026

ብዙ የተነበቡ

  • የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የወጣ አዋጅ 721/2004

    የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የወጣ አዋጅ 721/2004

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ስለ ግብር የሚከፈልበት የቤት ኪራይ ገቢ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአዲስ አበባ የቤት ሽያጭ ዋጋ ተመን ላይ በድጋሚ ማሻሻያ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የመሬት ልማትና አስተዳር ደንብ ቁጥር 163/2016

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ስለ ሪል እስቴት ምን ያውቃሉ?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Categories

  • Community & CSR (28)
  • Construction & Projects (29)
  • Construction Material Supply (9)
  • Design & Innovation (18)
    • Architecture (2)
    • Technology (14)
  • Global (4)
  • Insights & Profiles (20)
  • Legal Updates (89)
    • Community Complaints (8)
    • Corruption (ሙስና) (2)
    • Directives (መመሪያዎች) (1)
    • Proclamations (አዋጅ) (7)
    • Regulations (ደንብ) (2)
  • Mortgages & Finance (14)
  • Property Handover (16)
  • Public Housing (71)
  • Real Estate Guides (13)
    • Buying Guide (3)
    • Knowledge Base (1)
    • Renting Guide (2)
    • Selling Guide (7)
  • Sales & Marketing (67)
  • Tenders & Bids (60)
    • Land Lease (29)
    • Request for EOI (1)
  • Home
  • Guides
  • Mortgage
  • Highlights
  • Legal Updates
  • Tenders & Bids
Betegna Logo Footer

Betegna – ቤተኛ, powered by Betbegara.com, is a media platform that focuses on Ethiopian housing and real estate news, developments, technology, policies, and lifestyle.

© 2026 Betegna – ቤተኛ | Ethiopian Housing and Real Estate News & Insights

  • Home
  • Guides
    • Buying Guide
    • Renting Guide
    • Selling Guide
    • Knowledge Base
  • Mortgage
  • Technology
  • Legal
    • Proclamations (አዋጅ)
    • Regulations (ደንብ)
    • Directives (መመሪያዎች)
    • Community Complaints
    • Corruption (ሙስና)
  • Tender
    • Auction (ሐራጅ)
    • Land Lease (የመሬት ሊዝ)
    • Request for EOI
  • Project Highlight
  • More
    • Community & CSR
    • Construction & Projects
    • Construction Material Supply
    • Design & Innovation
    • Public Housing
    • Insights & Profiles
    • Sales & Marketing
    • Property Handover
    • Global
    • Contact Us
No Result
View All Result
Sell, Buy, Rent